February 21, 2019
https://youtu.be/9-3g3nt3-x0
https://youtu.be/9-3g3nt3-x0
ህወሃት ለጦርነት እያደረገ ያለውን ወታደራዊ ስልጠና እያጠናቀቀ መሆኑ ታወቀ!!
(Ayalew Menber)
“ከክልል 3 (አማራ ክልል) ጋር ለሚኖረን ጦርነት ትዋጋላችሁ” ህወሃት
“ከእኛ ህዝብ ጋር አንዋጋም” ህወሃት ለወታደራዊ ስልጠና ካምፕ ውስጥ ያስገባቸው የራያ ተወላጆች
ህወሃት በራያ አካባቢ በሚገኘው ዞኗ ብቻ ከ25ሺህ በላይ ሰልጣኞችን እያሰለጠነች ነው።የፖለቲካና ወታደራዊ ስልጠናውን ለ12 ቀን ሰልጥኖ ነገር ግን በራያ ጉዳይ ላይ ከህወሃት ጋር ባለመስማማቱ ስልጠናውን አቋርጦ እስከ ትጥቁ አማራ ክልል ቆቦ የገባው የአላማጣው ተወላጅ ስለህወሃት የወታደራዊ ስልጠና በኢሳት በስፋት አብራርቷል።
መሆኒ መውጫ ዋጅራት ገርቢቾ ሀጎስ ወረዳ ሀየሎም አርዓያ ት/ቤት ውስጥ የፖለቲካ ስልጠናውን እንደወሰደ የሚናገረው ይህ ግለሰብ ህወሃት ለምሽግ የሚሆንም በዶዘር እያስተካከለች እንደሆነ ይገልፃል።ከስልጠና ጅምር እስከሚያቋርጥበት ወቅት ከክልል ሶስት ጋር ልንዋጋ ነው ይሉ እንደነበር ያብራራው ሰልጣኙ እነርሱ ጥያቄ ሊጠይቁ ሲሉ እንደሚያፍኗቸው ተናግሯል።240 ሚሊሻ ካለው ከአንድ ወረዳ ብቻ 190 ሚሊሻ ስልጠና እንደገባና ስልጠናው በከፍተኛ የመከላከያ አመራሮች (ተመላሾች ይመስሉኛል) እንደሚሰጥ፣የተሟላ ቁሳቁስ እንዳለ ነው የገለፀው።
ጥሪው ከአማራ ክልል የሚመጣ ሽፍታ እና ኮንትሮባንድን መከላከል የሚል ጥሪ እንደነበር ያብራራው ይህ ሰልጣኝ ወታደር ህወሃት አሁን የጀመረው ሀገራችንን ወደ ውድቀት የሚያስገባ ከመሆኑም ባሻገር ለውጊያ እያዘጋጃቸው ያሉት የወልቃይትና የራያ ሚሊሻዎችን እንደሆነ፣ብዙዎች ግን አንዋጋም እንዳሉ ተናግሯል።
ህወሃት ሰሞኑን ከፍተኛ መሳሪያ የታጠቁ ወታደሮችን ወደ አላማጣ ማስጠጋቷን የአካባቢው ሰዎች ተናግረዋል።
ህወሃት የወታደራዊ ስልጠና እየሰጠች መሆኑን ካለፈው ስምንት ወር ጀምረን በግልፅ ስናሳውቅ ቆይተናል።መጀመሪያ አራት ቦታዎች ላይ የጀመረችውን ስልጠና አሁን በነፍስ ወከፍ እያሰለጠነች ነው።
(N.B በዚህ ዘገባው ኢሳት EBC የሚለውን ስሙን ለመቀየር እየጣረ ነው)
