
አንጋፋው ባለዋሽንት ዮሃንስ አፈወርቅ በ72 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።
አርቲስት ዮሃንስ በተለይም ፍቅር እስከ መቃብር የተተረከበትን ዋሽንት በመጫወት ይታወቃሉ።
ከዚህ ባለፈም ህዝብ ለህዝብ በተሰኘው የኪነ ጥበብ ጉዞ አባል በመሆንም ተሳታፊ ነበሩ።
አርቲስት ዮሃንስ አፈወርቅ በአዲስ አበባ ባህልና አዳራሽ ለረጅም ጊዜ ማገለግላቸውን ከኢቢሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አርቲስት ዮሃንስ ጎጃም በቀድሞው የአገው ምድር አውራጃ ባንጃ ወረዳ ታህሳስ 3 ቀን 1939 ዓ.ም ነበር የተወለዱት።
ስርዓተ ቀብራቸውም በነገው እለት 9 ሰዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ይፈጸማል።
አርቲስት ዮሃንስ አፈወርቅ ባለትዳርና የ4 ወንዶቹና የ1 ሴት ልጅ አባት ነበሩ።
► መረጃ ፎረም – JOIN US
