አለ ያገሬ ሰው፡፡ ታስታውሱ እንደሆን ወያኔ/ኢሕአዴግ ለውጥ ያለውን ድራማ እንደጀመረ ወያኔ/ኢሕአዴግ ሥልጣን ከመልቀቅ በመለስ ራሱን በሥልጣን ለማቆየት ምንም የማያደርገው የማስመሰያ፣ የማታለያ፣ የማጃጃያ እርምጃና የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም!” ብየ ነግሬያቹህ ነበረ፡፡

በዚህም መሠረት እስከአሁን ሲያደርገው የቆየውን መሬት ያልረገጠ የማጃጃያ፣ የመሸንገያ፣ እርምጃዎችን ሲወስድና ሕዝብን ሲሸውድ ቆየ!

ለሁን ደግሞ ከወራት በኋላ አራቱን የኢሕአዴግ ድርጅቶችና አምስቱን አጋር የሚላቸውን ድርጅቶቹን አዋሕዶ አንድ ብሔራዊ (ሀገር አቀፍ) ድርጅት ሆኖ እንደሚወጣ ተዋናይ ዐቢይ ገልጸዋል፡፡

ልብ በሉ ወያኔ/ኢሕአዴግ በዐቢይ በኩል በአዋሳው ጉባኤ የጎሳ ፌዴራሊዝም እንደኛ ብዝኃነት ላለው ሀገር አማራጭ የሌለው ሥርዓት ነው!” ያለውና ዐቢይ ሊቀመንበር ሆኖ የሚመራው ኦዴፓም በጎሳ ፌዴራሊዝሙ አልደራደርም!” ያለው ገና ትናንትና ነው፡፡

በአጭሩ ወያኔ/ኢሕአዴግ የኢትዮጵያን ሕዝብ እያለ ያለው “”የምትፈልጉትን ቅርፅ እይዝላቹሃለሁ ከአንተ ሌላ እራሳችን መርጠን ለሥልጣን የምናበቃው ሌላ ፓርቲ እንፈልጋለን!’ የምትሉትን ነገር ግን ተው!”” ነው እያለን ያለው፡፡

እኛ ደግሞ ወያኔ/ኢሕአዴግን እንዲህ እንለዋሐን፦

ወያኔ/ኢሕአዴግ ሆይ! አንተ እንደፈለክ መገለባበጥና ድራማ መሥራት ትችላለህ፡፡ ከፈለክ በዚህ ችሎታህና ብቃትህ የዓለም አቀፍ የዘርፉ ሽልማቶችን ጠራርገህ መውሰድ ትችላለህ፡፡ እኛ ግን ፍጹም ነጻና የሠለጠነ የፖለቲካ ምኅዳርና አሁንም ፍጹም ነጻ ፍትሐዊና ተአማኒ ምርጫ እንፈልጋለን!!! ይሄንን ማድረግ ካልቻልክና ለዚህ ካልታመንክ ግን ሞኝህን ሒድና እንጨቆረር ፈልግ እሽ???

አምሳሉ