March 3, 2019


ዐቢይ አሕመድ በውጥረት የሚሰራ መሪ ነው::ስራውን ለማሰናከል ህውሀት ሌሊት ተቀን ይሰራል:: ፅንፈኛ ኦሮሞዎች የእኛ ነው ብለው አልተቀበሉትም:: የዐቢይ ኢትዮጵያዊነት ይጎረብጣቸዋል::ህውሀት በጥቅም ሰንሰለት የዘረጋው ኔትዎርክ ጥቅማቸው ስለሚቀርባቸው ሆን ብለው ዐቢይ ግዝገዛ ላይ ናቸው::የላጋጣፎ አስቀያሚ ሂደትን የወለደው የ27 አመታት የዘረፋ ብልሹ አስተዳደር ውጤት ነው::የወደፊት የፖለቲካ የስልጣን እድል የጨለመባቸው ዐቢይን ለማዳከም ጋዜጠኝነትን ሽፋን አድርገው ሰፊ ዘመቻ ይዘዋል:: ዐቢይ ብዙ ደጋፊዎች አሉት::ሆኖም ደጋፊዎቹ ልፍስፍሶች ናቸው::

ድጋፋቸውን ከማሳየት ይልቅ ፕሮፌሰር መስፍን እንዳሉት ሀበሻ እድፍጦ ማየት ይችላል::ጥቂቶች ፕሮፓጋንዳውን ተቆጣጥረው ህዝብን ለማጋጨት ደፋ ቀና ይላሉ:: ሀገሩን የሚወድ ዝም የሚልበት ወቅት አይደለም:: ዐቢይ የእያንዳንዳችን ምኞትና ተስፋ አሰባስቦ በቅንነት የሚመራ ጠቅላይ ሚኒስትር ነው::ለብቻው ምንም የሚያገኘው ነገር እንደሌለ ግልፅ ነው::

