ከኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ማበረታቻ ጎን ለጎን ዋጋቸውና ጥራታቸውም ይታሰብበት!
APRIL 28, 2024 ናታን ዳዊት መንግሥት በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች እንዳይገቡ በተለያዩ መንገዶች ክልከላ እያደረገ ነው፡፡ በአንጻሩ በነዳጅ ከሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ይልቅ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች እንዲገቡ ማበረታቻዎችን እየሰጠ ነው፡፡ የገቢዎች ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በተለይ ሙሉ በሙሉ ተበትነው የሚመጡ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በአገር ውስጥ ሲገጣጠሙ የማኅበራዊ ዋስትና ከሚባለው የሦስት በመቶ ታክስ ውጪ ከታክስ ነፃ ናቸው፡፡ በቀጥታ የሚገቡ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች […]
መንግሥት የሪል ስቴት ንብረት ታክስና የተሽከርካሪ ዝውውር ታክስ ለመጣል አቀደ
ዜና መንግሥት የሪል ስቴት ንብረት ታክስና የተሽከርካሪ ዝውውር ታክስ ለመጣል አቀደ ዮሐንስ አንበርብር ቀን: April 28, 2024 መንግሥት የአገሪቱን የታክስ ገቢ ለማሳደግ የሪል ስቴት ንብረት ታክስና የሞተር ተሽከርካሪ ዝውውር ታክስ ለመጣል ማቀዱ ታወቀ። መንግሥት ሁለቱንም አዲስ ዓይነት ታክሶች ከዘንድሮ ጀምሮ እስከሚቀጥለው ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ለመጣል ያቀደ ሲሆን፣ ይህንን ዕቅዱንም በሁለተኛው አገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም […]
ከአይኤምኤፍ ጋር የሚደረገው ድርድር ብቃትና ብልኃት ይታከልበት!
April 28, 2024 ርዕሰ አንቀጽ ሰሞነኛው የመንግሥትና የዓለም ገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) በአሜሪካ የተደረገ ንግግር፣ የተለያዩ ዓውዶችንና ገጽታዎችን ተላብሶ ብዙ ሲባልበት ሰንብቷል፡፡ መንግሥት ከአይኤምኤፍም ሆነ ከሌሎች ድጋፍና ብድር ለማግኘት እያደረገ ስላለው ጥረት፣ የብርን የመግዛት አቅም የበለጠ እንዲያዳክም ጥያቄ እንደቀረበለትና ሌሎች ተያያዥ ነጥቦች በየተራ መነጋገሪያ ነበሩ፡፡ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው እንደሚያስረዱት ደግሞ፣ እነ አይኤምኤፍ የመንግሥት ሥጋት ያጠላበት ወጪና […]
ልንዘነጋው የማይገባንና የዘነጋነው የአፍሪካ ቀን
ቀን: April 28, 2024 በአሮን ሰይፉ የሰው ዘር መገኛ የሆነችውና የቀደምት ሥልጣኔዎች ባለቤት የሆነችው አፍሪካ በተለያዩ የታሪክ ዑደቶች ውስጥ ያለፈች አኅጉር ናት፡፡ በረዥሙ የአፍሪካ ታሪክ ውስጥ ታላላቅ ሥልጣኔዎችን፣ የንግድ ልውውጦችን፣ የትምህርትና የባህል በረከቶቿ እንደሚነሳው ሁሉ በአሥር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወጣት አፍሪካውያንን ለባርነት አትላንቲክ ውቅያኖስን አቋርጠው ወደ አውሮፓና አሜሪካ መጫናቸው፣ እንዲሁም በአውሮፓውያን ቅኝ ግዛት ሥር የመውደቅ ጨለማ […]
አገር ባለውለታነቷን የምታረጋግጥበት ሥርዓታችንን እንፈትሽ!
