ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀር
አኩሪ ታሪካቸው!!!!!!!
ባቢሌ ኅይለ ስላሴ ማን ነው??

“የባቢሌ ኅይለ ስላሴና የጓዶቹን መገደል የሰማሁት እኔም በዚሁ እንቅስቃሴ በድሬ ደዋ አካባቢ ተሳትፎዬ ለእስር ተዳርጌ በጂጂጋ ወህኒ ቤት ውስጥ ራድዮ ሳዳምጥ ነው። ከዚያ ግዜ ጀምሮ ባቢሌ ኅይለ ስላሴ የሚለው ስም በውስጤ ተቀርፆ እስከለተ ሞቴም አብሮኝ የሚኖር ስም ነው።”
የ 14 አመቱ ባቢሌ ኅይለ ስላሴ፤ የመጀመርያው ኢሕአፓን የማስተዋወቅ ሃገራዊ እንቅስቃሴ ላይ ተሳትፈሃል በመባል በፋሺስቱ መንግስቱ ኅ/ማርያም የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው በግፍ ከተገደሉት ወጣቶች አንዱ ነበር። ባጠቃላይ በኢትዮጵያ ከተሞች ውስጥ በተካሄደው በዚህ ሰላማዊ ትግል ላይ የተሳተፉትን ለውጥ ፈላጊ ወጣቶች ቅስም ለመስበርና ለሌላውም መቀጣጫ ይሆናሉ በሚል ፋሺስታዊ አስተሳሰብ፤ እነኚህን ጫቅላ ወጣቶች ” የፍየል ወጠጤ” አዘምሮና በህዝብ መገናኛ በሬድዮና በቴሌቪዥን እያስተላለፈ መፎከሩ ምን ያህል ፈሪና ፀረ ህዝብ መሆኑን ያረጋገጠበት ወቅት ነበር።
በሰላማዊ መንገድ ወረቀት በመበተን፤ ቀለምና ብሩሽ መሳርያቸው አድርገው ወቅታዊ መፈክሮችን ግርግዳዎች ላይ ለመፃፍና የህዝብን ድምፅ ለማሰማት የወጡ ሰላማዊ ወጣቶችን በግፍ የገደለ ፋሺስት ደርግ ኢሕአፓ ስለተኮሰብኝ ነው መግደል የጀመርኩት እያለ እስካሁን ድረስ በተላላኪዎቹ ሲዋሽና ሲቀጥፍ በጣም ይዘገንናል።
ይሄንንም ተግባራዊ ለማድረግ፤ ሕዳር 7 ቀን 1969 ዓም አራት ኪሎ ቤተመንግስት በደርግ ስብሰባ አዳራሽ ጠቅላላ ስብሰባ ተቀምጠው ሰው ለመግደል ተስማምተው ፀረ ሕዝብና ኢሕአፓ በማለት በተለይም ከከፍተኛ 3ና በአካባቢው ከዚህ የሚከተሉትን የሕዝብ ልጆች ባቢሌ ኅይለ ስላሴን ጨምሮ፤ ለደርግ ዘመቻና ጥበቃ መምሪያ ተእዛዝ ሰጥተው አዲስ አበባ ውስጥ ባልታወቀ ቦታ ጀግኖቻችንን ረሽነው ጥለዋል።
መኮንን ወዳጆ
ዳንሄል ኃይሌ
ውብሸት ሰይፉ
ተስፋዬ ሁንዴ
ንጋቱ ተሰማ
አሉላ ደበሳይ
ክፍሉ የማነ ብርሃን
ይስሐቅ ቢተውልኝ
አበበ ዋቄ
ደጀኔ ሰብስቤ
ጫን ያለው ካሣ
ደጀኔ በርሔ
ኢዮብ ገለሴ
ተሾመ አሰፋ
ታደለ እጅጉ
ኃይሌ ወልዴ ራህመቶ
ምትኩ ረመቹ
ተስፋ ማርያም ተስፋ ጋብር
ተስፋዬ ዳኜ
ክንፈ ዋቄ
ጌጡ አበኔ
አዳነ በቀለ
ለማ አበበ
ባቢሌ ኃይለ ሥላሴ
ተከስተ ወልደ ስላሴ
ግርማ ሰለሞን
ግርማ ቶሎሣ
ይሄንን አረመኔ ፋሺስት ደርግ ነው ያሁኖቹ የድል አጥቢያ አርበኞችና የወያኔ አጋፋሪዎች አገርወዳድ የሚሉን!!
ባቢሌ ኅይለ ስላሴ በአሁኑ ሰአት ከወያኔ ጋር እየተዋደቀ ላለው ወጣት ትውልድ አርአያና ምሳሌ ነው። በጣም እንኮራበታለን!!!!!
ነፍስ ይማር ለጀግኖቻችን!!!
የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO)ይቀጥላል !!!
