የኢትዮጵያ መንግሥት አንደኛው የህወሓት ክንፍ ከውጭ ኃይሎች ጋር ግንኙነት አለው ሲል ከሰሰ

ከ 8 ሰአት በፊት የኢትዮጵያ መንግሥት አንደኛው የህወሓት ክንፍ የአገሪቱ ተቀናቃኝ ከሆኑ የውጭ ኃይሎች ጋር ግንኙነት እና ትብብር አለው በማለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከሰሰ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጤሞቲዮስ ይህንን ያሉት አርብ አዲስ አበባ ውስጥ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር በክልሉ ስላለው ሁኔታ ለዲፕሎማቶች ማብራሪያ በሰጡበት ጊዜ ነው። ሚኒስትሩ ይህንን እና ሌሎችንም ክሶች […]

የዩኬ ዜጋ በኬንያው ፕሬዝዳንት ሩቶ አጃቢዎች ተገጭቶ ተገደለ

14 መጋቢት 2025, 14:44 EAT በናይሮቢ መንገድ ላይ እየተጓዘ የነበረ የዩናይትድ ኪንግደም ዜጋ በኬንያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ አጃቢዎች ተገጭቶ መገደሉ ተገለጸ። ኤድጋር ቻርልስ ፍሬድሪክ የተባለው የ79 ዓመት ግለሰብ ሐሙስ ዕለት ንጎንግ ሮድ የተባለ አካባቢ ተገጭቶ ነው ሕይወቱ ያለፈው። አንድ አሽከርካሪ በፖሊስ ተይዞ የነበረ ቢሆንም በዋስ ተለቋል። የፕሬዝዳንት ሩቶን መኪና አጅበው ሲጓዙ ከነበሩ ተሽከርካሪዎች አንዱን እየነዳ […]

የኡጋንዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ‘ከአገራቸው አታልለው ያመጧትን” ወጣት በዩኬ በባርነት በማሰራት ጥፋተኛ ተባሉ

14 መጋቢት 2025, 13:56 EAT የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንዲሁም የኡጋንዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ከአገራቸው ወደ ዩናይትድ ኪንግደም “አታልለው ያመጧትን” ወጣት በመኖሪያ ቤታቸው በባርነት እንድትሰራ በማስገደድ ወንጀል ጥፋተኛ ተባሉ። ሊዲያ ሙጋምቤ የተሰኙት ዳኛ “ያላቸውን ስልጣን በመጠቀም” ወጣቷን ቋሚ ስራ እንዳትሰራ በመከልከል “በነጻ የቤት ሰራተኛዋ እንዲሁም ለልጇም እንክብካቤ እንድታደርግ” ማስገደዳቸውን አቃብያነ ህግ አስረድተዋል። በኡጋንዳ የከፍተኛ ፍርድ […]