March 2, 2019 t

በድሮው የአደዋ ድል አከባበር በዋናነት የኢትዮጵያን ባንዲራ የያዙ ፈረሰኞቹ ዋናው የበዓሉ ድምቀት ነበሩ፡፡ ዛሬ በሚኒሊክ አደባባይ ከሚኒሊክ በቀር ፈረሰኛ የማይታይበት በእርግጥም እንደድሮው በኢትዮጵያ ባንዲራ የተዋበ በዓል ተከብሯል፡፡ ይሄን ታሪካዊ ቀን አከባበር ሳይ በአለፉ 28 ዓመታት የዚህን ታሪክ መሠረት ደብዛ ለማጥፋት የተሰራው ሴራና ጥረት ታሰበኝ፡፡ ሐዘንም ተሰማኝ! አሁን አሁን ሁሉም ወደልቡ እየተመለሰና ወደነበረ የኢትዮጵያዊነት ማንነቱ እየከተተ ነው፡፡ ከኢትዮጵያዊ ማንነት ሙልጭ ብሎ እንዲወጣ በአለ በሌላ ጉልበት ሲሰራበት የነበረው የኦሮሞ ማህበረሰብ ግን አሁንም ገና ነው፡፡
የኦሮሞን ሕዝብ ከኢትዮጵያዊነት ለማራቅ የተሰሩትን ዋና ዋናዎቹ ሴራዎች ከአደዋው ጀምሬ እስኪ ጥቂት ልጠቁም፡፡
- አደዋ፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ተመዝግቦ እንደምናየው ከየትኛውም ማህበረሰብ በበለጠ በአደዋው ድል ትልቅ አስተዋፅዖ የነበራቸው ዛሬ ኦሮሞ ከተባለው ማህበረሰብ የወጡ አባቶች ናቸው፡፡ ይሄን የካዱ ኦሮሞ ነን የሚሉ ዘረኛና በጥላቻ የመረቀዙ የኦሮሞን ሕዝብ ከኢትዮጵያዊነት ለማራቅ የአደዋ አባቶቻችንን መስዋዕትነት አጣጣሉት፡፡ ዛሬ በኦሮሞ ሕዝብ እነ ገበየሁ ጎራ ባልቻ ሳፎ (ባልቻ አባነብሶ) ሳይሆኑ ጀግኖቹ መንደርተኞችና በዘረኝነትና ጥላቻ እየበከሉት የአስተሳሰብ ባሪያ ያደረጉት ናቸው፡፡ ዛሬ ለኦሮሞ ሕዝብ የአደዋን ድል ማክበር የውርደት ያህል ነው የሚሰማው፡፡ በየአመቱ በዓሉ በተከበረ ቁጥር በመርዘኛ ታሪክ ሲመረዝ ይውላል፡፡ የአደዋው ድል ታላላቅ ጀግኖቹን ያፈራው ጎበና የኦሮሞ ጠላት ነው፡፡ የአደዋው ድል መሪ ሚኒሊክ ሥም ዛሬ ኦሮሞን ያስደንብረዋል ያባንነዋል፡፡ በታሪክ ኦሮሞ ከፍተኛ ልዕልናና ትልቅ የመሪነት ድርሻ የነበረው በሚኒሊክ እንደነበር እውነት ቢሆንም ዛሬ ለዛሬው ኦሮሞ ያ ታሪክ ሲዖል ሆኖ ተስሎበታል፡፡ ለዛም ነው የሚኒሊክ ሥም ሲጠራ የሚደነግጠው፡፡ የዛሬውን አደዋ የሰሩ ጀግኖች ሚኒሊክና ከሚኒሊክ ጋር የነበሩት ጀግኖች አባቶች ስለሆኑ በጠላቶቹ ትርክት ለተመረዘው ኦሮሞ ይህ በዓል ያመዋል፡፡ በዓሉ በመጣ ቁጥር የድሉን ገጽታ ለማራከስ በየአመቱ ሰዎችን የሚያነጋግረው ኦኤም ኤን የተባለው ብዙዎን ኦሮሞ የጀዋር መሀመድ አምላኪ እስከሚመስል የዳረገው የፕሮፓጋንዳ ሚዲ በዚህ አመት ለየት ያለ አመለካከት ያለው ሰው ጋብዞ ተመለከትሁ፡፡ ግለሰቡ በታሪክ ያላችው ግንዛቤ አልፎም አጠቃላይ በኢትዮጵያዊነት የሚኮሩ ናቸው፡፡ ሆኖም ጠያቂ ጋዜጠኛ ሆና የቀረበቸውን ልጅ ሳይ እጅግ አዘንኩ፡፡ ተጠያቂው ስለኢትዮጵያዊነት ሊናገሩና ኦሮሞ እንዴት በኢትዮጵያዊነት ታሪክ ድርሻ እንደነበረው ሊያብራሩ ይሞክራሉ፡፡ ልጅቱ ስትሞላ ያደገችበትን ትርክት እንዲነግሯት መከራ ታያለች፡፡ ሚኒሊክን ከአደዋ ድል ለመለያየት አለኝ የምትለውንና በአደዋ ላይ አሉታዊ ተጽኖ ይኖራቸዋል ብላ ያሰባቻቸውን ለሚዲያው ለማበርከት የበኩሏን ሞከረች፡፡ ተጠያቂው ቀዝቀዝ ብለውም ቢሆን እውነቱን ሊክዱላት ፍቃደኛ አልነበሩም፡፡ ይልቁንም ራሳቸውንም ሆነ መላውን ኢትዮጵያ በኦሮሞ ዘንድ እንዲጠላ የተደረገውን የሐበሻነት ስያሜ እየተጠቀሙ ማብራራት ቀጠሉ፡፡ ለዛሬው የኦሮሞ ዘረኛ ፖለቲካ ሰለባ ለሆኑት ኦሮሞዎች ሐበሻ ማለት ሌላው የሚያስበረግጋቸው ድምጽ ነው፡፡ ከራስህ ጋር ስትጣላ ሁሉም የሚያስፈራ ይሆንብሀል፡፡
- ኢትዮጵያ፡ ብዙ በዘረኞቹና ሴረኞቹ ኦሮሞ ነን የሚሉና አጋሮቻቸው መርዘኛ ትርክት ሰለባ የሆነው ኦሮሞ እንዲጠላው የተደረገው ሌላው ራሷ የሚኖርባትን ኢትዮጵያን ነው፡፡ ይሄም ከላይ ከተነሳው የአደዋ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ዛሬ ላለችው ኢትዮጵያ ጉልህ ድርሻ የነበራቸው ሚኒሊክና ጎበና አልፎም ሌሎች ብዙ አባቶች በኦሮሞ ዘንድ ማስፈራሪያ እስከሚሆኑ ድረስ እንዲጠሉ ትልቅ የሐሰት ትርክት በመስራት በብዙ ሕዝብ ስነልቦና ጥላቻ እንዲሰማው ተደርጓል፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስም ኦሮሞ ሆኖ ኢትዮጵያዊነቱን እንደልቡ በኩራት መናገር የሚችለው ጥቂት ነበር፡፡ ቆይቶ በቅርብ በመጣው ለውጥ ይልቁንም የለማ የኢትዮጵያዊነትን ዘመቻ ተከትሎ ብዙዎች በኢትዮጵያዊነት ስሜት ተመልሰው ቢገቡም አሁንም የ27ዓመቱ ሐሰተኛ ትርክት ሙሉ በሙሉ የስነልቦና ነጻነት ሊሰጣቸው አልቻለም፡፡ እስካሁንም ግን ኢትዮጵያዊ ነን ለማለት የልቻሉ ብዙዎች ናቸው፡፡ ግን ቀደም ባለው ጊዜ ብዙ ኦሮሞ ዜግነቱን ሲጠየቅ ኦሮሚያ እንደሚለው ዘመን አደለም፡፡ እንግዲህ ኦሮሞን ከገዛ አገሩ አስወጥቶ ኦሮሚያ በሚባል የቅዠት ሀገር ስደተኛ ያደረገው በፕሮፓጋንዳ የተፈጠረበት ስነልቦናው እንጂ በአካል ተሰዶ አልነበረም፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ኦሮሞ ምንም ድርሻ የለውም ብለው ከኢትዮጵያዊነት የለዩት ሴረኞቹ ዛሬም ይነግዱበታል፡፡ አሁንም ይቀራል፡፡ ዛሬ የኢትዮጵያዊነት አልፎም የአፍሪካም ልዩ ምልክት የሆነውን የኢትዮጵያን ባንዲራ ይዞ መገኘት በሀሰት ትርክት ስነልቦናቸው ለተጎዳና የሴረኞቹ የአስተሳሰብ ባሪያ ለሆኑት ብዙዎች ከምንም በላይ ውርደት ነው፡፡ በሌሎም ኢትዮጵያውያን ላይ በኦሮሞ የተደረገው ከኢትዮጵያዊነት ማግለል ሴራ ተሰርቷለ፡፡ እንደ ኦሮሞ ግን አልነበረም፡፡ ዛሬ ሌሎች በፍጥነት ወደ ኢትዮጵያዊነታቸውን እያጠነከሩ ነው፡፡ አፋር ከድሮው ጀምሮ እንኳን ሰው ግመሌቼም የኢትዮጵያን ባንዲራ ያውቋታል ባይ ነው፡፡ ለሱማሌም የኢትዮጵያ ባንዲራ ምልክቱ ነው የአሁን የሱማሌ አካሄድ ግን በታሪክ የተፈጠረውን የሴረኞችን ትርክት በእውነተኛው ትርክት መተካት በይበልጥም ደግሞ ከሱማሌ ማህበረሰብ ሆነው ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ጉልህ ድርሻ የነበራቸውን ግለሰቦች ታሪክ ወደፊት በማምጣት የኢትዮጵያዊ የአገር ባለቤትነት ድርሻን ማጉላት ነው፡፡ መልካም የሚባል ነው፡፡
- የፊደል መቀየር፡ የኦሮሞ ከግዕዝ ወደ ላቲን ፊደል መቀየር ከዚህ በፊት ብዙ ምሁራን ተከራክረውበታል፡፡ እውነታው ግን የግዕዝ ፊደል ለኦሮምኛ ቋንቋ ምቹ ያለመሆን ሳይሆን ሴረኞቹ ከኢትዮጵያና እነሱ ሐበሻ ከሚሉት ሕዝብ ለማራቅ ሆን ብለው ያደረጉት ነበር፡፡ ከዚህ ውጭ የግዕዝ ፊደል አዳዲሰ ምልክቶችም ለመፍጠር ሆነ ብዙ ድምፆችን ለማካትት ከየትኛውም ፊደል በተለየ የተሳካለት ነበር፡፡ የኦሮሞን ቃላት የሚወክሉ ፊደላት ቢጎድሉት እንኳን አዲስ ምልክትን መጨመር ቀላል ነበር፡፡ ለምሳሌ መቀሌ የመጻፍበት ቀ በግዕዝ ፊደል ውስጥ አልነበረም፡፡ የላቲን ፊደል ለብዙ ቋንቋዎች መገልገያ ቢሆንም እንደወረደ አደለም እንደየቋንቋው የሚጨመሩ ሌሎች ምልክቶችና አልፎም ራሳቸውን የቻሉ ፊደሎች አሉ፡፡ ግዕዝ እንደ አማርኛ አልነበረም፡፡ እጅግ የበለጸገ የቃላት ብዛት ነበረው፡፡ ፊደላቶቹም ለዛ የተዘጋጁ በመሆናቸው ብዙ ድምጾችን እንዲያካትቱ ነው፡፡ ዛሬ ላይ በአማርኛ አንድ አይነት ድምጽ የሚመስሉት የእነ ሀ አ፣ ሰ ዘሮች የተለያየ ድምጽ ነበራቻ፡፡ ለምሳሌ “ሰረቀ” ና “ሠረቀ” እዩ ሲነበቡም ትርጉማቸውም ፍጹም የተለያየ ነው፡፡ ዐ እና አ ድምጻቸው ሳይቀር በግዕዝ የተለያየ ነው፡፡ በአማርኛ ይሄ የለም፡፡ ከዚህ በተረፈ አዳዲስ ፊደላት መጨመር በግዕዝ ቀላል ነው፡፡ አንዴ የመሰረታዊ ድምጹን ፊደል ከተቀረጸ አባዥ ድምጾችን በቀላሉ ይ ቀረጻሉ፡፡ ለምሳሌ ፐ፣ ቨ የመሳሰሉ ፊደላትንና ዘሮቻቸውን የሚጠቀሙ ቃላት በግዕዝ የሉም እነዚህ ፊደላት የገቡት አንዳንድ የውጭ ቃላትን በግዕዝ ፊደል ለመጻፍ ነው፡፡ በኦሮምኛ ዛሬ dh በሚል ፊደላት የተተካው ድምጽ በግዕዝ ፊደል ተቀርጾለት ነበር ግን በምን ምክነያት እንደሆነ ባይገባኝም እስካሁንም የግዕዝ ፊደል ሶፍትዌር አዘጋጆች ይሄን ፊደል አላካተቱትም፡፡ አስናለሁ፡፡ ምን አልባት አታካቱ ተብለው ይሆን? በዚህ መልኩ ግን ግዕዝን ለኦሮምኛም ሆነ ሌሎች ቋንቋዎች መጠቀም ቀላሉና የራስ በሆነው መመካት ጭምር ነበር፡፡ በዋናነት በኦሮሞ የተጀመረው የፊደል መቀየር ሌሎችም የሄንኑ እንዲከተሉ ተደርጓል፡፡ወደፊት ግን ግዕዝ በአፍሪካ ደረጃ ፊደላችን ይሁን የሚል አስተሳሰብ ሊነሳ እንደሚችል አስባለሁ፡፡ ያኔ ኦሮሞ የግዕዝ ፊደልን ለመጠቀም አንዳዲስ አንግዳ ሊሆን ነው፡፡ ይሄ አይሆንም ብላችሁ ካሰባችሁ ተሳስታችኋል ሊሆን የሚችልባቸው ብዙ ምክነያቶች እየታዩ ስለሆነ፡፡ ዛሬ ላይመስል ይችላል ግን ቆይተን እናየዋለን፡፡
- ሐበሻዊነት፡- ሌላው ኦሮሞ እንዲጠየፈው የሆነው ከላይ የጠቆምኩት ሐበሻዊነት ነው፡፡ ሐበሻዊነት በእርግጥም የዘር መለያ ነው፡፡ ሐበሻ የሚባለው ማሕበረሰብ ከሌሎች ዓለም ላይ ከአሉት ማሕበረሰብ የሚለይበት በሕብረ ቀለምነቱ ነው፡፡ ሐበሽ ማለት ድብልቅ ሕዝብ ነውና፡፡ ይሄን ታላቁ መጻፍም የኢትዮጵያና የፉጥ (ሊቢያ) ድብልቅ ሕዝብ ሲል ይጠቅሰዋል፡፡ ለማንኛውም ሐበሻ የሚባለው ሕዝብ ዘሬ በሳይንስ ግልጽ ሆኖ ያለ የተለየ የዘር ግንድ ያለው ለሳይንስም ለየት ያለ ግብዓት የሆነ ነው፡፡ ሐበሻ ከሶስት ዋና ዋና የዘር ግንዶች የሚመጣ ነው፡፡ የጥንታውያን ሌቫንት (ለመጀመሪያ ጊዜ እርሻን የፈለሰፉ የሶሪያና አካባቢው)፣ የአሪ (አሪ ማህበረሰብ ውስጥ ዛሬም የዚህ ዘር ግንድ ነጹሁ አለ)፣ ከማሳይ ከሚባለው ኬኒያ ውስጥ ከሚኖረው ሕዝብ ጋር በሰፊው የምንጋራው አንድ ሌላ ኢትዮጵያና አካባቢው ያለ የዘር ግንድ ነው፡፡ እነዚህ ሶስት የዘር ግንዶች ከ99 በመቶ በላይ የሆነውን የዘር ድርሻ በመያዝ የአብዛናው ኢትዮጵያ፣ ሱማሌ፣ ጂቡቲ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን የመሳሰሉ በአካልም የሚመሳሰሉት ሕዝቦችን የሚወከሉት ዘሮች ናቸው፡፡ እንግዲህ ሐበሻ የሚባለው ህዝብ ይሄ ነው፡፡ የሚገርመው ይሄ ሕዝብ እነዚህ ሶስት