March 18, 2019
ከሀሰት ዜና እና ከጥላቻ ንግግሮች ህብረተሰቡ እንዲቆጠብ የጠቅላይ ሚንስትር ፅህፈት ቤት አሳሰበ

በዚህ የለውጥ ወቅት ግጭት በመቀስቀስ እና ብጥብጥ በማንገስ የህዝብ መፈናቀል እና ስቃይን ለማባባስ ከፍተኛ ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑን ፅህፈት ቤቱ አስታውቋል::
አንዳንድ ሀላፊነት የጎደላቸው ግለሰቦች በተለይም በማህበራዊ ሚዲያዎች የግለሰቦችን እና የድርጅቶችን የሀሰት ስም በመጠቀም እና በምስልም በማጀብ የሀሰት ዜናዎች እና የጥላቻ ንግግሮችን በስፋት በማሰራጨት ስሜት በመኮርኮር ላይ እንደሚገኙም ተገልጿል::
ይህንን የታቀደ እና የተደራጀ ዘመቻ ዓላማ ያልተረዱ ወገኖች ተነካብኝ ያሉትን ወገን ሳያጣሩ በሚሰጡት አፀፋ ምላሽ ወደ ግጭት ሲያመሩ እና ሲተናኮሱ ይስተዋላል::
ይህንን የሚሰሩ እና የሚቆሰቁሱ ደግሞ በሞቀ ቤታቸው ሆነው ሌላ ብጥብጥ ይጠነስሳሉ ::
ስለሆነም በግጭት እና ብጥብጥ ፀብ በመፍጠር የአመራሮችን እና የድርጅቶችን ስም በመጠቀም፣ ብሄር፣ ፆታ እና ቦታ በመቀየር የግጭት ድግስ የሚደግሱ የተበራከቱ በመሆኑ ማጣራት፣ መመርመር እና ማስተዋል የወቅቱ የሰላም ቁልፍ ነው::
የጠቅላይ ሚንስትር ፅህፈት ቤት
► መረጃ ፎረም – JOIN US
