February 28, 2019

“የፌደራል መንግስት እጁን አስገብቶ ግድያውንና አፈናውን ማስቆም ካልቻለ የለየለት ጦርነትና የዘር ጭፍጨፋ ስለሚከተል በአስቸኳይ ገለልተኛ የፀጥታ አካል ተሰማርቶ ሕዝቡን እንዲታደገው ኮሚቴው ያሳስባል”

“በ19/06 2011 ዓም ብቻ 2 ወጣቶች ሲገደሉ፣ 5ቱ ቁስለኛ ሆነዋል። ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ደግሞ በትግራይ ልዩ ኃይል ታፍነው የት እንደደረሱ አይታወቅም። በአዲረመጥ 4 የኃይማኖት አባቶችም ለእስር ተዳርገዋል።”