የዓለማችን ጦር መሳርያ ሽያጭ አገሮች

March 12, 2024 – DW Amharic  የጎርጎረሳዉያን 2023 ዓመት የዓለም የጦር መሳርያ ዝዉዉርና ሽያጭን በተመለከተ፤ በዓለማችን የጦር መሳርያ ንግድ ዩናይትድ ስቴትስ አንደኛ፤ በሁለተኛ ፈረንሳይ ፤ ሦስተኛ ሩስያ፤ አራተኛ ቻይና፤ አምስተኛ ጀርመን ስድስተኛ ጣልያን ፤ ሰባተኛ ኢጣልያ ፤ እንዲሁም ስምንተኛ ታላቅዋ ብሪታንያ መሆናቸዉ ዓለም አቀፉ ተቆጣጣሪ ተቋም አስታወቀ።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የዐማራ አጠቃላይ ጉባዔ በአትላንታ

March 12, 2024 – DW Amharic  ዐማራው በአሁኑ ጊዜ ከሁሉም የከፋ ጥቃት እየረሰበት ነው ያሉት ሊቀመንበሩ፣ዓለም አቀፉ ማኀበረስብ ግን ለዚህ በደል ትኩረት አለመስጠቱን አመልከተዋል። በዚህ ላይም ውይይት መካሄዱንም አመልክተዋል።የመጀመሪያ የዐማራ አጠቃላይ ጉባኤ የዛሬ ዓመት ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ዘንድሮ ደግሞ በዐማራ ማኀበር አስተናጋጅነት በአትላንታ ጆርጅያ ተካሄዷል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የሲቪክ ድርጅቶች ስለ የሽግግር ፍትሕ ረቂቅ ፖሊሲ

March 12, 2024 – DW Amharic  በአሁኑ ወቅት በርካታ የአገሪቱ ክፍሎች በማያባራ ግጭት ውስጥ መሆናቸውን የጠቀሱት ድርጅቶቹ መንግሥት ሕግና ሥርዓት የማስከበር ግዴታውን በአግባቡ ካልተወጣ በስተቀር የሽግግር ፍትሕን ተግባራዊ ለማድረግ በጣም አዳጋች እንደሚሆን አመላክተዋል፡፡ቀውሱ ለሽግግር ፍትሕ አፈጻጸምም እንቅፋት እንዳይሆኑ፣ መንግሥት የሕግ የበላይነትን እንዲያረጋግጥ ጠይቀዋል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የኢትዮጵያ ጥልፍልፍ ቀዉሶች

March 12, 2024 – DW Amharic  ምክንያቱ ምንም ሆነ ምን የአዲስ አበባና የመቀሌ መሪዎች ኃላፊነት እንደሚሰማዉ ፖለቲከኛ ትግራይ፣ አማራ ይሁን ኦሮሚያ ክልሎች የሚያልቀዉን ሰዉ ሕይወት ማደን አይደለም ዉዝግባቸዉን እንኳን ራሳቸዉ ማስወገድ አቅቷቸዉ እንደሚያዉቁና እንደለመዱት የአሜሪካ-አዉሮጳና አፍሪቃን ሽምግልና እየተማጸኑ ነዉ።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የረመዳን ጾም መጀመርን በማስመልከት የተላለፉ የሰላም ጥሪዎች

March 12, 2024 – DW Amharic  የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ዛሬ ሰኞ የጀመረዉን የረመዳን ጾምን በማስመልከት በእስራኤል-ሀማስ መካከል ጋዛ ሰርጥ ዉስጥ የሚካሄደዉ ጦርነት ብሎም በሱዳን የሚታየዉ ግጭት እንዲቆም እና እርቅ እንዲወርድ ጥሪ አስተላለፉ። ጉቴሬዝ በሃማስ የተያዙ የእስራኤል ታጋቾች እንዲፈቱም ጠይቀዋል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