March 7, 2019

t

የኮዬ-ፈጬ ኮንዶሚኒየም ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኖ ሰነባብቷል፡፡ ‹‹ከኮንዶሚኒየም መስሪያ ስፍራው የተፈናቀሉ ወገኖች ቤት ያግኙ!›› ከሚሉ ሰዎች እስከ ‹‹መሰጠት የለበትም!›› የሚሉ ታዛቢዎች ድረስ ብዙ አነታርኳል፤ አሰዳድቧል፤ አገለማምጧል፡፡ ጉዳዩ የጦዘው በአካባቢው ይኖሩ የነበሩ ገበሬዎች ተፈናቅለው በአሳዛኝ ሁኔታ እየኖሩ ‹‹ነው!›› የሚል መረጃ በኦሮሞ ዘረኞች በኩል ስለተራገበ ነው፡፡ በተጨማሪም፣ ኮንዶሚኒየሙ በኦሮሚያ ‹‹ክልል›› ስር ስለተገነባ፣ ዕጣው በ‹‹ክልሉ›› ፈቃድ ተመስርቶ መተላለፍ ‹‹አለበት!››ም ብለዋል፡፡ ሃቁ ግን ይህ አይደለም፡፡ ከጀርባ ብዙ ፖለቲካዊ ተውኔት እየተከናወነ ነው፡፡

የጃዋር መንግስት

ራሱን ‹‹የፖለቲካ ሳይንቲስት›› እያለ የሚያቆሻብለው ጃዋር መሃመድ አሜሪካ – ሚኒሶታ ሳለ፣ ሃገር ውስጥ በርካታ ወጣቶችን ጠርንፎ ሲመራ ነበር፡፡ ‹‹መንገድ ዝጉ!›› ሲል የሚዘጉ፣ ‹‹አድማ ምቱ!›› ሲል የሚያድሙ ሮቦትና ስራ-እጥ ወጣቶችን በ‹‹ኔትወርኩ›› ስር አቅፎ ነበር፡፡ ለውጥ-አልባው ‹‹ለውጥ›› ከመጣ በኋላ፣ አገልግል ሚዲያውን – OMNንና ጀሌዎቹን በአውሮፕላን ጭኖ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ፡፡ መመለሱ ግን ሰላምን ሳይሆን ጥፋትን ነበር ይዞ የመጣው፡፡ መጀመሪያ በ‹‹ሸኔ-ኦነግ›› የአቀባበል ዝግጅት ላይ በተከሰተ ውርክብ ምክንያት የተፈጠረውን ግጭት አጋግሎ እስከ ቡራዩ የተራዘመ አስከፊ ዘር-ተኮር ጥቃት እንዲከሰት አበረታቷል፡፡ አወናባጅ ወሬዎችን በአገልግል ሚዲያው በመንዛት፣ የወሮበሎችን ወንጀል ለማለባበስ ሌት ተቀን ጥሯል፡፡ ቀስ እያለም የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ግጭት በመቀስቀስ፣ አጥፊ ሚናውን ተወጥቷል፡፡ አገልግል ሚዲያው ላይ ቀርቦ ‹‹ሁለተኛ መንግስት›› ስለመኖሩም በጨረፍታ ተናግሯል፡፡ ዕውነትም ‹‹ሁለተኛ መንግስት››!

በየሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የራሱን ጀሌዎች ከግብረ-አበሮቹ ጋር በመመሳጠር አስቀምጧል፡፡ ደህንነቱንም፣ ኢኮኖሚውንም፣ ጠቅላዩንም…ጠፍንገው ይዘውታል – የጃዋር ጀሌዎች፡፡ ማንኛውንም – የእነርሱን ጥቅም የሚጻረር ውሳኔ – በጫና አስቀይረው ህገ-ወጥ ውሳኔ ያስወስናሉ፡፡ የታከለ ኡማ ‹‹ለገበሬዎች ቅድሚያ ቤት ይሰጣል!›› ማለቱን ልብ ይሏል፡፡

ሁለተኛው መንግስት (የጃዋር መንግስት) የሴራ ድርጊያውንና ደጀኑን አስፍቷል፡፡ የማይነቃነቅ መሰረቱንም እያሰቀመጠ ነው፡፡

ምርጫችን ምን መሆን አለበት?

መጪው 2012 ዓ.ም የምርጫ ጡዘት የሚበዛበት ዓመት እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ በእርግጥ፣ መካሄድ – አለመካሄዱ አልታወቀም፡፡ ግን የምርጫ ቦርድ መጠነ-ሰፊ ዝግጅት ላይ ነው፡፡ ምርጫው ‹‹ይካሄዳል!›› ብለን ከገመትን፣ ምርጫችን ‹‹ምን መሆን አለበት?››የሚለው ቁልፍ ጥያቄ ነው፡፡ የምርጫ ወረቀት (እንደምግብ menu ያለ) ላይ በተቀመጠልን ምልክት መሰረት፣ የምንመርጠው ፓርቲ መጀመሪያ አዲስ አበባን እንደአዲስ አበባነቷ ጠብቆ የሚያዘልቅ ዕቅድ ሊኖረው ያስፈልጋል፡፡ ግን የምርጫው መዘርዝር ውስጥ ተፈላጊው ፓርቲ ባይኖርስ? አማራጭ የለንም፣ ወገብን አጥብቆና ተደራጅቶ ለአዲስ አበባና አዲስ አበቤነት መታገል ብቻ! የጃዋርንና የጃዋር-ብክል የሆነውን መንግስት አምኖ መቀመጥ እንደመጠቃት ይቆጠራል! ሲለጥቅ፣ በሃገር-አቀፍ ደረጃም የህዝባዊ መንግስት ህልውና እንዲረጋገጥ በአንድነትና በቁርጠኛነት መታገሉ ይመከራል! ምርጫችን ለህዝባዊ መንግስት መታገል መሆን አለበት!