March 17, 2019

በእኛ አገር የሃይማኖት ፓርቲ እንደሌለ ሁሉ የጎሳ ፖለቲካም ሊከለከል ይገባል። ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት

በመጀመሪያ ደረጃ ፓርቲዎች የሉም።
እነዚህ አንቺ ፓርቲ የምትያቸው የጎሳ ድርጅቶች ናቸው።
በዚህ የጎሳ ድርጅቶች ውስጥ መሪ ነን የሚሉት ንጉሥ ለመሆን የሚፈልጉ ናቸው። ሁሉም ንጉሥ መሆን የሚፈልግ ባለበት ድርጅት ውስጥ ደግሞ መስማማት አይችልም። ምክንያቱም ወንበሩ አንድ ነው። ስለዚህ ስምምነት ላይ ሊደርሱ አይችሉም።

ጎሳዎቹ ብዙ ስለሆኑ በቁጥርም ሊያንሱ አይችሉም።
እናም የሚያዋጣው ነገር የጎሳ ፓርቲን መሰረዝ ነው። በእኛ አገር የሃይማኖት ፓርቲ እንደሌለ ሁሉ የጎሳ ፖለቲካም ሊከለከል ይገባል። የፖለቲካ ፓርቲ የሚባለው የሚጣጠሙ ሰዎች አንድ ላይ ሆነው የሚመሰርቱት የፖለቲካ ቡድን ነው። ማንም ሰው ሊገባ ይችላል። ክፍት ነው። የጎሳ ቡድን ዝግ ነው።

ለምሳሌ አሜሪካ ጥቁሮች ፓርቲ የላቸውም።
ያ ሁሉ ስቃይ የደረሰባቸው ደቡብ አፍሪካ እንኳ የጎሳ ፓርቲ የላቸውም። እኛ ጋ ፖለቲካውም አዲስ ነው። ፖለቲካ ምን እንደሆነ አናውቅም። ዋናው ነገር ስልጣን አግኝቶ ለመደፍጠጥና ረጋጭ መሆን ነው የሚፈልገው። ስለዚህ ፓርቲ በሌለበት የምመክረው የለኝም።
► መረጃ ፎረም – JOIN US