በተለይም አማራው ለይቶለት ህሊናው ካልሸጠ ዐቢይ ለአማራ ክፉ ያስባል ብሎ የሚያሳምን መረጃ የለውም::ቆም ብሎ ማሰብና ማመዛዘን ይበጃል:: ህውሀት ከላይ  በአማራው ላይ ጦርነት አውጆ ትጥቁን እያዘጋጀ ነው:: ከመሀል ሀገር ደግሞ የህውሀት ርዝራዦችና ተስፈኛ የፖለቲካ ደላላዎች አማራንና ኦሮሞን ለማጋጨት ደፋ ቀና ይላሉ:: በዚህ ድምር ውጤት ተጎጂው የአማራ ህዝብ ነው:: አዴፓ ይህንን ችላ ብሎ ማየት የለበትም:: ህውሀት ተሳክቶለት 27 አመታት ጨምድዶ በመግዛት ሀገሪትዋን የዘረፈው በአንድ አቢይ ጉዳይ በእጁ ስላስገባ ብቻ ነው:: ይኸውም ኦሮሞንና አማራን በመለያየት የፖለቲካ ጥበብ የተካነ በመሆኑ ነው:: የኢትዮጵያን ሀይል ለመምታት የኢትዮጵያ ልብ የሆነውን ሸዋ ክፍለ ሀገር መበተን ነው::ሸዋ የኦሮማራ ሀገር ነው ማለት ይቻላል ::በህዝብ ብዛትም ከኢትዮጵያ 70% ኦሮሞ ወይንም አማራ ነው::በሸዋ ህዝቡ በደምና በባህል ተቀላቅሏል:: ይህን አንድነት ከበተነ ለህውሀት ኢትዮጵያን ረግጦ እንደሚገዛ እሙን ነበር::ይህ ነው የህውሀት ጥበብ:: ይህ ነው በ 27 አመታት 6% ህዝብ የሚወክል ድርጅት 100% ጨምድዶ ለመዝርፍና መግዛት ያበቃው::ለኦሮሞው የአማራውን ጭራቅነት በመስብክ : ጎንደሬውንና ወሎዬውን ደግሞ ከሸዋ እኛ እንሻልሀለን በማለት በኤርትራዊው በረከት ስምኦን fake ጎንደሬ የጎንደር አማራ ሸዋን እንዲርቅ በጥሩ ሰርቶላቸዋል::በተፈሪ መኮንን ዘመን በሸዋና በጎንደር በሸዋና ወሎ መካከል የነበሩ የጦርነት ቁርሾዎች ለህውሀት ከፋፋይነት አጀንዳ አገልግለዋል:: ይህን በመአሕድ የመጀመሪያ አመቶች መገንዘብ ችዬአለሁ::በጎንደሬው ላይ ከመላው አማራነት ትግል እንዲርቅ በሰፊው ተሰርቶበታል::ይህ ለህውሀት ህዝብን ለመለያየትና ለዘረፋ አገልግሏል::ይህቺን የሚያውቁ የትግራይ ዘፋኞች ስለኢትዮጵያ ሲያቀነቅኑ ክሊፓቸውን አፄ ቴዎድሮስን ብልጭ አድርገው በአፄ ዮሐንስ ይጨርሱታል:: ምኒልክና ቀጣዮችን የእነሱ ኢትዮጵያ አታስተናግድም:: ይህ ከፋፋይ አጀንዳ በደንብ ነው የተሰራበት::የመንግስት መዋቅር በተለይም በአዲስ አበባ ከላይ እስከፅዳት ሰራተኛ በህውሀት ሰንሰለት የተቆላለፈ ነው::ጌቶቻቸው መቀሌ ይመሽጉ እንጂ የዘረጉት መዋቅር ለዐቢይ እጅግ ፈታኝ ይሆናል:: ህዝብ የተባለው ቆም ብሎ ከማገዝ የሚያማርርና የሚያለቃቅስ የሞብ (mob) ስራ ስለሚጠመድ ጠዋት ሲያሞግስ ማታ የሚራገም ነው::አስታውሳለሁ ኮልፌ አካባቢ የኢትዮጵያ እግር ኳስ አሸነፈ ተብሎ መንገድ ማቋረጥ አልቻልኩም:: ለህይወት የሚያስጋ እብደትና ደስታ ነበር::ፊቱን የተቀባው ደጋፊ ህይወቱን ለቲሙ የሚሰጥ ይመስላል::ግን 6 ወራት በሗላ አዲስ አበባ ተመልሼ ያየሁት ክስተት ተስፋ አስቆራጭ ነበር:: በኢትዮጵያ ቡድን ላይ የነበረው ስድብ ሞራል ይገላል:: በአሜሪካ የቲም ደጋፊ በክፉም ደጉም ቲሙን 40 አመታትም ቢሆን አብሮ ይቆማል ይደግፋል:: የኢትዮጵያ ህዝብ አስቸጋሪ ባህል አለው::ዐባይ አሕመድን ልዑል እግዚአብሄር ብቻ ይርዳው::ህውሀት አማራን ለመውረር ዝግጅቱን አጠናቋል:: የጄኔራል ተፈራ ማሞ መረጃ ችላ የሚባል አይደለም:: ልቡ የተወጠረ እብሪተኛ በወንጀል የሚፈልግ ሽብርተኛ ቡድን ወረራ አያካሄድም ብሎ መዘናጋት ጅልነት ነው:: ህውሀት ፊታውራሪዎቹን በማሰለፍ በመሀል ሀገር በኦዴፓና አዴፓ መካከል ክፍተት በመፍጠር አማራውን የበለጠ አዳክሞ ለወረራው እያመቻቸ ነው::ለዚህም ፈቃደኛ በመሆን ኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ደላላዎች የህውሀት ጉዳይ አስፈፃሚነት ስራ ላይ ተጥደዋል::የአዴፓ እመራርና ኦዴፓ ወቅታዊ ስብሰባዎችን በማካሄድ ክፍተቶችን መሸፍን ይኖርባቸዋል::አዴፓና አብን ከምንጊዜው በላይ በዚህ ፈታኝ ወቅት በአማራ ጉዳይ እብረው መስራት ይኖርባቸዋል::አዴፓ ዳር ቆሞ የሚመለከተውን አማራ በሙሉ ማሳተፍ ወቅቱ የሚጠይቀውም ክስተት ነው::ፖለቲካ ስልጡን ታክቲክና ንቃት ተሳትፎን ይጠይቃል:: በዚህ ፈታኝ ወቅት አዴፓ በአዲስ አበባ ጉዳይ መምከር ይኖርበታል::አማራውንና ኦሮሞውን ለመለያየት ለሚፈልጉ ደላሎች እድል መክፈት የለበትም::የዛሬ ጦርነቶች የሚካሄዱት በፌስቡክ ጫካ ነው::ህውሀት 35 ሺ ዲጂታል ወያኔዎች አሰማርቷል::አዴፓና ኦዴፓ ተቀራርበው በመስራት በህዝባቸው መካከል የሚፈጠሩትን ደባዎች ማምከን ይኖርባቸዋል::