የቤንዚን የችርቻሮ ዋጋ በ11 ብር ጨመረ

24 መጋቢት 2025 የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ትናንት ይፋ ባደረገው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ጭማሪ የአንድ ሌትር ቤንዚን ዋጋ 112 ብር ከ67 ሳንቲም ደረሰ። የነጭ ናፍጣ ዋጋ ደግሞ የዘጠኝ ብር ገደማ ጭማሪ ተደርጎበታል። ከእሁድ መጋቢት 14/2017 ዓ.ም. ምሽት ጀምሮ ተግባራዊ መሆን የጀመረው የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ማሻሻያ በዚህ ዓመት ለሶስተኛ ጊዜ የተደረገ የመሸጫ ዋጋ ጭማሪ […]