የዘር ግንዶች በጋራ ሲጋራ ከሌሎች አፍሪካውያን ጋር ያለው ዘር ትስስር ሳይቀር የተለየ ነው፡፡ ሶሶስቱም የዘር ግንዶች በሌሎች አፍሪካውያን ዘር ውስጥ እምብዛም አይታዩም፡፡ ከላይ እንደጠቆምኩት ማሳይ በብዛት አንደኛውን ኢትዮጵያዊ መሠረት ያለውን የዘር ግንደና(ከ70 በመቶ በላይ ለማሳይ ይሄ የዘር ግንደ ነው) የሌቫንቱን(በጥቂቱ) ይጋራናል፡፡ ሆኖም ግን ብዙ ኢትዮጵያውያን ዘልቀው እስከ ደቡብ አፍሪካ እንደሄዱ የሚያሳይ ይሄንኑ ከላይ የጠቀስኳቸውን ዘር ግነዶች በደማቸው የየዙ ይታያል፡፡ ለምሳሌ ታንዛንያ ውስጥ በብዛት አሉ፡፡ ወደፊት ማንነትን ፍለጋ መነሳቱ አይቀሬ ነው፡፡ ሐበሻ ዘር ነው፡፡ ነገድ ነው፡፡ በኦሮሞ አማራ ትግሬ ሱማሌ አፋር መካከል አንድም ልዩነት የለም፡፡ አማራ ሐበሻ ሆኖ ኦሮሞ ሐበሻ የማይሆንበት ተፈጥሮአው እውነት የለም፡፡ ሐበሻነት ተፈጥሮዋዊ እውነት እንጂ ባሕልም ቋንቋም አደለም፡፡ ይሄን ጉዳይ ደጋግሜ አንስቼዋለሁ፡፡ የሚገባው ቢኖር እውነቱ ይሄ ነው፡፡ ለፖለቲካ መጠቀሚያ ያመቸናል ያሉ ነበሩ ኦሮሞን ከሐበሻዊነት አውጥተው አሁንም በገዛ የደም ማንነቱ ሳይቀር ባይተዋር ያረጉትና ሐበሻ የሚለውን ቃል ራሱ እንዲጸየፈው የሚያደርግን ስነልቦና የፈጠሩበት፡፡
- የኢትዮጵያ ባንዲራ፡ ከላይ አንስቼዋለሁ ግን ጉዳዩ በራሱ ትልቅ የስነልቦና ችግር ስለሆነ ነው፡፡ ዛሬ ለብዙ ኦሮሞ ድሮ አባቶቹ የነጻነት አርማ አድርገው ሲዋደቁላት ለነበረች አገር ምልክት አድርገው ያቆዩትን ባንዲራ ማስጣል ትልቁ የሴረኞቹ ድል ነበር፡፡ አሁን ለብዙ ኦሮሞ የኢትዮጵያ ባንዲራን ሲያይ ይነዝረዋል፡፡ አሳዛኝ ነው፡፡ በዚህም ሌሎች ኢትዮጵያውያን ሁሉ ከሚጋሩት እውነት ወጥቶ በራሱ ጊዜ የሥነልቦና ቀውስ ውስጥ ገብቶ እናየዋለን፡፡ አደዋ በሉት ሌላ ሴረኞቹ አሁን የፈጠሩበትን የስነልቦና ቀውስ እስከሚያመጡበት ጊዜ ድረስ ከሌሎች በተለየ የኢትዮጵያ ባንዲራ ለኦሮሞ ጌጡ ነበር፡፡ በቅርብ አብይ ተመርጦ አምቦ በሄደ ጊዜ ሊያውም ባለኮከቡን አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ባንዲራወን ይዘው የወጡ ፈረሰኞች በመታየታቸው በኦሮሞ የዘረኝነትና ጥላቻ አራማጆች ዘንድ ምን ያህል ውግዘት እንዳስከተለና ፈረሰኞቹንም ለማሸማቀቅ ምን ያህል ፕሮፓጋንዳ እንደተሰራ አይተናል፡፡ ዛሬ ኦሮሞ ግራ ገብቶታል፡፡ በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምነው ራሱ ኦሮሞ ከሆነ የኢትዮጵያን ባንዲራ መያዝ ቢፈልግ እነኳን የሚደርስበትን ውግዘትና የሥነ ልቦና ጫና በመፍራት አይዝም፣ የኦነግን እንዳይዝ በብዙዎች ኦነግ የወሮበላ ቡድን እንደሆነ ይታወቃል፣ የኦፒዲኦን አንዳይዝ ኦነጋውያን ይነሱበታል ብቻ ምን አለፋችሁ ይሄ አንዱና ትልቁ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ የስነልቦና ቀውስ የፈጠረ ነው፡፡
እንግዲህ ከእውነትና ከማንነት ጋር ተጣልቶ ነጻና ሠላም ሆኖ መኖር ከየት ይመጣል? ዛሬ ላይ ብዙ ኦሮሞ ከኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ጋር የተያያዙ ታሪካዊና ተፈጥቶአዊ እውነቶችን እንዲክድና ከማንነቱ ውጭ በሆነ የስነልቦና አስተሳሰብ ስለሚኖር በኢትዮጵያውያን ምድር የሚሆነውን ሁሉ እንደልቡ በባለቤትነት ለመጋራት አልቻለም፡፡ በሚኒሊክ አገር እየኖረ ሚኒሊክ የሚለው ቃል በተጠራ ቁጥር ስቅጥጥ እያለው ይኖራል፡፡ በኢትዮጵያ እየኖረ የኢትዮጵያዊነት መገለጫ የሆኑ ባህልና አስተሳሰቦች አንዲሁም የኢትዮጵያዊነት ምልከቱ ባንዲራው ሳይቀር የሚያስበረግገው ኦሮሞ ቀላል አደለም፡፡ ሐበሻ ነኝ ማለት ለብዙ ኦሮሞ ያሳፍረዋል ብቻም ሳይሆን ሐበሻ በለው የነገሩትን ሌሎችንም እጅግ በካፋ ጥላቻና ዘረኝነት ነው የሚያየው፡፡ አሁንም ከዚህ የስነልቦና ቀውስ ለመመለስ ከመሞክር ይልቅ ሌላ ተጨማሪ ከማንነቱ የሚያወጣውን ትርክት አቀንቃኝ እየሆነ እንዲቀጥል በአስተሳሰብ ባርነት ውስጥ ከተው የሚነግዱበት በአለ በሌላ ጉልበታቸው እየሰሩበት ነው፡፡ እንግዲሀ በዋናነት ከራሱ በወጡ ኦሮሞ ነን በሚል ኦሮሞን የአስተሳሰብ ባሪያቸው ያደረጉትን እየተከተለ ብዙ የራሱ የሆኑትን እውነተኛ ማንነኖችና የባለቤትነት ድርሻ አልፎም ከዘር ማንነቱ እራሱን በስነልቦና በማግለል በባይተዋርነት እንዲኖር ብዙ ኦሮሞ ግድ ሆኖበታል፡፡ የራሱን አደዋን፣ የራሱን ጀግኖች አባቶች ገድል፣ አባቶቹ ሰርተውና ጠብቀው ያኖሯትን አገር ታሪክ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በኩራትና በደስታ እየዘከረው ለብዙ ኦሮሞ ግን የሚያሸማቅቀው ሆኗል፡፡ የሚገርም ነው! ይሄን ማስተዋል እንዴት ተሳነን? አሁንም እላለሁ በኢትዮጵያዊነታችሁና አባቶቻችሁ በሰሩት ታሪካዊ ገድል የምታምኑና የምትኮሩ ከዚሁ ማህበረሰብ የወጣችሁ ሁሉ ይሄን ታሪክ ወደ እውነቱ በመቀየርና ኦሮሞን ሁሉ ወደ ክብሩ እንድትመልሱት መሥራትን እጠይቃችኋለሁ፡፡ ጉዳዩ የፍትህም የዲሞክራሲም ሳይሆን እጅግ ሕዝብን የሚያዋርድና በስነልቦና ከሌሎች ባይተዋር የራሳቸው ንግድ መጠቀሚያ ያደረጉት የሴረኞች ሴራ ነው፡፡
