February 25, 2019

ጣናን በተመለከተ ህዝባዊ አጀንዳ ከሆነ ወዲህ ህዝቡ ራሱ ስለሚጠይቅና መንግስትም ትኩረት ስለሚሰጠው እኛ ሌሎች ተግባራት ላይ እናተኩር በሚል ትኩረት ነፍገነው ነበር።
ይሁንና ከጊዜ ወደጊዜ መሻሻሎች ይመጣሉ ስንል እንዲያውም እየተባባሰ ነው።የገንዘብ ችግር ስለነበር እርሱ ከበቂ በላይ ተሰብብሷል፣የባለሙያ ችግርም ስለነበር ምሁራን ለማገዝ ተስማምተው እያገዙ ነው።

ምንም እንኳን በጣና ላይ ቢዝነስ መስራት የሚፈልግና በርካታ ግልፅ ያልሆነ ፍላጎት ያላቸው አካላት ብዙ ሆነው ችግሩን ቢያወሳስቡትም መሰረታዊው የጣና ችግር ግን የአመራር ጥበብን ተላብሶ ችግሩን በዘላቂ የሚፈታ አመራርም ይሁን የተቋም ባለሙያ አለመገኘት ነው።
ይህንን በድፍረት መናገር አለብን።ጣና ህልውናችን ነውና ቁስላችን ነው።ይህንን ተረድቶ የሚሰራ አመራር ያስፈልጋል

ከዚህ በፊትም ተናግሬዋለው።የጣና ችግር የአመራር ነው።
ጣና አጀንዳ እየሆነ እየመጣ ሌላ አጀንዳ እያስተወን ነው።ይህንን ተቋም እኔ ልምራው ብሎ የሚመጣ አመራር መፈለግ አለበት።

ዛሬ የዚህ አማጋ የገዛው ማሽንን እንዲያንቀሳቅሱ የተመደቡ ቴክኒሽያኖች እያዘኑ ነው ያጫወቱኝ።ማሽኑ ሁለት ወር ሙሉ ቁሟል።ነገር ግን በዚህ ሳምንት ሚዲያ ሊመጣ ስለሆነ አንቀሳቅሱት ተብለው እነርሱም በጣና ለምን ይነገዳል? በሚል ቅሬታ አንስተዋል።ይህ ብቸኛ ማስረጃ ሆኖ ባይቀርብም ጣና ፕሮፖጋንዳውና እውነታው እንደተራራቁ ለብዙ ጊዜ በቪዲዮም በፎቶም ቀርቧል።ይህንን ለመደበቅ የሚደረግ ጥረት ለጊዜው ግለሰቦችን ሊጠቅም ይችላል እንጅ ጣናን አልታደገም።በጣም የሚያበሳጨው ደግሞ በጣና የሚነግደው ሀላፊው ብቻ ሳይሆን ጥቂት ባለሙያዎችም ጭምር መሆናቸው ነው።በአባይ ማዶው ገብርኤል እንለምናችሁና እባካችሁ በጣና ላይ ጥቅም ስለማግኘት አታስቡ።እንዴት እንታደገው? ብላችሁ ከክ ከልባችሁ ስሩ።

የክልሉ መንግስት ጣናን በሚመለከት ፈጥኖ ርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን።ይህንን ጉዳይ የሚመራ አካል መድቦ ካላስተካከለው ነገ ራሱን አጣብቂኝ ውስጥ