
10 March 2019
የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) ስብሰባ በደቡብ ክልል የሲዳማ ዞን ተወካዮች ምክንያት ተቋረጠ፡፡ ለስብሰባው መቋረጥ ምክንያት የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄ በስብሰባው ተንኳስሶ ቀርቧል በሚል ሲሆን፣ ስብሰባው በተጀመረ በሁለተኛ ቀኑ ተወካዮቹ እንዲቋረጥ ማድረጋቸው ታውቋል፡፡
የድርጅቱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ከሐሙስ የካቲት 28 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ እሑድ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ ሊያካሂደው ያቀደውን ስብሰባ በሐዋሳ ለአንድ ቀን ካደረገ በኋላ፣ በሁለተኛ ቀኑ ዓርብ የካቲት 29 ቀን 2011 ዓ.ም. በሲዳማ ዞን አመራሮች ጥያቄ ምክንያት ሊቋረጥ ችሏል፡፡
የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄ በደቡብ ክልል ምክር ቤት ከወራት በፊት ቀርቦ፣ ምክር ቤቱም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ሪፈረንደም እንዲካሄድ በጽሑፍ ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፣ በምላሹ መዘግየት ምክንያት በሐዋሳ ከተማ ሪፈረንደሙ በፍጥነት እንዲካሄድ በቅርቡ ሠልፍ ተካሂዶ ነበር፡፡ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በወቅቱ በሰጡት ምላሽ፣ ምርጫ ቦርድ አሁን ሌላ ሥራ ላይ በማተኮሩ ሪፈረንደሙን በቅርቡ ማድረግ እንደማይቻል ተናግረው ነበር፡፡
ይሁንና የሪፈረንደሙን አለመደረግ ምክንያት በማድረግ ደኢሕዴን በሚያደርገው ስብሰባ ላይ እኛም እንሳተፋለን በማለት የሲዳማ ‹‹ኤጄቶ›› የሚባሉ ወጣቶች የስብሰባው አዳራሽ ገብተው እንደነበር ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
በዚህ መሀል ስብሰባው እንዲቀጥል ቢደረግም የሲዳማ ዞን የደኢሕዴን አመራሮች ጥያቄቸው ከሌሎች አዳዲስ ጥያቄዎች ጋር እኩል መታየት የለበትም ሲሉ እንደ ተቃወሙም ተሰምቷል፡፡ በዚህም ምክንያት በክልሉ ውስጥ የሚነሱ የክልልነት ጥያቄዎችን ለማጥናት የተቋቋመው ቡድን ‹የእኛን ጉዳይ መመልከት የለበትም› በማለት ተቃውሞ ማሰማታቸው ታውቋል፡፡ ነገር ግን ሌሎች አባላት በቀደመና ባልቀደመ ሳይሆን፣ ምክንያታዊ ጥያቄ በማቅረብና ባለማቅረብ መመዘን አለበት በማለት፣ የሁሉም ጥያቄ በአጥኚ ቡድኑ ግኝት ምላሽ ያግኝ ሲሉ መከራከራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ከስብሰባው ውጪ በሐዋሳ ከተማ በተለያዩ ሥፍራዎች ‹‹ኤጄቶ›› በመባል የሚታወቁት የዞኑ ወጣቶች በተለያዩ አደባባዮችና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የክልሉን ሰንደቅ ዓላማ ሲያወርዱ ታይተዋል፡፡
የድርጅቱ ስብሰባ በዘጠኝ ቡድኖች ተከፍሎ ሲካሄድ እንደነበር የገለጹት ምንጮች፣ ስብሰባው የተቋረጠበት ሰዓት እንደ ቡድኑ መለያየቱንና የተወሰኑት ቡድኖች ግን የቀኑን ስብሰባቸውን ሊያጠናቅቁ ሲሉ መቋረጡን አክለዋል፡፡
የተለያዩ የክልልነት ጥያቄዎች መነሳታቸው ሕጋዊ አግባብ ያለው መሆኑን ሁሉም የድርጅቱ አባላት እንደሚስማሙ የተናገሩት ምንጮች፣ የክልልነት ጥያቄ የቀበሌነት ጥያቄን ያህል እንኳን የመተግበር ክብደት ስለሌለው በአጥኚ ቡድኑ የሚቀርበውን ምክረ ሐሳብ መጠበቅ እንደሚገባ መተማመንም አለ ብለዋል፡፡
የክልልነት ጥያቄ የሚያቀርቡ ዞኖች በቢሊዮን የሚቆጠር በጀት እየተመደበላቸው እነሱ ግን አመንጭተው ሩብ ያህሉን እንኳ እንደማይሸፍኑ፣ በዞን አደረጃጀት መቀየር ምክንያት ካሁን ቀደም ወደማያባራ ብጥብጥ የገቡ አካባቢዎችን እያዩ ትምህርት መውሰድ እንደሚገባ በርካቶች ያሳስባሉ፡፡
ስብሰባው ሲቋረጥ ከዘጠኙ ቡድኖች በአንዱ የወላይታ ዞን የድርጅት አመራሮች ቡድን ከውጭ ከገቡ ግለሰቦች ጋር በተፈጠረ ግጭት ሁለት ሰዎች መጎዳታቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ስብሰባው ሲጀመር መደበኛ የፀጥታ አስከባሪዎች በሥፍራው እንደነበሩ የገለጹት ምንጮች፣ ዓርብ ከቀትር በኋላ የመከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል ፖሊስ አባላት በሥፍራው መሰማራታቸውን አስታውቀዋል፡፡ድ

