February 22, 2019

ሌንጮ ለታ – አብይ አህመድ – ጃዋር ሙሀመድ
አብይ አህመድ – general anesthetic
ጃዋር ሙሀመድ – surgeon
ሌንጮ ለታ – Nurse
ሦስቱ አካላት በተጠናና በተመከረ መልኩ የሥራ ክፍፍል አድርገው በመላ ኢትዮጵያውያን ላይ በተለይም በአማራው ላይ ሴራ እያሴሩ ናቸው። አማራውን ለማዳከም እየሠሩት ያለውን ሴራ በዝርዝር በሌላ ጽሁፍ ማቅረብ ይሻላል።
አብይ አሀመድ ተስፈኛውን ኢትዮጵያዊ በተመረጡ ቃላቶችና ንግግሮች እያደነዘዘ ይገኛል። ይህን በማድረግ ስልጣኑ እስኪደላደል ሰፊው ህዝብ እንዲታገሰው ማድረግ ዋነኛ ዓላማው ነው።
ጃዋር ሙሀመድ በአደባባይ ሲናገር የኖረውን በተግባር ለመፈጸም ኢትዮጵያን ዓይናችን እያየ ቀዶ ጥገና እያካሄደባት ነው። ማስረጃ፦ የቡራዩ ጭፍጨፋ፣ የለገጣፎ፣ ሰንዳፋ፣ አራት ኪሎ የማፈናቀል ሥራ፤ ኦህዴድ ዘርን መሰረት ባደረገው ፌድራሊዝም ላይ ከማንም ጋር ለድርድር አልቀመጥም ማለቱ …ወዘተ አብይና ድርጅቱ በጃዋርና ሌንጮ ቡድን መካሪነት የፈፀሙት ግፍ ነው።
ሌንጮ ለታና ቡድኑ ለአብይ (ኦህዴድ) ከአማራና ትግራይ ውጭ የሆነ ታዛዥና የማይቀናቀን አጋር (alliance) ለማግኘት ከፍተኛ የውስጥ ለውስጥ ሥራ እየሰሩ ናቸው። አብይ ይህን ሥራ ለሌንጮ ለታው ኦዴግ የሠጠበት ዋነኛ ምክንያት አዴፓን ለማዘናጋት ነው። ኦህዴድ በቀጥታ በዚህ ሥራ ቢሳተፍ ከአዴፓ ጋር መለያየትን የሚያስከትል ሲሆን ሌሎችም አካባቢዎች በተለይም በደቡብ ኢትዮጵያውያን (ለምሳሌ በጉራጌ፣ በወላይታ፣ በጌዴኦ፣ በስልጤና ጋሞ ህዝብ) ዘንድ ተቃውሞ እንዳይገጥመው በማሰብ ነው።
ይህ ድፍረት ከየት መጣ?
አክራሪ የኦሮሞ ልሂቃን እንዲህ ብለው ገምግመዋል፦
«የኦሮሞ አክራሪነት ኦሮሞን አንድ አድርጎ ማሳለፍና ማታገል ችሏል። ከሊቅ እስከ ደቂቅ አንድ የጋራ ጠላት ፈጥረናል። ከኦሮሞ ውጭ የሆነው በተለይም ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ የሚጮኸው የእኛን ያህል በአንድ ዕዝ መደራጀት አቅሙ የለውም። በድርጅት ደረጃ የኢትዮጵያ አንድነት የሚሉት ወላዋይና መሬት ላይ መሠረት የሌላቸው ናቸው።
ሌላው ደግሞ በፌስቡክና በየቡናው ለአንድ ሰሞን ከመጮኸ ባለፈ ተሰባስቦና ግንባር ፈጥሮ መፋለም አይችልም። የተበተነ ጩኸት ምንም አይፈጥርም። ስለዚህ ስልጣኑን ተደራጅቶ የተቆጣጠረ ሃይል የፈለገውን ቢያደርግ የሚያስቆመው አይኖርም። የህወሃት ዓይነት የመነጠልና የመሸነፍ ዕጣ በሦስት ምክንያት አይገጥመንም። አንደኛው፦ የህወሃት የድጋፍ መሠረት ከሆነው የትግራይ ህዝብ ቁጥር ፣ የኦህዴድ/ኦዴግ/ጃዋራውያን መሠረት አራት እጥፍ ነው። ሁለተኛ፦ ለፖለቲካ ማዕከሉ ቅርብ መሆን የስነልቦና የበላይነትና ፖለቲካዊ ንቃተ ህሊና ለማህበራዊ መሠረታችን ይሰጣል። ሦስተኛ፦ አብይን በመጠቀም ኢትዮጵያውያንን እና ዓለም ዓቀፉን ማህበረሰብ ማዘናጋት፣ የጃዋርግንባርን (ኦፌኮ+ልፊቃን) በመጠቀም የኦሮሞ ወጣቶችን በደቦ እንዲያስቡ ማድረግና የታዘዙትን ያለምንም ማወላወል እንዲፈጽሙ ማድረግ፣ ሌንጮ ለታን (ኦዴግ) በመጠቀም ከህዳጣን ብሔረሰብ ድርጅቶች ጋር አጋርነት መፍጠር» የሚል ነው።