March 19, 2019
Source: https://mereja.com/amharic/v2/101948

የባልደራስ ህዝባዊ ስብሰባ ውሳኔ፣ ለአብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ ለአቶ ለማ መገርሳ እና ለአቶ ታከለ ኡማ ተላከ።
መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም በባልደራስ አዳራሽ ውይይት በህዝብ ከተሰጠ የአቋም መግለጫ መካከል አንዱ የሆነው፣ በአዲስ አበባ ከተማና በኦሮሚያ ክልል መስተዳድሮች መካከል ስላለው የወሰንና የሚደረጉ ሰፈራዎችን በተመለከተ “የሚቀጥለው ምርጫ ተደርጎ በሁለቱም በኩል በህዝብ የተመረጡ መስተዳድሮች እስኪሰየሙ ድረስ የአስተዳደር ወሰን ድርድር ሆነ የሰፈራ እቅድ ተግባራዊ እንዳይሆን” የሚል ነበር።
ይሄም የአቋም መግለጫ ሀሳብ እንዳይተገበርና በአጭር ጊዜ ውስጥም ምላሻችሁን እንዲያሳውቁ በማለት፤ የአዲስ አበባ ባለአደራ ም/ቤት በዛሬው ዕለት (መጋቢት 10 ቀን 20011 ዓ.ም) ለጠ ሚ ጽ/ቤት፣ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማ እና ለኦሮሚያ ክልል ፕሬዚደንት አቶ ለማ መገርሳ ደብዳቤ በመጻፍ በፓስታ ቤት በኩል በአስቸኳይ ተልኳል።


በአዲስ አበባ ነዋሪ፣ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም በባልደራስ አዳራሽ በህዝብ ድምጽ ከተወሰኑ አራት አንኳር ጉዳዮች መካከልም አንዱ፣ በአዲስ አበባ ከተማ እና በኦሮሚያ ክልል የወሰን ድርድር የተመለከተ እንዲሁም አዲስ የሰፈራ ዕቅድ ትግበራ መሆኑ የሚታወስ ነው።
የአዲስ አበባ ባለአደራ ም/ቤት (ባልደራስ)
መጋቢት 10 ቀን 2011 ዓ.ም
አዲስ አበባ
