March 18, 2019
Source: https://mereja.com/amharic/v2/101596

በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ሚካኤል አከባቢ የቦሌ ቄሮዎች ነን በሚሉ በቁጥር 200 የሚደርሱ ወጣቶች እና በአከባቢው ወጣቶች መካከል ከትላንት ጀምሮ አለመግባባት ነበር፡፡ ነገሩ እየተባባሰ ሄዶ ዛሬ ወደ ኣላስፈላጊ ግጭት አምርቷል፡፡
ራሳቸውን የቦሌ ቄሮዎች በማለት ከሚገልፁት ወጣቶች መካከል አንዳንዶቹ የስለት መሳሪዎችን (ሜንጫና ገጀራ) በመያዝ በአከባቢው ወጣቶች ላይ ድብደባና ማስፈራሪያ ፈፅመዋል፡፡ ይህን ተከትሎ ፖሊስ በአከባቢው ደርሶ ወጣቶቹን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ታውቋል::
የአከባቢው ወጣቶች ከቄሮዎች ጋር ግጭት ውስጥ ከመግባት አልፈው በአከባቢው በሚገኘው የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ህንፃና (ሰራተኞች) ላይ ጥቃት ፈፅመዋል፡፡ (ስዩም ተሾመ)
