እስራኤል በጋዛ የሕክምና ባለሙያዎች ላይ ያደረሰችውን ጥቃት የሚሞግተው ተጎጂ

ከ 8 ሰአት በፊት “ባልደረቦቼ ላይ የተፈፀመውን በዐይኔ ያየሁ ብቸኛ ተጎጂ ነኝ” ይላል ሙንተር አቤድ በእጅ ስልኩ ላይ የባልደረቦቹን ፎቶግራፍ እየተመለከተ። ከሳምንት በፊት በጋዛ 15 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በእስራኤል ጥቃት ሲገደሉ በአምቡላንሱ ወለል በመወርወር ሕይወቱ ተርፏል። ከፊት የነበሩ ሁለቱ ባልደረቦቹ በተተኮሰባቸው ጥይት ተገድለዋል። “ረፋድ አካባቢ ከዋና መስሪያ ቤታችን ተነሳን” የሚለው ሙንተር፤ የፍልስጤም ቀይ ጨረቃ፣ የጋዛ […]