አዴፓና ኦዴፓ አዲስ አበባን በጋራ ለማሥተዳደር ተስማሙ!” ተባለ፡፡ ይሄ ዜና ብአዴን ከኦሕዴድ ወይም ኦዴፓ ጋር በሥራ አስፈጻሚ ደረጃ ከለውጥ ወዲህ ባሉ ችግሮች ጉዳይ የሁለትዮሽ ውይይት አደረኩ!” ካለ በኋላ በኢሳት በኩል ትናንትና ያስነገረው ዜና ነው፡፡

በቃ ይሄ ብአዴን የሚባል ፀረ አማራ የአህዮች ቡድን አማራን ማስበላቱንና የአማራን ጥቅም ማስወሰዱን ማስወረሱን ማዘረፉን መቸም ቢሆን አያቆምም ማለት ነው???

ለነገሩ ሕዝቡ ይሄንን መረዳት ተሳነው እንጅ ለባርነት፣ ለአህያነት፣ ለባንዳነት ዲዛይን ተደርጎ (ተተልሞ) የተፈጠረ የሕሊናቢሶች፣ የሆዳሞችና የአህዮች ጥርቅም ይሄንን የተፈጠረበትን ዓላማና ተልእኮ እንዴትና በምንስ ተአምር ሊተውና ሊለወጥ ይችላል???

መሰንበቻውን በኦሕዴድ/ኦዴፓ በሚባሉት የኦነግ ጭፍሮች የተፈጸሙና እየተፈጸሙ ያሉ አፓርታይዳዊ (የዘር መድሏዊ) ተግባሮችንና ግፎችን ተከትሎ የሕዝብ ቁጣ በማየሉ ኦሕዴድ/ኦዴፓ በአጉል ሁኔታ የተጋለጠበትና በዚህም የተከፋው ፀረ አማራውና ቀንደኛው የአማራ ጠላት ብአዴን ሕዝብን ያስቆጡና ሕዝብ ሲጮህባቸው የቆዩ በደሎችና ግፎች ሲፈጸሙ ዝም ብሎ ቆይቶ ወይም በአባሪነት ሲፈጽም ቆይቶ አሁን ኦሕዴድ ችግር ላይ ሲወድቅበት በሥልጣን ክፍፍልና በአሠራር ግድፈቶች ዙሪያ ለምሳሌ አንባቸው የአዲስ አበባ ከንቲባ ሊሆን የነበረውን ቀርቶ ታከለ በመሾሙ፣ ኢፍትሐዊ በሆነ መንገድ በፌዴራልና በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የሥልጣን ቦታዎችን በኦሮሞ ተወላጆች እንዲሞሉ የተደረገበትን አግባብነት የሌለው አሠራር ዙሪያ፣ አግባብነት በሌለው መንገድ የአዲስ አበባ የነዋሪነት መታወቂያ አሰጣጥ ዙሪያ…. በአዴፓና በኦዴፓ ሥራ አስፈጻሚዎች ደረጃ ውይይት ተደርጎ መግባባት ላይ ተደርሷል ችግሮቹን ገምግመን ለውጡን በጋራ ለማስቀጠል ተስማምተናል!” የሚል ዜና በማስነገር ሕዝቡ በቃ መፍትሔ ተገኝቷል!” ብሎ ከቁጣውና ያደርግ ይሆናል ተብሎ ከሚፈራው ዐመፅ እንዲመለስ ለማድረግ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

ልብ በሉ ዜናው ስሕተቶቹ መፈጸማቸውንና አግባብ አለመሆኑን መግባባት ላይ ተደርሷል ለውጡን በጋራ ለማስቀጠል ተስማምተናል!” አለ እንጅ ግልጽ በሆነ መንገድ ችግሮቹ ፍትሐዊ ክፍፍልንና ዕኩል ተጠቃሚነትን መሠረት አድርጎ በዚህ በዚህ መልኩ ይሄን ይሄን በማድረግ ይታረማሉ!” የሚል አንድም ነገር የለውም!!!

በኦሕዴድ/ኦዴፓ በሰፊው እየተደረገ ስላለው የመሬት ወረራ ጉዳይም ማለትም በሽታዎች ለሚቆጠሩ የሱማሌ ክልል ከሚሉት ተፈናቀሉ ለሚሏቸውና በተመሳሳይ መልኩ የተፈናቀሉ የሌሎች ብሔረሰቦችን ተፈናቃዮች ፈጽሞ ባላካተተ መልኩ በሽታዎች ለሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች ብቻ ሕጋዊነትና ፍትሐዊነት በሌለው መልኩ በአዲስ አበባ የተለያዩ ስፍራዎች ቤት ገንብተው ለማስፈር በሰፊው እየተሠራ ስላለው መጠነሰፊ አፓርታይዳዊ ወንጀል ግን ምንም ያለው ነገር የለም፡፡

እንኳን ለሌሎች ብሔረሰቦች ተፈናቃይ ዜጎችም ዕኩል መብትና ዕድል ተሰጥቷቸው አዲስ አበባ እንዲሠፍሩ ሊደረግ ቀርቶ ጭራሽ የራሳቸውን ጥሪት አፍስሰው ደም ተፍተው ባፈሩት የሠሩትን ቤት እላያቸው ላይ እንዲፈርስና እንዲፈናቀሉ እየተደረገ ከአዲስ አበባና አካባቢዋ እንዲጸዱ ሲደረግ የዚህች ሀገር ዜጋ ኦሮሞ ብቻ ይመስል ኦሮሞ ብቻ ተመርጦ በመንግሥት ወጭ ቤት ተገንብቶለት እንዲሰፍር የሚደረግበት አሠራር አግባብነቱ ምንድን ነው???

ገና ከበፊቱ ጀምሮ ይህ የኦነጎቹ ኢፍትሐዊ በሆነ መንገድ ስለሚያደርጉት የሥልጣንና የመሬት ወረራ ሕዝቡ ጥርጣሬው በማየሉና ስላሳሰበው በድኖቹ እነ አቶ ገዱ አሜሪካን በጎበኙ ጊዜ በፍትሐዊ የሥልጣን ክፍፍል ዙሪያ ከኦሕዴድ ጋር ተደራድራቹሃል ወይ? ተነጋግራቹሃል ወይ?” ተብሎ ሲጠየቅ እኛ ለሥልጣን ሳይሆን ሀገርን ለማዳን ነው የታገልነው!” ብሎ ነበር የመለሰው፡፡

ብአዴን እንዲህ እያለ ኦሕዴድን አይዞህ በርታ!” እያለ ሥልጣን የተባለውን ሁሉ አማራን ጉራጌንእያባረረ በኦነግ ጭፍሮች እንዲሞላ እንዲያደርግ ሲያግዝ ሲተባበር ከቆየ በኋላ አሁን የሕዝብ ቁጣ እያየለ ሲመጣና ወደ ዐመፅ የመቀየር አዝማሚያ ሲያሳይ ወጥቶ እንዲህ ሲል ለሕዝብ ተቆርቁሮ ከመሰላቹህ ማሰብ ማገናዘብ የተሳናቹህ እንደሆናቹህ ዕወቁት!!!

እኔ ግን እላለሁ ዘለዓለም ዓለምህን ስትጃጃል፣ ስትቄል፣ መጫወቻ ስትሆን ለመኖር እንደፈቀድክላቸው አውቀዋልና ከፍተኛ ንቀት በተሞላበት ሁኔታ እንዲህ ሲያጃጅሉህ፣ ሲያቄሉህ፣ ሲጫወቱብህ ይኖራሉ!!!

ኢሳት የሚባለው የደናቁርት ስብስብም መቸም ቢሆን የማይነቃ፣ ካለፈው የማይማር በድን ነውና ወያኔ/ኢሕአዴግ በራሱ የብዙኃን መገናኛዎች እንዲነገሩ የማይፈልጋቸውን ይሄንን መሰል የፖለቲካ ቁማሮቹን አፈትልከው የወጡ መረጃዎች እያስመሰለ በኢሳት በማስነገርና ለሕዝብ እንዲደርስ በማድረግ ጥቅሙን ሲያስጠብቅና ኢሳትንም መጠቀሚያው እንዳደረገው ይቀጥላል፡፡

ኢሳት የሚባል ጣቢያ ባይኖር ኖሮ የሕዝብ ትግል ባልተቀለበሰ ነበር፣ ወያኔ ለውጥ በሚለው ድራማ (ትውንተ ሁነት) ሕዝብን ለማጃጃል ባልቻለ ነበር፡፡ ይሄ ጣቢያ በመኖሩ ከጠቀመው ይልቅ የጎዳው በእጅጉ ይበልጣል፡፡ ከዚህ የተነሣ ኢሳት ለኢትዮጵያ ሕዝብ መርገምት እንጅ በረከት አይደለም!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com