March 5, 2019

ለማ መገርሳ እና ዐቢይ አሕመድ ከእግዚአብሄር የተላኩ ናቸው ሲሉ የቆዩት ፕ/ር  መስፍን ወልደማርያም፣ ራሳቸው ለማ እና ዐቢይ ለውጡን እየቀለበሱት ነው ብለዋል። ,,, ( ቪዲዮን ያዳምጡት )

00:00/01:0700:00Next Video×

“…..ነገሩ በንግግር ደረጃ: ለማ መገርሳንም ስሰማ (በተለይ ለማ መገርሳ!) በዘር ፖለቲካ ላይ: በጣም ጫን ብሎ: ተቃውሞ ድምፅ ያሰማ ይመስለኛል–እኔ እንደሰማሁት:: አብይ እንደሱ [እንደ ለማ] ያህል ባይሰማኝም: እሱም አንድ ላይ ናቸው ያሉት::

ነገር ግን ይህ ዲስኩር ነው:: በዲስኩር ደረጃ ግሩም ናቸው:: በተግባር ደረጃ ግን: የሚሰራው: የምናየው ሹመቱንም: ምኑንም ስንመለከት: የምንገንዘበው እልተለውጥንም:: ያው ነው:: መንግዳችን ያው ነው:: የዘር መንገድ ነው የያዝነው:: ላለፉት 40 ዓመት ከሄድንባቸው ጉዞ: እንዲያው መንጥቆ የሚያወጣን: ደረጃ ላይ ደርስን ስንል: ቀስ ቀስ እያለ እንደገና የሚደፍቀን ሁኔታ ውስጥ እየገባን ነው:: እናም አሳዛኝ ሁኔታ እየተፈጠረ እንደሆነ ይመስለኛል::

የእነ ለማና አብይ አብዮት እተቀለበሰ ነው ለማለት ይቻላል [ይመስለኛል]:: ደግሞ ሌላ ስው ቀልብሶባችው አይደለም:: እራሳቸው [ለማ+ አብይ] እየቀለብሱት ነው።”

ፕ/ር  መስፍን ወልደማርያም እንደተናገሩት