ገዱ አንዳርጋቸው የስራ መልቀቂያ ማቅረባቸውን ተከትሎ ዶ/ር አምባቸው መኮንን የአማራ ክልል ም/ርእሰ መስተዳድር ሆነው ተመረጡየአማራ ክልል ምክር ቤት እያደረገ ባለው ስብሰባ ላይ የአቶ ገዱ አንዳርጋቸውን የመልቀቂያ ጥያቄ ተቀብሏል፡፡የአማራ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (አዴፓ) ክልሉን እንዲመሩ ዶ/ር አምባቸው መኮንንን በእጩነት አቅርቧል፡፡ዶ/ር አምባቸው መኮንን የአማራ ክልል ም/ርእሰ መስተዳድር ሆነው የተመረጡት የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ያቀረቡት መልቀቂያ ተከትሎ ነው፡፡
ዶ/ር አምባቸው መኮንን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ – ቢቢሲ/ አማርኛ

የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የመልቀቂያ ጥያቄ ማቅረባቸውን የኃገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ዘገባውም እንደሚያስረዳው ጥያቄውን ያቀረቡት እየተካሄደ ባለው የክልሉ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ነው።
•የብአዴን መግለጫ፡- ከስያሜ መቀየር እስከ ኢትዮ ሱዳን ድንበር
ፓርቲያቸው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የርዕሰ መስተዳድሩን ጥያቄ የተቀበለው መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ምክንያታቸውንም ፓርቲያቸው ለክልሉ ምክር ቤት ያቀርባል።
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለአምስት አመታት ያህል ክልሉን በርዕሰ መስተዳድርነት መርተዋል።
በምትካቸውም ዶ/ር አምባቸው መኮንን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾመዋል።
