March 1, 2019

ጃዋር ሞሃመድ ትናንት ዋልታ ጋር በነበረው ቆይታ አዲስ አበባን ላለመጥራት “ፊንፊኔ” እና “ሸገር” እያለ ሲጠራ ነበር። የጃዋር አይገርምም። “ሸገር” የአዲስ አበባ አማራጭ መጠሪያ ሆኖ ሲያገለግል ይታያል። ግን መደበኛ አጠረር አይደም። የሚገርመው የጃዋር እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አንድ መሆን ነው።

በተለይ በመንግስት ደረጃ የሚፃፍ፣ የሚነገር ሁሉ ሕጋዊና መደበኛ መሆን አለበት። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ፌስቡክ ገፅ ላይ የሚፃፈው የጠቅላይ ሚኒስትሩን አቋም የሚገልፅ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደግሞ መደበኛና ህጋዊ በሆነው አጠቃቀም ነው መጠቀም ያለበት። ፊንፊኔም፣ ሸገርም በሕጉ ሕጋዊ አጠራር አይደለም።

በእርግጥ በቅርቡ ዐቢይም “ፊንፊኔ” ሲል ተደምጧል። ይህ “የፊንፊኔ ኬኛ” ፖለቲካ ትዝብት ውስጥ ሲከታቸው አዲስ አበባን በኦሮሚያ ልዩ ጥቅም ስሟ ለመጥራት ባይደፍሩም፣ አዲስ አበባ የሚለው ስምም እያስጠላቸው ይመስላል። ጠ/ሚ ዐቢይም ለባለሀብቶች አንድ ራት በ5 ሚሊዮን ብር እሸጣለሁ ያሉበትን መድረክ የ”ሸገር” አድርገውታል። ግለሰቦች፣ ተቋማት (የግል)……ሌሎችም ኢ መደበኛውን ስም ሊጠቀሙ ይችላሉ። በጠቅላይ ሚኒስትር ደረጃ ሲሆን ግን ሕገወጥ ነው። ሕጋዊ አይደለም። ምን አልባት አዲስ አበባን “ፊንፊኔ” እስኪያስብሉ መሸጋገሪያ ስም ይሆናል!