February 28, 2019

የወላይታ ዞን ተጠባባቂ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ የሀውልት መሰረት ድንጋዩን ሲያስቀምጡ እንደገለጹት ለትውልድ አርአያ ለሆኑ የብሔሩ መሪዎች ኃውልት ማቆም አስፈልጓል።

ከሁለቱ የቀድሞ ንጎሦች በተጨማሪ ለቀድሞ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ለአቶ ፍሬው አልታዬ ሀውልት ይቆምላቸዋል ነው ያሉት።

ኃውልቶቹ ከቱሪስት መዳረሻነት ባለፈ ታሪክን ለትውልድ ጠብቆ ለማቆየት እንደሚረዱ ተገልጿል።

ምሁራንን ያሳተፈ ኮሚቴ ተዋቅሮ በተካሄደ ጥናት መሰረት ለሶስቱ የቀድሞ መሪዎች ኃውልቶቹ እንዲቆሙ መወሰኑን ተናግረዋል።

ዲዛይናቸው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተውጣጡ ምሁራን መከናወኑን ገልጸው ኃውልቶቹን የማቆም ሥራ በቅርቡ እንደሚጀመር ተናግረዋል።

ካዎ ሞቶሎሚ 10ኛው የወላይታ ንጉሥ ሲሆኑ ከ1251 እስከ 1298 ዓ.ም ድረስ አካባቢውን ያስተዳደሩ ሲሆን ካዎ ጦና ጋጋ ከ1866 እስከ 1887 ዓ.ም አስተዳድረዋል።

ENA