March 19, 2019

የፖለቲካ ፍላጎት እንደሌለው የሚናገረው ንቅናቄው አዲስ አበባ የመላው ኢትዮጵያዊያን እና የአፍሪካ መዲና መሆኗን ስለምናም ለሁለንተናዊ እድገቷ እና ለህዝቦቿ ጥቅም እንጮሃለን ብሏል፡፡ አዲስ አበባ የኢትዮጵያዊነት ማሰሪያ ውል ነች የሚለው ንቅናቄው በመላው ዓለም የሃሳቡ ተጋሪ ከሆኑት ጋር በጉዳዩ ላይ ጠንክሮ እንደሚሰራ አስታውቋል።

https://youtu.be/9Xi3sjgAU4I
https://youtu.be/9Xi3sjgAU4I

«አዲስ አበባን እና ሰማይን የኔ ነው» የሚልን አንቀበልም ሲል አዲስ አበባ ለኢትዮጵያዊያን ንቅናቄ ለ«DW» ተናገረ፡፡ ምንም አይነት የፖለቲካ ፍላጎት እንደሌለው የሚናገረው በቅርቡ የተቋቋመው ይኽው ንቅናቄ አዲስ አበባ የመላው ኢትዮጵያዊያን እና የአፍሪቃ መዲና መሆኗን ስለምናምን ለሁለንተናዊ እድገቷ እና ለህዝቦቿ ጥቅም እንጮሃለን ብሏል፡፡ አዲስ አበባ የኢትዮጵያዊነት ማሰሪያ ውል ነች የሚለው ንቅናቄው በመላው ዓለም የሃሳቡ ተጋሪ ከሆኑት ጋር በጉዳዩ ላይ ጠንክሮ እንደሚሰራ አስታውቋል።