February 22, 2019

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከአፋር፣ ከሶማሌ፣ ከሐረሪ፣ ከቤንሻንጉል ጉሙዝና ከጋምቤላ ክልል አጋር ፓርቲዎች ጋር እየተወያዩ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአጋር ፓርቲዎች የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ጋር ውይይት እያደረጉ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። በውይይታቸው ወቅት በመደመር እሳቤ የመለወጥና አብሮ የማደግን አስፈላጊነት አስምረውበታል።
ከዚህ ባለፈም ተሳታፊዎቹ ለግል ዕድገት፣ እምነት፣ ርኅራሄ እና በተለይም ማኅበረሰባቸውን ለመምራት ገንቢ ዕሴቶችን እንዲያበለጽጉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
(ኢፕድ)
