1. በዘረኝነትና በጥላቻ ምክንያት የወገኖቻችን መገደል፣ የቤት ንብረታቸው መዘረፍና መቃጠል፣ ከቀያቸው መፈናቀልና በሀገራቸው ስደተኛ መሆናቸው በአስቸኳይ እንዲቆም የተፈናቀሉት ወደቀድሞ መኖሪያቸው እንዲመለሱ፣ ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ መንግሥት ሕግን የማስከበር ኃላፊነቱን እንዲወጣ እንጠይቃለን፣
2. ዘረኝነትንና ጥላቻን ከሚያራምዱ ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች ጋር የሃሳብ ፍልሚያ በማድረግ ጊዜ ያለፈበት የፖለቲካ መስመር መያዛቸውን ለማሳወቅ በሰላማዊ መንገድ እንሠራለን፣
3. ዘረኝነትንና ጥላቻን ለማስወገድ በምንወክለው ሕዝብ መሃል የመከባበርንና የአብሮነትን ፖለቲካ ለማስረጽ ሌትና ቀን ለመሥራት ዝግጁ መሆናችንን እንገልጻለን፣
4. ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ውስጥ በመረጡት ቦታ የመኖር፣ በፈለጉት የሥራ መስክ የመሰማራት፣ የመንቀሳቀስ እና ሃብት የማፍራት መብታቸው እንዲከበር እንሠራለን፣
5. አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳትሆን የመላው አፍሪካውያንም ከተማ ነች። በመሆኑም በአዲስ አበባ ላይ የሚነሳን የተናጠል የባለቤትነት ጥያቄ አጥብቀን እንቃወማለን። በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚነሱ የሕዝብ ጥያቄዎችን መንግሥት ዴሞክርሲያዊ በሆነና የከተማዪቱ ኗሪ የሆነውን ሕዝብ ይሁንታ ባገናዘበ መልኩ እንዲያስተናግድ አጥብቀን እንጠይቃለን፣
6. የኢትዮጵያ ህዝብ የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠል ይቻል ዘንድ ከለውጥ አራማጆቹ ጎን እንዲቆምና ለውጡ ፈር እንዳይስት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ፣ ስህተቶች ሲኖሩ እንዲቃወም፣ በአጠቃላይ የሸበበውን ዝምታ እንዲሰብርና የፖለቲካ ተሳትፎውን እንዲያሳድግ በፓርቲዎች ዙሪያ እንዲሰበሰብ እንጠይቃለን፣
7. የአገራችንም ሆነ የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ያለአንዳች ማጋነንና ማቃለል ለኢትዮጵያ ሕዝብም ሆነ ለዓለም ኅብረተሰብ በማሳወቅ በመንግሥት ላይ ተጽዕኖ እንዲያሳድር እንጠይቃለን።
8. መገናኛ ብዙሃን ፍቅርንና መተሳሰብን፣ አብሮ የመኖርን ሀገራዊ ጠቀሜታ እንጂ ዘረኝነትንና ጥላቻን እንዳያራግቡ በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም እንጠይቃለን።
9. አቅማችንን አጠንክረን የፖለቲካ ሥራዎቻችንን በማፋጠን ተፎካካሪ የሆንነው የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁላችንም መጋቢት 5 ቀን 2011 ዓ.ም. የፈረምነውን የቃልኪዳን ሰነድ በማክበር ለመሥራት በሙሉ ልብ እንድነሳሳ ጥሪያችንን ለሁሉም ፖለቲካ ፓርቲዎች እናቀርባለን።
ኢትዮጵያ በአንድነቷ ተከብራና ተጠብቃ ለዘላለም ትኑር!!!
አዲስ አበባ

የፍትኅና ዴሞክራሲ ለኢትዮጵያ ሥርየት (ሥርየት) አባል ድርጅቶችም፦
1. የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣
2. የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)፣
3. የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኅብረት (ኢዴኅ)፣
4. የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ (ኢብአፓ)፣
5. የአፋር ሕዝቦች ፍትሃዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አሕፍዴፓ)፣
6. የአፋር ሕዝብ ነፃነት ፓርቲ
7. የኦሮሞ ነጻነት ንቅናቄ