ከላይ እንደጠቆምኩት ዛሬ ለብዙ ኦሮሞ ጀግና የለውም! ጀግና አድርጎ እንዲያምን የተደረግው ዛሬም እየነገዱበት ያሉትን ነው! ዛሬ ለብዙ ኦሮሞ ምሁር የለውም ምሁር ብሎ እንዲቀበል የተደረገው ራሳቸውን ትልቅ በማድረግ የስነልቦናና አስተሳሰብ ዘመቻ የከፈቱበትን ተራ ወሮበሎችን ነው፡፡ ዛሬም ከሌሎች በተለየ በጭቆናና በበታችነት ስነልቦና እያኖሩት ነጻ አውጭህ ነን በሚል እየነገዱበት ነው፡፡ ቢያንስ ለ50 ዓመት ተነገደበት፡፡ ይሄን ማስተዋል ሳንችል በዚሁ ከቀጠለ ዛሬ በቁጥር በዝቶ የምናየው ሕዝብ በቁጥርም እንደሚወርድ አትጠራጠሩ፡፡ ኢትዮጵያዊ መሠረት ላይ ከአልታነጸ በኢትዮጵያ ምድር እየኖሩ ከስነልቦና የበታችነት ማምለጥ አይቻልም፡፡ ሚኒሊክን እየፈሩ በሚኒሊክ አገር ሠላም አግኝቶ መኖር አይቻልም፡፡ ሚኒሊክ ከሸዋ እስከቦና ዛሬም ድረስ የሚታዩ የኦሮሞ እሴቶች እንዲቀሩ ያደረጉ ጭርሱንም የኦሮሞ መሪ በሚያስብል መልኩ የመሩ ታላቅ ንጉስ ናቸው፡፡ ሚኒሊክ ባይኖሩ ዛሬ ገዳ እያለ የሚያቅራራ ይቅርና ገዳ የሚለውን ሥም ራሱ የሚያውቅ ባልኖረ ነበር፡፡ ሚኒሊክ በኬኒያ ተቆርጠው እንደቀሩ ኦሮሞዎች ሥርዓታቸውን ሁሉ አጥፍቶ የነጭ ታሪክን የፈጠሩለት እንጊሊዞች ሳይሆን ቦረናን በገዳ ሥርዓት እንዲተዳደር በቀጥታ ገዳን የቦረና አስተዳደራዊ መንግስታዊ መዋቅር በማድረጋቸው ነው ዛሬ ድረስ የቆየው፡፡ የኦሮሞ የተባሉ ዛሬም ድረስ የምናያቸው ባህሎች የገዳውና ሌሎች ባህላዊ እሴቶችን በመጠበቅ የቆዩት የሚኒሊክ ዋና የነበሩት ሸዋዎች እንጂ ወለጋ፣ አርሲ፣ ባሌ፣ ሐርር፣ ጂማ አደለም፡፡
ይሄን የምለው ዛሬ በሚኒሊክ ላይ ከሚነሱ የኦሮሞን ባህልና እምነት አጠፋ የሚሉ የሐሰት ትርክቶች አንጻር እንጂ እንደእውነቱ ሰው እንደሚኖርበት ማህበረሰብና ሌሎች እውነታዎች ባህሉም ሊቀየር ይችላል፡፡ በአርሲ፣ ባሌ፣ ጂማ፣ ሐረር አብዛኛው የአሮሞ ማሕበረሰብ የእስልምና ተከታይ በመሆኑ የእስልምናውን እምነት ባሕሎችናና አኗኗሮችን ስለሚከተል ዛሬ ጠፉብን የሚባለው ግን ያለቦታው ሚኒሊክ የሚጠሉበት ባህሎች በእነዚህ ቦታዎች የሉም፡፡ ለዚህ ምንሊክ አደሉም ምክነያቱ፡፡ ለውጥ ደግሞ የሕዝብ ሂደት ነው፡፡ ሚኒሊክን ለመክሰስ የሌለ ታሪክ ሲፈጠር ማስተዋል አእንኳን የለም፡፡ ሚኒሊክ የማንንም ሀይማኖት ባሕል