March 22, 2019
Source: https://mereja.com/amharic/v2/103054

አቶ በቀለ ገርባ የኦፌኮ ም/ሊቀመንበርና በኦሮሞ ፖለቲካ ውስጥ በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ ፖለቲከኞች መካከል አንዱ ናቸው። ትውልዳቸው በወለጋ ሲሆናሁ አሁን ነዋሪነታቸው በአዳማ/ናዝሬት ነው። አቶ በቀለ ፣ ከኦሮሞ ሜዲያ ኔትዎርክ ስራ አስኪያጅ ጃዋር መሐመድ ጋር በቅርበት የሚሰሩ የለማ ቲም ስልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ በለማ ቲም ደስተኛ አለመሆናቸውን ብዙ ጊዜ ሲናገሩ የሚደመጡ ናቸው።
ልክ እንደ አቶ በቀለ የወለጋ ተወላጅ የሆኑና ኦሮምኛን አቀላጥፈው የሚናገሩ ዶ.ር አብርሃም አለሙ ፣ የአቶ በቀለ የኦሮምኛ ንግግር እንደሚከተለው ተርጉመው አቅርበዉልናል።
——————————-
ስለ ኦሮሞ ቋንቋና ባህል እድገት – በኦሮሞ ባህል ማእከል የተካሄደ የፓነል ውይይት
አዲስ አበባ፣ 08/07/2011
የኦሮሞን ቋንቋና ባህል አዲስ አበባ ውስጥ ማሳደግን ዐቢይ ዓላማው አድርጎ የተቋቋመው የኦሮሞ ቋንቋና ባህል ቦርድ፣ ምሁራንና የማህበረሰቡን ልዩ ልዩ አካላት ያሳተፈ የፓነል ውይይት በአዲስ አበባ የኦሮሞ ባህል ማእከል በ 08/07/2011 አካሂዷል፡፡ …..
በውይይቱ ላይ ንግግር ያቀረቡት የፖለቲካ መሪና የቋንቋ ባለሙያ የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ፣ “የኦሮሞ ቋንቋ ጉዳይ፣ የኦሮሞ ማንነት ጉዳይ ነው፤” አሉ፡፡
ቋንቋ የሌለው ህዝብ (ማህበረሰብ) የለም፡፡ አንድ ማህበረሰብ እንደ ማህበረሰብ አለ፣ እከሌ የሚባል ማህበረሰብ ነው ተብሎ ከሚታወቅበትም ነገር አንዱ ትልቁ ቋንቋው ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ያን ማህበረሰብ እንዳይኖር ሲፈልጉ፣ አስቀድመው ቋንቋውን ይገሉታል፤ ቋንቋውን ይገሉታል፡፡ እንዲህ ነው የሚሉት፤ መፈክራቸውም እንዲህ ነው፤ “ቋንቋውን ግደል፤ ከዚያም ቀጥለህ ሰውዬውን ግደል፤” ይላሉ፡፡ በዚህ ምክኛት የራስን ቋንቋ መጠበቅ፣ መንከባከብ፣ የራስን ማንነት መጠበቅ ማለት እንደሆነ ይታወቃል ማለት ነው፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞFiled in:Amharic
