February 26, 2019

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ የ6 ወራት የስራ አፈጻጸምን ለጨፌ ኦሮሚያ ያቀረቡ ሲሆን፣ በሪፖርታቸው የመሬት ወረራና ሕግ ወጥ ግንባታን ለመከላከል ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸው፣ ህዝቡ የሕግ የበላይነትን በማስከበር ሂደት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡
በክልሉ ተከስቶ የነበረውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት ባለፉት 6 ወራት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን አቶ ለማ ተናግረዋል፡፡
የክልሉ መንግስት ሰላም እንዲኖር እየሰራ ቢሆንም በክልሉ አንዳንድ አከባቢዎች የጸጥታ ችግሮች መከሰታቸውን የገለጹት አቶ ለማ፣ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ችግሩ እንዲከሰት ያደረጉ አካላትን ወደ ሕግ የማቅረብ ስራዎች እየተሰሩ ናቸው ብለዋል፡፡
በተለይ በጉጂና በምዕራብ ጉጂ ዞኖች የተከሰቱትን የጸጥታ ችግሮች በትዕግስትና በሳል አመራር በመስጠት ሁኔታው ወደ ሰላም እንዲመጣ መደረጉን አቶ ለማ በሪፖርታቸው ገልጸዋል፡፡
ህዝቡ ከመጣው ለውጥ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ ስራዎች መሰራታቸውንም አቶ ለማ ገልጸዋል፡፡
የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት በተሰራው ስራ የተለያዩ ፓርቲዎች ወደ አገር ገብተው የፖለቲካ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆናቸው በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡

ሪፖርተር: – መለሰ አምዴ
