ሶማሊያ ውስጥ ቢያንስ ሰባት ኢትዮጵያውያን ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገደሉ

6 የካቲት 2024 በደቡባዊ ሶማሊያ በምትገኘው ጌዶ ክልል ውስጥ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ቢያንስ ሰባት ኢትዮጵያውያን ሲገደሉ በርካቶች ስጋት ውስጥ መሆናቸው ተገለጸ። በሶማሊያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ተወካይ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ሶማሊያ ከኬንያ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው በለደሀዎ ከተማ በተፈጸመው ኢትዮጵያውያን ስጋት ላይ እንደሆኑና በርካቶች ወደ አገር ቤት መመለስ ይፈልጋሉ ብለዋል። ታጣቂዎቹ ሌሊት በጌዶ ክልል በለደሀዎ በተባለ ወረዳ […]

“ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር የመዋጋት ፍላጎት የላትም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

ከ 8 ሰአት በፊት የኢትዮጵያ መንግሥት ከሶማሊያ ጋር ጦርነት ውስጥ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህንን ያሉት ዛሬ ማክሰኞ ጥር 28/2016 ዓ.ም ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ እና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ውሏቸው ከሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቤሂ ጋር ከአንድ ወር በፊት የተፈራረሙት የባሕር […]