March 3, 2019
Source: https://mereja.com/amharic/v2/97261

ስለ ለገጣፎ እንጽፋለን ….. በአቶ አብዱረህማን
(የቀድሞው የፓርላማ አባል)
በፖለቲካ ጡንቻ የታገዘው የለገጣፎ ቤት ፈረሳ አሁንም ሙሉ ለሙሉ አልቆመም፡፡ በሜዲያ ያልቀረቡ ብዙ አሳዛኝ ሁኔታዎችን እያየን/እየሰማን ነው፡፡ በአረብ ሀገር በበርሃ ተጠብሳ ባፈራችው ሳንቲም የሰራቺው ቤት በደቂቃዎች ውስጥ እንዳልነበር የሆነባት አንዲት ከርታታ ወጣት ራሷን ማጥፋቷን ስሰማ ወፈጠሬን ነው ያስጠላኝ፡፡
እነዚህ ቤታቸው የፈረሰባቸው ሰዎች ለኦሮሚያ መንግሥትና ለከንቲባዋ እንደ ስደተኛ የሚታዩ “መጤዎች” እንጂ ኢትዮጵያዊ ዜጋ መሆናቸው አልታያቸውም፡፡ ከስደተኛ ካምፕ ነዋሪዎች ጋር እያነጻጸሩ መግለጫ እስከ መስጠት የደረሱት ለዚሁ ነው፡፡
የሚገርመው ነገር ቤታቸው ከፈረሰባቸው ዜጎች ይልቅ አካባቢውን የማታውቀውና የአካባቢውን ማህበረሰብ ስነ-ልቦና ያልተገነዘበቺው “መጤ” ራሷ ከንቲባዋ ናት፡፡
ሁሉም አካባቢ ራሱን በራሱ እያስተዳደረ፣ በለገጣፎ ከንቲባ መሆን የሚችል ሰው የሌለ ይመስል ስለከተማ ማስተዳደር ምንም ግንዛቤ የሌላቸው ሰዎች ሁልጊዜ ከሌላ አካባቢ እየመታ የሚጫንብን እስከመቼ ነው? ወ/ሮ ሐቢባ የለገጣፎ ተወላጅ ብትሆን ኖሮ በህዝቧ ላይ ያን ያህል አትጨክንም ነበር፡፡ ሁሉንም ነገር በምክክር ትሰራ ነበር፡፡
በኢትዮጵያ ቤት ማፍረስ የሚገርም ነገር አይደለም፡፡ የህይወታችን አካል ከሆነ 27 ዓመታት ተቆጠሩ፡፡ እናም በለገጣፎ ቤት መፍረሱ አላስገረመኝም፡፡ የገረመኝ ነገር ማክሰኞ የካቲት 19 ቀን 2011 የከተማው ከንቲባ በአራት ፖሊስ ታጅባ ወደ ፈረሰው መንደር መጣች፡፡ እኔም በአቅራቢያው ነበርኩ፡፡ ምን ልታደርግ ነው ብለን ስንጠብቅ በአቅራቢያው ወደ ነበረው ቤተክርስቲያን ገባች፡፡ እዚያ ተጠልለው ለነበሩ ዜጎች አንዳች ማበረታቻ ልታደርግ ነው ብለን ስንጠብቅ “እነዚህ ሰዎች እዚህ መጠለላቸው የከተማችንን ገጽታ እያበላሸ ስለሆነ ከአሁኗ ሰዓት ጀምሮ አንድ
