ወልቃይት ላይ እስርና ወከባው ቀጥሏል!
የአማራ ታርጋ ያላቸው ሞተሮች እየተወረሱ ነው
የ80 አመታ ቄስን ጨምሮ አራት ሰዎች በጥምቀት ሰንደቅ አላማ ሰበብ ታስረዋል

ሕወሓት ወልቃይት ላይ ወከባውን ቀጥሏል። ዳንሻ ላይ ከ50 በላይ “አማራ” የሚል ታርጋ ያላቸው ሞተሮች ተወርሰዋል። አንድ ሞተረኛ መንገድ ላይ እያለ ተመትቶ ሆስፒታል ገብቷል። ወልቃይት ውስጥ “አማራ” ታርጋ ያላቸው ሞተሮችን መጠቀም የተለመደ ነው። ብዙ የወልቃይት አማራዎች የሚጠቀሙት አማራ ታርጋ ያላቸውን ሞተሮችን ነው።
በሌላ በኩል አድረመጥ ላይ ሶስት ቀሳውስት ታስረዋል። አንደኛው የ80 አመት አዛውንት ናቸው። አዛውንቱ የጥምቀት ኮከብ ያለው ባንዲራ እንዳይወጣ ሲከለከሉ “ሰንደቅ አላማው ከተከለከለ ታቦቱም አይወጣም” በማለታቸው ክልከላው ተነስቶ ኮከብ የሌለው ሰንደቅ አላማ መውጣቱ ተገልፆአል።
ቀሳውስት ጥምቀት ላይ በወጣ ሰንደቅ አላማ ሰበብ ዛሬ መታሰራቸው ተሰምቷል። የ80 አመቱ ቄስ ጉይ ዘነበ ታፈረ፣ ቄስ አዛናው ጌታሁን፣ ዲያቆን አለማየሁ፣ እንዲሁም ወጣት ደሞዝ መልኬ መታሰራቸው ታውቋል። ወጣት ደሞዝ መልኬ ከአሁን ቀደምም “አማራ ነኝ ብለሃል ” ተብሎ መታሰሩ ተገልፆአል።
