March 10, 2019


አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ማጋቢት 2 ቀን 2011 ዓ.ም ብሄራዊ የሃዘን ቀን እንዲሆን አወጀ፡፡
በዚሁ መሰረት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በመላው ሀገሪቱ፣ በውጭ ሀገር በሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሲዎችና ቆንሰላ ጽህፈጽ ቤቶች እንዲሁም በኢትዮጵያ መርከቦች ላይ ዝቅ ብሎ ይውለበለባል፡፡
ምክር ቤቱ ብሄራዊ የሀዘን ቀኑን ያወጀው ዛሬ ንብረትነቱ ኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 737 አውረፕላን ተከስክሶ የ157 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተክትሎ ነው፡፡
