ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀር
አኩሪ ታሪካቸው!!!!!!!
ዘርዓብሩክ አበበ ማን ነው??

ማሳሰብያ፤..…ስለ ዘርዓ ብሩክ አበበ ተጨማሪ ታሪክ ያላችሁ ትልኩልን ዘንድ እንጋብዛችኋለን
ዘርዓብሩክ ለውድ ኢትዮጵያ ሀገራቸውና ለሕዝቧ ሲሉ ከኢሕ አፓ ጎን ተሰልፈው መስዋዕት ከሆኑት ወጣት ጀግኖች አንዱ ነው ። ዘር ዓብሩክ ለትምህርት ከሄደበት ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ኢሕአሠን ከተቀላቀሉትና ስልጠና ከወሰዱት ከመጀመርያው ቡድን አንዱ ነበር። እንደሱ ጓዱ መሀመድ ማህፉዝ በበረሃ ጉዞ ላይ ሕይወቱ ያለፈ ሲሆን ዘርዓብሩክ ግን ወደ አሲምባ መግባት ያላቻለበት ምክንያት ሌላ ነበር ። በትውልዱ ኤርትራዊ በመሆኑ በእኛ ስር ይታገል እንጂ ወደ ኢትዮጵያ አናሳልፈውም ብሎ ሻዕቢያ እምቢ በማለቱ ዘርዓብሩክ ከሰለጠነበት ወደ አውሮጳ መመለስ ተገዶ ነበር ። በዚህም ድርጅቱ የኢትዮጵያ ፓስፖርት አውጥቶ ወደ አዲስ አበባ በቦሌ በኩል የመለሰው ሲሆን፤ ከአዲስ አበባ በድርጅቱ መዋቅር ወደ ሠራዊቱ ተልኮ ግዳጁን ሲወጣ ቆይቷል ። በወሎ ውስጥ በተደረገው ውግያ አርሶ አደር ላይ አንተኩስም በማለት ተከበው ከተያዙት አንዱ ሲሆን ወደ አዲስ አበባ ከነውብሸት ረታና ሌሎችም ጋር አምጥተው 1969 ዓም ከ 23 የኢሕአሠ ሠራዊት አባላት ጋር ተወስደው በግፍ ተገድለዋል። በሚረሸኑበትም ወቅት የትግሉ ነው ሕይወቴን የሚለው መዝሙር እየዘመሩ እንደተረሸኑ ይነገራል። ዘርዓብሩክ ኢትዮጵያዊነቱን ኢሕአፓነቱን ቃል ኪዳኑን እንዳከበረ በጀግንነት መስዋእትነትንም ተቀብሏል።
ዘርዓብሩክ አበበ በአሁኑ ሰአት ከወያኔ ጋር እየተዋደቀ ላለው ወጣት ትውልድ አርአያና ምሳሌ ነው። በጣም እንኮራበታለን!!!!!
ነፍስ ይማር ለጀግኖቻችን!!!
የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO)ይቀጥላል !!!
