ስለዚህ የአዲስ አበባ ወንዞች ልማት ፕሮጀክት (የሥራ እቅድ) ጉዳይ ይፋ በሆነበት ቅጽበት በጠራና ማንንም ሊገባው በሚችል አመክንዮ ስውር ዓላማውን አስረድቻለሁ፡፡

በዚህ በማይመስል ፕሮጀክት ሰበብ ማለትም የክረምት ወቅት የጎርፍ መፋሰሻ እንጅ ወቅት ሳይገድበው ውኃ የሚፈስበት ቋሚ ወንዝ ለሌላት አዲስ አበባ ደረቅ ወንዟን ወይም የከተማውን ነዋሪ ቆሻሻ ፍሳሽ መፋሰሻን ወንዝ አስመስለው በወንዝ ማልማት ሰበብ እናለማዋለን በሚሉት በሁለቱ ደረቅ ወንዞች ዳርቻ በአራት ሽህ ሔክታር ላይ ያለውን የአዲስ አበባ ነዋሪ ማለትም ባለ250 ካሬ ሜ. ግቢ ቤት ባለቤት የሆነውን ሁለት መቶ ሰማኒያ ሽህ አባወራ የማፈናቀያ ስልት እንደሆነና አፈናቅለውም ወገኖቻቸውን ለማስፈር እንደሆነ ነጥቦችን ጠቅሸ ገልጨ ነበረ፡፡

እንዲያው ሲመስላቹህ ሀገሪቱ በገንዘብ እጥረት ተቆራምዳ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ማስጨረሻ ገንዘብ ጠፍቶ ቆመው ባሉበት በዚህ ሰዓት ይህ የወንዞች ዳርቻ ልማት የተባለ ፕሮጀክት አንገብጋቢ ሆኖ ይመስላቹሃል ይሄ ሁሉ ጥድፊያና ሩጫ ወገኖቸ??? ይመስላቹሃል ወይ??? የምር ይዋጥላቹሃል??? “ትለብሰው የላት ትከናነበው አማራት!” ሆኖም አይደለም፡፡ ይሄ በሆነ በማን ዕድልህ? ነገሩ ግን ሌላ ዓላማ አለው፡፡ አስቀድሜ ገልጨልሃለሁ!!!

ይህ ወንዞችን ለማልማት በሚል ስም የተጠራ የዐቢይ የእራት ግብዣ ስውር ዓላማ ደግሞ የሚገኘውን ገንዘብ ዐቢይና ለማ አዲስ አበባ ላይ ሊያሰፍሩት የመኖሪያ ቤት ግንባታ ላስጀመሩለት ወገናቸው ገቢ የማሰባሰቢያ ዘዴ ነው ሌላ እንዳይመስልህ!!!

እስካሁን በተለያየ መንገድ ቀላል የማይባል ገንዘብ አሰባስበዋል፡፡ በቀደም ለአንቦ ልማት!” በሚል ሽፋን አራት መቶ ሚሊዮን (አእላፋት) ብር አግኝተዋል፣ ቀደም ሲልም በኦነግ ስም ከተለያዩ ባንኮች የተዘረፈ ሰባ ሚሊዮን ብር አግኝተዋል፣ ለዝርፊያ እንዲመቻቸው ሌላውን ኢትዮጵያዊ እያዛወሩና እያባረሩ የራሳቸውን ሰዎች በመሾም በብቸኝነት ከተቆጣጠሯቸው ከፍተኛ ገንዘብና ንብረት ከሚያንቀሳቅሱ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እየተዘረፈ ያለ የሕዝብ ሀብት አለ፣ አሁን ደግሞ በዚህ የአዲስ አበባ ወንዞች ዳርቻ ልማት!” ባሉት ሽፋን የሚያሰባስቡት ገንዘብ አለ፣ በቀጣይ ጊዜያትም ሌሎች ገንዘብ የማሰባሰቢያና የመዝረፊያ ዘዴዎች አሉ፡፡

በእነዚህ መንገዶች ገንዘቡን አሰባስበው ዐቢይና ለማ ጨፌ ኦሮሚያ በሚሉት የምክርቤት ጉባኤ ላይ ሲናገሩ እንደሰማቹሃቸው 500 ሽህ ወገኖቻቸውን የመንግሥትን መሬት በሕገወጥ መንገድ ዘርፈው ቤት በመገንባትና ወገኖቻቸውን በማስፈር የቤትና የመሬት ባለቤት በማድረግ የአዲስ አበባን ዲሞግራፊ (ነባራዊ ምኅዳር) መቀየር ነው የዚህ ሁሉ ሩጫ ዓላማው ሌላ አይደለም፡፡

እንደምታዩዋቸው እነ ዐቢይ አሁን ባላቸው የዘረፋ ተግባርና ከፍተኛ ፍላጎት ከወያኔ የሚስተካከሉ ሆነዋል፡፡ የዘረፉትን መጠን አይደለም እየተናገርኩ ያለሁት፡፡ ለመዝረፍ ያላቸውን ፍላጎትና ቁርጠኝነት እንጅ፡፡ ቀጥሎ ደግሞ ወንጀል በባሕርይው ተነጣጣይ አይደለምና ማለትም አንዱ ወንጀል ሌላን ወንጀል ይስባልና ቀሪዎቹን ወያኔ ሲፈጽምብን የኖራቸውን ግፎችና ወንጀሎች በሚገባ አስተካክለው ሲፈጽሙ የምታዩዋቸው ይሆናል፡፡

እናም ይሄ የአዲስ አበባን የወንዞች ልማት ፕሮጀክት!” የተባለ ነገር ሽፋን ነው!” ነው የምልህ ወገን፡፡ ዓላማው አንተን አፈናቅለው ባንተው ገንዘብ አንተው በነበርክበት ቦታ ላይ ወገኖቻቸውን ማስፈር ነው ሌላ አይደለም፡፡

አንተ በድን መንጋ እስኪ እባክህ ንቃ??? በማይመስልና ሊታመን በማይችል ፕሮጀክት (የሥራ እቅድ) አንተን ሊያጃጅሉህ መሞከራቸው እኮ የሚያሳየው ላንተ ያላቸውን መጠን የለሽ ንቀት እኮነው፡፡ በሚመስል ነገር መታለል እንኳ ያለ ነገር ነው፡፡ ሰው እንዴት በማይመስል ነገር ይታለላልና ይጃጃላልና ተባባሪ ይሆናል???

ሌላው ሁሉ ይቅርና ወንዞቹ ላይ የሚፈሰው ንጹሕ ውኃ ከየት መጥቶ ሊፈስ ነው ወንዞቹ እንደምዕራባውያን የከተማ ወንዞች የአዲስ አበባ ወንዞች ንጹሕ ውኃ ሞልቶ እየፈሰሰባቸው መዝናኛ ሊሆኑ የሚችሉት???” ብለህ እንኳ አትጠይቅም??? የምትጠጣውን ውኃ እንደፍላጎትህ ያላገኘህ ሕዝብ ሆነህ እያለህ እንዴት ይሄንን የማታለያ ወሬ ልታምን ቻልክ??? ኧረ ተው ኧረ ተው በቅዠት ዓለም ውስጥ መኖርህን አቁም ነው???

በክረምት ወቅትስ እሽ የጎርፍ ውኃ አለ፡፡ እሱም ቢሆን ዝናብ በዘነበ ጊዜ አንድ አፍታ ጎርፎ የሚያልፍ ነው፡፡ በጋ ላይ ግን ውኃው ከየት መጥቶ ሞልቶ ይፈስበታል ብለህ አስበህ ነው የምትጃጃለው??? በወንዞቹ ላይ በበጋ የሚፈሰው ውኃ እንደሆን ከየቤቱ፣ ከየድርጅቱ፣ ከየፋብሪካው የሚወጣው ፍሳሽ ቆሻሻ እንጅ የወንዝ ውኃ አይደለም፡፡ ይሄንንም ቆሻሻ ውኃ ሌላ መፋሰሻ ይዘጋጅና በዚህ በሚዘጋጀው መፋሰሻ እንዲሔድ ይደረጋል!” ነው ያሉት፡፡ ይሄ ከሆነ ደግሞ ወንዞቹ በበጋ ቆሻሻ ውኃም የሌላቸው ደረቅ ይሆናሉ ማለት ነው፡፡

መቸም ጅል ነህና የክረምቱን ውኃ ገድበን እንይዘዋለን!” ብለው ሊያጃጅሉህ ይሞክሩ ይሆናል፡፡ ይሄንን ቢሉህ አንደኛ የአዲስ አበባ አቀማመጥ ደፋታ ስለሆነ የጎርፉን ውኃ ገድበው ይዘው ወንዙ ላይ ሊያስተኙት እንደማይችሉ ዕወቅ፡፡ ሁለተኛ የአዲስ አበባ አቀማመጥ ደፋታ ባይሆንም ኖሮ በአነስተኛ ስፍራ ላይ ተገድቦ የሚያዝ ውኃ እንደ ኩሬ ውኃ ቶሎ ተበላሽቶ መጥፎ ሽታ የሚያመጣና ለጤና ጠንቅ ስለሚህን በዚህ መልኩ የክረምትን ውኃ ይዞ ለመዝናኛነት ማዋል የማይቻል መሆኑን ዕወቅ፡፡ ስለሆነም የሚሉት ነገር ማጭበርበሪያ ነው ሌላ ነገር የለውም!!!

ሰው እንዴት በራሱ ላይ ለሚደረግ የጥፋት ወንጀል ተግባር ከጠላቱ ጋር ይተባበራል??? በዚህ የኦነጎች የገቢ ማሰባሰቢያ ግብዣ ላይ ተገኝተህ ገንዘብ በመለገስ ለድብቅ የጥፋት ሥራቸው የምትተባበር ዜጋ ብትኖር በተለይ አማራ ጉራጌብትኖር ለገዛ እራስህ ጥፋት ከጠላትህ ጋር እንደተባበርክ ዕወቅ!!! በኋላ ላይ እንደ የእግር እሳት የሚያቃጥልህን ስሕተት ከመሥራት ተጠንቀቅ!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com