ከአጼ ቴዎድሮስ ቁንዳላ በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ቅርሶችም ተዘርፈዋል
አጭር የምስል መግለጫ ከአጼ ቴዎድሮስ ቁንድላ በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ቅርሶችም ተዘርፈዋል

የአፄ ቴዎድሮስ ቁንዳላ ከ150 ዓመታት በኋላ ሊመለስ ነው።

በመቅደላ ጦርነት ወቅት ለእንግሊዞች እጅ አልሰጥም ብለው ራሳቸውን ያጠፉት የአፄ ቴዎድሮስን ቁንዳላ ከ150 ዓመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ሊመለስ መሆኑን በእንግሊዝ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ገልጿል።

“ፍቃዱ ተክለማርያም የሀገር ቅርስ ነው”

ኢትዮጵያዊው ጀማል ይመር በአስር ሺ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆነ

በእንግሊዝ ሀገር በሚገኘው የብሔራዊ ጦር ሙዝየም በይዞታው ሥር የቆየውን የአፄ ቴዎድሮስ (መይሳው ካሳ) ቁንዳላ ለመመለስ መስማማቱን የተገለፀ ሲሆን በመጪው ሐሙስም ከኤምባሲው ጋር ውይይት ሊያደርግ ቀጠሮ ተይዟል።

አፄ ቴዎድሮስ መቅደላ ላይ በ1868 ዓ. ም. ከእንግሊዝ አገር ከመጡ 32 ሺ ወታደሮች ጋር ተዋግተው ራሳቸውን ማጥፋታቸውን ተከትሎ በሀገሪቷ ላይ ከፍተኛ ዘረፋ እንደተፈፀመ የታሪክ መዛግብት ያወሳሉ።

ምንም እንኳን የእንግሊዝ ጦር አዛዦች አፄ ቴዎድሮስ ይዘዋቸው የነበሩ እስረኞችን ለማስፈታት ነው ቢሉም የንጉሡን ቁንዳላ ከመሸለት በተጨማሪ መስቀልና የጣት ቀለበታቸውን፤ ሸሚዛቸውንና ሽጉጣቸውን ዘርፈዋል።

አሜሪካ ለላሊበላ ቤተክርስትያን ጥበቃ ፕሮጀክት 13.7 ሚሊዮን ብር ሰጠች

900 ዓመታትን ያስቆጠሩ የወርቅ ሳንቲሞች ተገኙ

ከዚህም በተጨማሪ መጻሕፍት፣ የተለያዩ ከወርቅ የተሠሩ ቅርሶችን፣ መንፈሳዊ ሥዕሎችን፣ ታቦታት፣ ታሪካዊና ባሕላዊ ቅርሶች ሳይቀሩ ተዘርፈዋል፤ ቅርሶች ተቃጥለዋል፤ መጻሕፍትንም ቀዳደዋል።

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የጀግና ተምሳሌት የኾኑት የአፄ ቴዎድሮስ ቁንዳላ ወደ ሀገራቸው መመለስ ከፍተኛ ደስታን እንደፈጠረም ኤምባሲው በመግለጫው አስታውቋል።

በባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ የታሪክ ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት ተመስገን ገበየሁ “የአጼ ቴዎድሮስ ቁንዳላ ወደ ኢትዮጵያ ሊመለስ በመሆኑ ደስ ብሎኛል” ብለዋል። በርካታ የአጼ ቴዎድሮስ የግል ንብረቶች በመቅደላው መዘረፋቸውን ገልጸው፣ የንጉሡ ቁንዳላ ሊመለስ መኾኑን በጎ ጅማሮ ነው ብለዋል።

“ይህ ጅማሮ ነው። ብዙ መመለስ ያለባቸው ቅርሶች አሉ፤ ይመለሳሉ ብዬ አምናለሁ”

የአጼ ቴዎድሮስ ቁንዳላ መመለስ ጎብኚዎችን ስለሚስብ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንደሚኖረው መምህሩ ተናግረዋል።

ተያያዥ ርዕሶች


March 4, 2019

7

የአፄ ቴዎድሮስ ፀጉር (ቁንዳላ) ወደ አገሩ ሊመለስ ነው

ከ150 ዓመታት በፊት በመቅደላ በተደረገው ጦርነት ለእንግሊዞች እጅ አልሰጥም ብለው እራሳቸውን ካጠፉ በኋላ የተወሰደው የአፄ ቴዎድሮስ ጸጉር ወደ አገሩ ሊመለስ ነው።
የእንግሊዝ ብሄራዊ የጦር ሙዚዬም ፀጉሩን በሚመለስበት ሁኔታ ላይ ለንደን ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር ለመነጋጋር በቀጣዩ ሃሙስ ቀጠሮ መያዙንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የሙዚየሙ እርምጃ ለበርካታ ዓመታት ለዘለቀው የኢትዮጵያና እንግሊዝ በጋራ ጥቅምና መከባባር ላይ የተመሰረተው ግንኙነት አንዱ ማሳያ እንደሆነ ለንደን የሚገኘው ኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
የዘመናዊ ኢትዮጵያ ቀያሽ ተደርገው የሚወሰዱት አጼ ቴዎድሮስ ጸጉራቸው ወደ እናት አገራቸው ሲመጣ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ደስታ እንደሚፈጥር ይጠበቃል።
ሙዚየሙ ለወሰደው እርምጃ ከፍተኛ አድናቆት እንዳለው ኤምባሲው አስታውቋል።
ምንጭ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር