March 3, 2019

Source: https://mereja.com/amharic/v2/97263

ኢትዮጵያን የሚያስጠቃት ወዶ ገብ ነው! (ጌታቸው ሽፈራው)
በተለያየ ጊዜ ጠላትና ገዥዎችን ተንበርክኮ የተቀበለ ወዶ ገብ ይኖራል። ዛሬ ዘመኑ ብዙ ያስተምራል። ስለ እኩልነት ያስተምራል፣ ስለ ፍትሕ ያስተምራል፣ ፖለቲካ በየቦታው ይተነተናል። ከቀደመው አርበኛ ትውልድ በላይ የዚህ ዘመን ትውልድ አርበኛ ለመሆን እድል ነበረው። ጠላትና ወዳጁን ጠንቅቆ የሚያውቅበት መረጃ በእጁ ላይ ነው። ሆኖም ከድሮው አንፃር የዚህ ዘመን ትውልድ ወዶ ገብነት ያጠቃዋል። በዚህ ዘመን አርበኛ ነኝ የሚል ወዶ ገብ በዝቷል። ኢትዮጵያን የሚያስጠቃትም ይህ ተቃዋሚ ነኝ፣ አርበኛ ነኝ የሚል ወዶ ገብ ነው!
የድሮዎቹ አንድ ነገር ሲከሰት “ቆይ በደንብ ይለይለት” ይላሉ። “ለውጥ መጣ” ቢባሉ “ሽልም ከሆነ ይገፋል፣ ቦርጭም ከሆነ ይጠፋል” ብለው ይጠብቃሉ። “ለውጥ መጣ” ሲባል አይንገበገቡም!
ወዶ ገብነትን በዚህ ዘመን በስፋት እያየነው ነው!
~ታጣቂ ቡድን ነኝ ያለው ሳይቀር ለታጋዮቹ ጥቅም ሳይደራደር ተልፈስፍሶ ገዥዎቹ እግር ስር ወደቀ! አፋሽ አጎንባሽ ሆኖ አረፈው!
~የነፃነት ታጋይ ነኝ ባዩ ሁሉ የገዥዎች የድጋፍ ሰልፍ አስተባባሪ ሆነ። ኢህአዴግ መሆናቸውን ረስቶ ፎቷቸውን አመለከው፣ አሳትሞ በክብር ሰቀለው፣ ቲሸርት ላይ አሰርቶ በኩራት ለበሰው። ወዶ ፈቅዶ! ሳይጠየቅ!
~የወዶ ገብነት ትልቁ በሽታ “ከአፈርኩ አይመልሰኝ” ባህሪው ነው። ያደነቀው ሲሳሳት “ተሳሳተ” ቢል ስህተቱ የእሱም መሆኑን ያውቃል። ገዥነቱን አድልቦለታልና! በመሆኑም ወዶ ገብ የገዥን ህፀፅ ማስተባበል ላይ ይጠመዳል። በሕዝብ ቁስል ጨው ይጨምራል። ተቃውመው የሚናገሩትን ከገዥዎች ጋር ሆኖ ያስጠቃል፣ ያጠቃል። የገዥዎች መንገድ ብቻ እንዲቃና፣ ድምፃቸው እንዲሰማ በማድረግ ሕዝብን ያስጠቃል! ወዶ ገብ ከአፈርኩ አይመልሰኝ ብሎ