አንድም ቦታ አልቀየሩም፡፡ ሰሞኑን ጀነራል ኃይሉ ጎንፋ የተናገሩት አሳፋሪ ንግግርን አስታውሱ፡፡ እንደ ኃይሉ ጎንፋ ዛሬ ኃይሉ የመባላቸው ምክነያት ምኒሊክ ናቸው፡፡ በዚህ ደግሞ ሚኒሊክ እጅግ ማንነትን የሚያጠፋ ሥራ እንደሰሩ ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ለመሆኑ እኝህ ሰው የእስልምና እምነት ተከታይ ከሆኑ ኦሮሞ ማህበረሰብ ቢወለዱ ሥማቸው የኦሮሞ ይሆን ነበር ወይ ተብሎ ቢታሰብ ያለው እድል 20 በመቶም አይሆንም፡፡ በእስልምና እምነታቸውን በሚገልጽ ሁኔታ ሥማቸው ከመገርሳነት ወደ አበዱልቃዲሪነት የቀየሩም ምክናያቱ ሚኒሊክ ይሆኑ፡፡ ልብ በሉ ሕዝብ እንሚያምነው እምነት፣ በአጎራባችና አብሮ እንደሚኖረው ሌላ ሕዝብ ባሕል በሂደት ብዙ የነበሩትን ባህል በአዳዲስ ከሌሎች በሚወርሳቸው ባሕል ሊቀይር ይችላል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ የመነግስት መዋቅር ደርሻ ሊኖረው ይችላል፡፡ የሚኒሊክ መንግስት ግን በአስደናቂ ሁኔታ ከዚህ አይነት ሕዝብን ከነበረበት ባህልና እምነት የመቀየር ደርጊት ፍጹም የጸዳ ነበር፡፡ ኢትዮጵያንም ዘሬ በምናየው ሕብረ ብሔራዊ ባህልና እምነት ያገኘናት የሚኒሊክ አገር በመሆኗ ነው፡፡ ይሄ የሚኒሊክ ልዩ ታሪካዊ አሰራር ነው ዘሬ ተገልብጦ እየተነገረው በሥነልቦና ራሱን የሴረኞች ባሪያ ያደረገ ትውልድ የተፈጠረው፡፡ ሚኒሊክ ብቻም አደሉም ለአልጋ ወራሽነት የመረጡት ኢያሱንም አሰድገው ዙፋናቸውን ያስረከቡት በዚህ ፍልስፍና አሳድገው ነበር፡፡ ይሄ ፍልስፍና ከዛም በፊት በነበሩ፣ ከዛም በኋላ በመጡ አልተሞከረም፡፡ ኃይለስላሴ እንደዛ አልነበሩም፣ ደርግም እኳን እንደዛ አልነበረም፡፡የወያ ወሮበላ ቡድንና ኦነጋውያን ሚኒሊክን ኢላማ ያደረጉበት ምክነያትም የሚኒሊክ ታሪክ እውነታዎች ፍጹም እነሱ ላሰቡት ሴራ አደገኛ በመሆኑ ነበር፡፡ እውነቶች በተገለጡ ቁጥ ሁሉንም ሊጠይቅ የሚችል ትውልድ እንደሚመጣ አስቡ፡፡ ያኔ በውሸት ትርክትና ስነልቦና የተገነባ ማህበረሰብ አባል መሆንን የሚፈልግ የለም፡፡ ቁጭ ብለው የሰቀሉት ቆመው ማውረድ እንደሚያዳግት አትጠራጠሩ፡፡
ቅዱስ እግዚአብሔር አጥንጣቸውንና ደማቸውን አፍሰው አገራችንን ጠብቀው ያስርከቡንን የጀግኖች አባቶቻችንን ወኔና መንፈስ ያድለን!
ለዕል አምላክ እግኢአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይባርክ! አሜን!
