ከማኮነን ተስፋየ ፌስ ቡክ የተወሰደe

ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀር
አኩሪ ታሪካቸው!!!!!!!
ፍቅሬ ዘርጋው ማን ነው?
.
ፍቅሬ ዘርጋው ከእናቱ ከ ወ/ሮ አዳበሴ ቡታ እና ከአባቱ ከአቶ ዘርጋው ቡሪሳ በ 1940 ዓ.ም በደብረ ዘይት ከተማ ተወለደ። እድሜው ለትምህርት ሲደርስ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን ደብረ ዘይት በሚገኘው በልብነ ድንግል ከተማረ በኋላ የሁለተኛ ደረጃ ትምህትርቱንም ናዝሬት በሚገኘው በ አፄ ገላውድዮስ ገብቶ ተከታትሏል።
በትምህርቱም በጣም ጎበዝ የነበረው ፍቅሬ ዘርጋው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በከፍተኛ ውጤት በማጠናቀቁ ሓረር ይገኝ በነበረውና “የሓረር አካዳሚ” ተብሎ በሚታወቀው ተቋም ተመድቦ ለተወሰነ ግዜ የከፍተኛ ትምህርቱን ሲከታተል ቆይቷል። በምደባውም ብዙ ፍላጎት ያልነበረው ፍቅሬ በሓረር አካዳሚ ለስድስት ወራት ያህል ከተከታተለ በኋላ ከዛ ወጥቶ አዲስ አበባ ስድስት ኪሎ የድሮው ቀዳማዊ ኅ/ስላሤ ዩኒቨርሲቲ ያሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመግባት በህግ ዲግሪ መመረቁ ይታወቃል።
በተማሪው ትግል ከፍተኛ አስተዋፅኦ የነበረው ፍቅሬ ዘርጋው በ 1960 ዎቹ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ማሃበር ( USUAA) ይዘጋጅ በነበረው “ታገል” (STRUGGLE) መፅሄት አዘጋጅ ከነበሩት ግንባር ቀደም የተማሪው መሪዎች አንዱ ነበር።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከተመረቀም በኋላ ወላይታ ውስጥ ይገኝ በነበረውና “ዋዱ እርሻ ልማት” በመባል በሚትወቀው የአመሪካን ድርጅት ውስጥ እየሰራ በነበረበት ወቅት ስኮላርሺፕ አግኝቶ ለከፍተኛ ትምህርት አመሪካን በመሄድ ማስተርሱን በኢኮኖሚክስ ለመስራት ችሏል።
ፍቅሬ ዘርጋው ከአሜሪካን ከተመለሰ በኋላ ከ 1967 ጀምሮ ኤፒድ በመባል ይታወቅ በነበረው ድርጅት በፕላኒንግ ማኔጄርነት ተቀጥሮ ሲሰራ ቆይቷል። በወጣትነቱ ግዜ ጀምሮ ላገሩና ለህዝቡ በጣም ይቆረቆር የነበረው ፍቅሬ ዘርጋው የአፄውን የፊውዳል ስርአት ለመቀየር በተማሪዎች ትግል ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ አድርጓል በ 1964ዓ.ም ኢሕአፓ ከተመሰረተ በኋላ በተወሰነ ግዜ በከፍተኛ አመራር ውስጥ እንደነበረም ይታወቃል።
ፍቅሬ ዘርጋው ለሚወዳት ሓገርና ለሚወደው ህዝብ ከተማሪዎች ትግል፤ ከዚያም በኢሕአፓነት በከተማም በገጠርም በኢሕአሠ ውስጥ ሲታገል ቆይቶ በ 1970 ዓ.ም በወሎ ውስጥ በደርግ ተይዞ በአዲስ አበባ መአከላዊ ለረጂም ግዜ አስከፊ ስዬል ተካሂዶበት በግፍ ተገድሏል።
ይሄንን አረመኔ ፋሺስት ደርግ ነው ያሁኖቹ የድል አጥቢያ አርበኞችና የወያኔ አጋፋሪዎች አገርወዳድ የሚሉን!!
ፍቅሬ ዘርጋው በአሁኑ ሰአት ከወያኔ ጋር እየተዋደቀ ላለው ወጣት ትውልድ አርአያና ምሳሌ ነው። በጣም እንኮራበታለን!!!!!
ነፍስ ይማር ለጀግኖቻችን!!!
የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO)ይቀጥላል !!!