Mar 10, 2019መንግሥት ያረቀቀው የጦር መሣሪያ ቁጥጥር አዋጅ ፖለቲካዊ ፋይዳMar 10, 2019በሰብዓዊ መብት ጥሰት ተጠርጥረው የተከሰሱት መርማሪዎች መቃወሚያ አቀረቡMar 10, 2019የቀድሞ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ከቀረጥ ነፃ ኃላፊ እስራት ተፈረደባቸው

Mar 10, 2019‹‹ፀብ አጫሪና የጥላቻ ድርጊቶች ጎጂ በመሆናቸው ተማምነንና ተግባብተን ውድቅ ልናደርጋቸው ይገባል›› አምባቸው መኮንን (ዶ/ር)፣ ተመራጩ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት

Mar 10, 2019የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተሾሙ

Mar 10, 2019የኮንዶሚኒየም ቤቶችን ለማስተላለፍ የወጣው ዕጣ ተቃውሞ ቀረበበት
ማስታወቂያ

ማስታወቂያ

ለዜና መጽሔታችን ደንበኝነት ይመዝገቡ
የኢሜል አድራሻ ዜና መጽሔት
- ሳምንታዊ ዜና መጽሔት
- ሰበር ዜና
ማስታወቂያ
ማስታወቂያ

የቅርብ ዜና
- 01‹‹ፀብ አጫሪና የጥላቻ ድርጊቶች ጎጂ በመሆናቸው ተማምነንና ተግባብተን ውድቅ ልናደርጋቸው ይገባል›› አምባቸው መኮንን (ዶ/ር)፣ ተመራጩ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት
- 02የለገጣፎ ተፈናቃዮች መውደቂያ አጥተናል እያሉ ነው
- 03የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተሾሙ
- 04የደኢሕዴን ስብሰባ በሲዳማ ዞን አመራሮች ተቃውሞ ምክንያት ተቋረጠ
- 05የኮንዶሚኒየም ቤቶችን ለማስተላለፍ የወጣው ዕጣ ተቃውሞ ቀረበበት
- 06የአማራና የትግራይ ክልል መንግሥታት በመካከላቸው ለጠፋው ሰላም በተጠያቂነት ተወነጃጀሉ
ማስታወቂያ
ብዙ የተነበቡ
- ማኅበራዊ | Mar 06የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ተመዝጋቢዎች መቆጠብ ያለባቸው የገንዘብ መጠን ይፋ ሆነ
- ፖለቲካ | Feb 24በአዲስ አበባ የነዋሪነት መታወቂያ የሚሰጥበት መመርያ ሥጋት አጭሯል
- ፖለቲካ | Feb 27በሚመሠረተው አገር አቀፍ ፓርቲ መካተት ለሚፈልጉ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም በሩ ክፍት መሆኑን ኢሕአዴግ ገለጸ
- ፖለቲካ | Mar 03አምስት ሚሊዮን ብር ለሚከፈልበት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የራት ግብዣ ምላሾች እየመጡ ነው
- ማኅበራዊ | Feb 24የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር ቤቶችን የማፍረስ ዕርምጃና የተፈናቃዮች ጩኸት
- ፖለቲካ | Mar 03በዩኤንዲፒ ድጋፍ በከፍተኛ የመንግሥት አማካሪነት ያለ ውድድር የሚቀጠሩ ግለሰቦች ጉዳይ ቅሬታ ፈጠረ
e-bound adds
የሪፖርተር አድራሻ
ሪፖርተር
ሚዲያና ኮምዩኒኬሽንስ ሴንተር
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የሪፖርተር አገልግሎት
Reporter Tenders
https://www.reportertenders.com
Reporter Jobs
https:\\www.ethiopianreporterjobs.com
Goalgoogle
http://goalgoole.com/
የሪፖርተር የሥራ ሰአት
ከሰኞ እስከ አርብ: ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ምሽት 11 ሰዓት
የቅጂ መብት © 2018 ሚዲያና ኮምዩኒኬሽንስ ሴንተር፡፡ ሁሉም መብቶች የተጠበቁለት፡፡ ✓Thanks for sharing!Facebook Twitter Email Pinterest LinkedIn Reddit WhatsApp Gmail Telegram Pocket Mix Tumblr Amazon Wish List AOL Mail Balatarin BibSonomy Bitty Browser Blinklist Blogger BlogMarks Bookmarks.fr Box.net Buffer Care2 News CiteULike Copy Link Design Float Diary.Ru Diaspora Digg Diigo Douban Draugiem DZone Evernote Facebook Messenger Fark Flipboard Folkd Google Bookmarks Google Classroom Google+ Hacker News Hatena Houzz Instapaper Kakao Kik Kindle It Known Line LiveJournal Mail.Ru Mastodon Mendeley Meneame MeWe Mixi MySpace Netvouz Odnoklassniki Outlook.com Papaly Pinboard Plurk Print PrintFriendly Protopage Bookmarks Pusha Qzone Rediff MyPage Refind Renren Sina Weibo SiteJot Skype Slashdot SMS StockTwits Svejo Symbaloo Bookmarks Threema Trello Tuenti Twiddla TypePad Post Viadeo Viber VK Wanelo WeChat WordPress Wykop XING Yahoo Mail Yoolink Yummly AddToAnyFacebook Twitter Email Pinterest LinkedIn Reddit WhatsApp Gmail Email Gmail AOL Mail Outlook.com Yahoo Mail
