በአማራጭነት ከቀረበው የጂቡቲው ታጁራ ወደብ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥያቄዎች

ከ 5 ሰአት በፊት ኢትዮጵያ ራሷን በነጻ አገርነት ካወጀችው ሶማሊላንድ ጋር በፈረመችው የባህር በር መግባቢያ ስምምነት የተነሳ ከሶማሊያ ጋር የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ እንዲሁም የኢትዮጵያን የባህር በር መዳረሻ ችግር ለመቅረፍ በሚል ጂቡቲ አማራጭ ያለችውን ሀሳብ ያቀረበችው ባለፉት ሳምንታት ነበር። የጂቡቲው ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ማህሙድ አሊ ዩሱፍ፣ ቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ላይ በቀረቡበት ወቅት፣ የታጁራ ወደብን ኢትዮጵያ […]

ዶ/ር አሸብርን ጨምሮ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቲ አመራሮች በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ክስ ተመሰረተባቸው

ከ 2 ሰአት በፊት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቲ ፕሬዝዳንት [ዶ/ር] አሸብር ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ አራት አመራሮች በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ሌሎች ተያያዝ ጉዳዮች ክስ ተመሰረተባቸው። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቲም ከተከሳሾቹ መካከል ነው። ክሱን የመሰረቱት ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ አትሌት ገዛኸኝ አበራ፣ የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን እና የኢትዮጵያ ቴኒስ ፌዴሬሽን ናቸው። በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት […]