March 1, 2019
ህወሃት በአማራ ላይ ጦርነት ያወጀች ይመስላል
ትናንት የሁለት የወልቃይት አማራ ወጣቶችን በጠራራ ፀሀይ የገደለችው ህወሃት ዛሬ ምሽት በሁመራ የሚኖሩ ትግሬዎችን ከዳንሻ ከተማ ስታስወስጣ እንዳመሸች ከስፍራው የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል።
እነዚህን በዴንሻ የሚኖሩ የነበሩ ሰፋሪ ትግሬዎችን በማስወጣት ከዳንሻ ብዙም በማይርቀውና የትግራይ ምልስ ወታደሮች ወደሰፈሩበት ካምፕ ካሰፈረች በኋላ በምትኩ ታጣቂዎችን ከሽሬ መስመር ወደ ዳንሻ ከተማ በሶስት FSR እንዳስገባች ለማወቅ ተችሏል።
ህወሃት በሌሊት ምን ለመፈፀም እንዳሰበች እርግጠኛ መሆን ባይቻልም በወልቃይትና በራያ በኩል ከፍተኛ ጦር ማስፈሯ ይታወቃል።
የአማራ ልዩሀይል ሀላፊ ብርጋዴር ተፈራ ማሞም ዛሬ ህወሃት ወታደር ማሰልጠንና ማስፈሯን ለኢሳት አረጋግጠዋል።
እናም ህወሃት ዛሬ ምሽት ወደ ዳንሻ ያስገባችው የታጠቀ ወታደር እንዲሁም ትግሬዎችን ከዳንሻ ማሰወጣቷ የራሷን ዜጎች ከለላ ከሰጠች በኋላ በሌሎች ንፁሃን ላይ ጥቃት ለመፈፀም የመዘጋጀቷ ምልክት ነው።
ይህንን በጥርጣሬ የሚመለከተው የአርማጭሆ ገበሬ ወደ ስፍራው ለማቅናት ቢሞክርም በመከላከያ እንደተመለሰ ለማወቅ ተችሏል።
በስፍራው በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ህወሃት የሰራችውን ስራ ቢያውቅም ለአካባቢው ንፁሃን ዜጎች ከለላ ይሰጣል ወይስ አይሰጥም?፣ የማዕከላዊ መንግስቱስ ህወሃትን ያስቆማታል ወይ? የሚሉት ጉዳዮች እስካሁን ግልፅ አይደሉም።
የትግራይ ክልል ወታደርና ደህንነት ሲያሰለጥን ገና ከጅምሩ መረጃው ያለው የአብይ መንግስት ይህንን ማስቆም አልቻለም።ይባስ ብሎ የትግራይ ክልል የአንድን ሉዓላዊ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ሲያግትና መሳሪያውንም ከክልሌ አላስወጣም ብሎ ሲያስቀር ርምጃ አልወሰደም።
የማዕከላዊ መንግስቱ መዳከም/እያወቀ ችላ ማለት ለህወሃት መልካም አጋጣሚ ሆኖለታል።
ይሁንና የሀገር መከላከያን ዘርፎ በታጠቀው መሳሪያ እና ባሰለጠነው ሰራዊት የሚመካው ህወሃት በአማራ ክልል በኩል ምን አፀፋ አለ? የሚለውን ያጠናው አይመስልም።
ህወሃት የሚጎሽመው ጦር ለትግራይ ህዝብ የበለጠ አደጋ ይዞ የሚመጣ ነው።የትግራይ ህዝብ ግን ሳያውቀው በየዋህነትም ይሁን በተዛባ መረጃ ከወንድሙ የአማራ ህዝብ ጋር እንዲዋጋ ህወሃት ሌት ተቀን እየሰራ ነው።
ይህ ለትግራይም ይሁን ለአማራ ህዝብ የማይጠቅም ጦርነት መሆኑን ተገንዝቦ የትግራይ ህዝብ ለፀብ አጫሪው ህወሃት እረፍ ቢለው ጥሩ ነው።እዚህ ላይ ቀና አንድም ሁለትም ትግሬዎች ካላችሁ ጦርነት ለማንም አለመጥቀሙን ብቻ ሳይሆን በተለይ በአማራ እና በትግሬ መካከል ጦርነት መከፈቱ አሳፋሪም ከማንም በላይ አክሳሪም መሆኑን ልትረዱት ይገባል።ትግሬና አማራ በህወሃትና መሰል ተንኮለኞች ህዝቡ እንዲለያይ እና እንዲጣላ ቢሰራበት እንኳን እጣፋንታው አንድ መሆኑን ማስረዳት ያለብን አይመስለንም።ኪሳራው ለጋራ ነው።የከፋው ደግሞ ለትግራይ ነው።ይህንን እናንተም ታውቁታላችሁ።
የዶ/ር አብይ መንግስትም በትግሬና አማራ ጦርነት አተርፈዋለው ያለውን የፖለቲካ ትርፍ ወደጎን በመተው የትግራይ መንግስትን የወራሪነት አባዜ እና የትንኮሳ ሱስ መከላከያውን ተጠቅሞ ቢያስቆመውና ከመከላከያ የተወሰደውን ትጥቅም ቢያስመልሰው መልካም ነው።ይህንን ማድረግ አለመቻል ጉዳቱ ለብዙ አካል ነው።544
