March 18, 2019
የታዬ ደንደአ የዘር ማጥፋት ዘመቻ! አቻምየለህ ታምሩ ከታች የምትመለከቱትን ነውረኛነት የጻፈው Taye Dendea ይባላል። ታዬ ደንደአ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነበር። ታዬ ባሁኑ ወቅት በዐቢይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኦዴፓ ማዕከላዊ ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ምክትል ኃላፊ ነው። ከታች የጻፈውን ብቻ ብንወስድ ሰውየው በአማራ ላይ ያለውን የመረረ ጥላቻ ናላው እንዳዞረው ማየት ይቻላል። የነታዬ የፖለቲካ መራቀው ሰው ለሆነ ፍጡር ሁሉ የተሻለ አስተሳሰብ መያዝ ሳይሆን አማራን መጥላት ነው። ዐቢይ የሚመራው ፓርቲ ማዕከላዊ ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ምክትል ኃላፊው ታዬ [አማራን ከአዲስ አበባ አባረን] ዲሞግራፊውን በኦሮሞ እንቀይረዋለን ይለናል። ካሁን በኋላም አማራ ወደ ዐፄ ዳዊት ከተማ እንደሚገባ እንደማይፈቅዱለት ይነግረናል። እንዲህ አይነት የጭካኔ አስተሳስብ የያዘው ሰው ሕዝብ በሚገለገልበት ቦታ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሆኖ በሚጠላው ሕዝብ ላይ የሚፈጽመውን ነውረኛነት፣ ወንጀልና ኢሰብአዊ ግፍ መገመት አይከብድም። ታዬ የሕግ ባለሞያ ነው። የሥራ ድርሻውም ሕግ ማስከበር ነው። ሆኖም ግን እንኳን ሕግ ሊያስከብር አማራን እያፈናቀለ ኦሮሞን በማስፈር ዲሞግራፊን በመቀየር የዘር ማጥፋት ወንጀል ራሱ እየሰራ ይገኛል። እንደ ታዬ አይነቱ በውስጣቸው ያለውን የመረረ ጥላቻ በአደባባይ እንዲህ እያወጡ የሚጽፉ ባለሥልጣኖች መኖራቸውን ወድጀዋለሁ። እንደነሱ አይነት ሰዎች ባይኖሩ ኖሮ የዘር ማጥፋት እያካሄዱበት ያለው አማራ በርስቱ ላይ የኅልውና ተጋድሎ ሊያደርግ እንዲህ ከዳር እስከዳር አይነሳም ነበር። እኛ አማራ እንዲደራጅ ከቀሰቀስነው በላይ አማራው እንዲደራጅና እንዲጋፈጥ ጉልበት የሆነው እነ ታዬ ደብደአ አይነት የዘር ማጥፋት ዘመቻ እያካሄዱ እንደሆነ የሚነግሩን የኦሮሞ ባለሥልጣኖች ናቸው። አሁንም እንደ ታዬ ደንደአ አይነት ሰዎችን ያብዛልን! «ርስት በሺ ዓመቱ ለባሌቤቱ» ይላል ያገራችን ሰው ሲተርት። ኢትዮጵያ በምትባል አገር በጋራ እንኖራለን ብሎ ከርስቱ ፈልሶ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ሁሉ እነ የታዬ ደንደአ የዘር ማጥፋት ዘመቻ በልቶ ሳይጨርሰው በአንድ ላይ ሆኖ ለጋራ አገር ሲል ርስቱ ፈልሶ ዝም ብሎት የኖረውን በወረራ የተወሰደበትን የአባቶቹን ምድር ወደባለቤቱ እንዲያስመልስ ጉልበት እየሆኑት ይገኛሉ! Filed in:Amharic

