ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀር
አኩሪ ታሪካቸው!!!!!!!
ተስፋዬ አሰግድ፤ተፈሪ በርዋቅና ብርሃኑ አለማየሁ እነማን ናቸው??

ግራ ወደቀኝ ተስፋዬ አሰግድ በቅፅል ስሙ “ድብና” ( ከዚህ በፊት ከተሰዋች እህቱ ጋር ዘክሬዋለሁ) መሃከለኛው ተፈሪ በራወርቅና የመጨረሻው ብርሃኑ አለማየሁ በቅፅል ስሙ “ደርቆ”በመባል ይታወቃሉ። የሓረር ቀላድ አንባ ያንድ ሰፈር ልጆችና ከመገደላቸው በፊት ያንድ ት/ቤት (መድሃኒዓለም) ተማሪዎች ሲሆኑ፤ ባንድ አላማ ተሰልፈው በኢሕአፓነት ሲታገሉ በፋሺስቱ ደርግ በግፍ የተገደሉ ናቸው። ተስፋዬ አሰግድና ተፈሪ በራወርቅና ባንድ ላይ የተገደሉ ሲሆን ብርሃኑ አለማየሁ ከነሱ በኋላ ተገድሎ ሬሳው የት እንደተጣለ የማይታወቅ በመሆኑ እናቱ መሞቱን አላምንም ብለው ለረዢም አመታት እህህ ሲሉ እንደኖሩ ይነገራል። ሓረር መድሃኒዓለም ከመግባታቸው በፊት ሶስቱም ወጣቶች የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁት ቀሓሥ እየተባለ በሚታወቀውና ሓረር ውስጥ በሚገኘው ት/ቤት ነበር።
ተሰፋዬና ጓደኞቹ ሐረር ሚሊተሪ ፖሊስ እስር ቤት አንድላይ ታስረው በነበረበት ወቅት ማንኛውም ተጠርቶ የሚወጣ ወጣት እጣ ፋንታው መገደል ስለነበርና የነሱም የጊዜ ጉዳይ መሆኑን ስለተረዱ ለማለጥ እቅድ ያወጣሉ። የእስር ቤቱ ዘበኞች በሚዘናጉ ሰአት እየጠበቁ የእስር ክፍላቸውን ግድግዳ መቆፈር ይጀምራሉ። በየቀኑ ቀዳዳውን በጋዜጣና በቡቱቱ እየሸፋፈኑ ቁፋሮአቸውን በየግዜው ይቀጥላሉ። በመጨረሻ ግን ተነቅቶ ሊረሸኑ ችለዋል።ቀንቷቸው ቢወጡ ኖሮ ቦታው ለመቆራ ወንዝ ቅርብ ነበርና በዚያ አቆራርጠው ወደ ጉርሱም ከዚያም በቶጎ ጫሌ በኩል ወደ ሶማልያ ለመሄድ እንደነበር ይነገራል።
ተስፋዬ አሰግድ፤ተፈሪ በርዋቅና ብርሃኑ አለማየሁ በአሁኑ ሰአት ከዘረኛው ወያኔ ጋር እየተዋደቀ ላለው ወጣት ትውልድ አርአያና ምሳሌ ናቸው። ነፍስ ይማር በጣም እንኮራባቸዋለን!!!!!
የደርግና የወያኔ ወንጀለኞች ለፍርድ እስኪቀርቡ ትግላችን ይቀጥላል!!
አንድነት ሃይል ነው! ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!!!
የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO)ይቀጥላል !!
