March 8, 2019

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 29 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረዳት ዋና ፀሀፊ በመሆን ተሾሙ ።
የድርጅቱ ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቶሬዝ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁን የድርጅቱ ረዳት ዋና ጸሀፊ አድርገው መሾማቸውን በዛሬው እለት የካቲት 29 ቀን 2011 ዓ.ም ይፋ አድርገዋል።
ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ለዚህ ከፍተኛ ሃላፊነት የተሾሙት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን እንዲሁም ለድርጅቱ ዘላቂ የልማት ግቦች መሳካት ላደረገችው አስተዋጽኦ ከፍተኛ የመሪነት ሚና በመጫወታቸው ነው።
የተመድ ውሳኔ ኢትዮጵያ በባለብዙ ወገን መድረኮች እስካሁን ላከናወናችው እንቅስቃሴ የተሰጠ እውቅና መሆኑን የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በቀጣይም ከፍተኛ አካባቢያዊና አህጉራዊ ሃላፊነት እንዳለባት የሚያመለክት ነውም ብሏል።
የተመድ ረዳት ዋና ጸሀፊ ቦታ በድርጅቱ ሶስተኛው ከፍተኛ የሃላፊነት እርከን ነው።
ዶክተር ወርቅነህ መቀመጫውን ኬንያ ናይሮቢ ያደረገውን የተመድ ዋና ጽ/ቤት የመምራት እና የማስተባበር ሃላፊነት ተሰጥቷቸዋል።
የተመድ የኬንያ ጽ/ቤት አምስት ሽህ ሰራተኞችን የያዙ አስራ ስምንት ኤጄንሲዎችን የሚያስተዳድር ሃላፊነት አለው።