ተሟገት አገር ባለውለታነቷን የምታረጋግጥበት ሥርዓታችንን እንፈትሽ! አንባቢ ቀን: April 28, 2024 በገነት ዓለሙ በሕግ አምላክ እያለ የሚማጠነው ፖለቲካችን፣ ሰላማችን በአጠቃላይ አኗኗራችን ሁሉ ሕግ ማክበርን፣ ለሕግ መገዛትን የግድ እንደሚጠይቅ ሳይታለም የተፈታ በየትም አገር የታወቀ እውነት ነው፡፡ ባለፈው ሳምንት ጽሑፌ እንደጠቆምኩት ሕጋዊና ቀጥተኛ መንገዶች እንዲታመኑና እንዲመረጡ፣ ዘወርዋራ፣ መሠሪና ሕገወጥ መንገዶች እርም እንዲባሉ፣ በየትኛውም ዘርፍ ያለው ሕይወት በተገኘው […]
የአዲስ አበባ ከተማ ፈቃድ ሰጪ ተቋማት ተናበው ስለማይሠሩ ነዋሪዎች እየተንገላቱ መሆኑ ተነገረ
ማኅበራዊ የአዲስ አበባ ከተማ ፈቃድ ሰጪ ተቋማት ተናበው ስለማይሠሩ ነዋሪዎች እየተንገላቱ መሆኑ ተነገረ አበበ ፍቅር ቀን: April 28, 2024 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ተቋማት በማይመለከታቸው ሥራ ፈቃድ በመስጠታቸው፣ ቁጥጥር በማድረጋቸውና በመመርያ መሠረት ተናበው ባለመሥራታቸው ኅብረተሰቡን ለእንግልት እየዳረጉ መሆናቸው ተገለጸ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ሚያዝያ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. ላለፉት ዘጠኝ ወራት […]
ለከፋ የጤና ዕክል የሚዳርገው የፅንስ ኅብረሰረሰር ዘንግ ክፍተት
ማኅበራዊ ለከፋ የጤና ዕክል የሚዳርገው የፅንስ ኅብረሰረሰር ዘንግ ክፍተት የማነ ብርሃኑ ቀን: April 28, 2024 በቅድመ ወሊድ ወቅት የሚከሰት የኅብረሰረሰር ዘንግ ክፍተትና የጭንቅላት ውኃ መቋጠር ሕፃናት ከተወለዱ በኋላ ለከፍተኛ የጤና እክል የሚያጋልጥ ነው፡፡ ፅንሱን ለዚህ ጉዳት የሚዳረገው ደግሞ የምግብ ንጥረ ነገሮች በተለይም የፎሊክ ኢሲድ እጥረት ነው፡፡ የበሽታው ተጠቂ ሕፃናት የመንቀሳቀስ እክል፣ የስሜት ማጣት፣ የአዕምሮ ውስንነት፣ […]
‹‹ብሪክስ ኢትዮጵያ የበለጠ ጠንካራ ሆና የትኛውንም ዓይነት ጫና መቋቋም ያስችላታል›› ቪክቶሪያ ፓኖቫ፣ የሩሲያ የብሪክስ የልሂቃንና የባለሙያዎች ምክር ቤት ዋና ኃላፊ
ናርዶስ ዮሴፍ April 28, 2024 ቆይታ ቪክቶሪያ ፓኖቫ (ዶ/ር) በሩሲያ የብሪክስ የልሂቃንና የባለሙያዎች ምክር ቤት ዋና ኃላፊና በሩሲያ ኤችኤስኢ ዩኒቨርሲቲ ሥር በሚተዳደረው የአገር አቀፍ የኢኮኖሚክስ ምርምር ዩኒቨርሲቲ ምክትል ዲን ሲሆኑ፣ በትምህርታቸውም ሦስተኛ ዲግሪያቸውን በታሪክ የትምህርት ዘርፍ ያጠናቀቁ ናቸው። በሩሲያ የብሪክስ የልሂቃንና የባለሙያዎች ምክር ቤትን በሩሲያ መንግሥት ትዕዛዝ በአገሪቱ የውጭ ጉዳይና የገንዘብ ሚኒስቴር ትብብር የተቋቋመ በፖለቲካዊ፣ […]
የመጥፋት አደጋ ከተጋረጠባቸው ቋንቋዎች ውስጥ ሁለቱ በድጋሚ እንዲያገግሙ እንደሚደረግ ተገለጸ
ማኅበራዊ የመጥፋት አደጋ ከተጋረጠባቸው ቋንቋዎች ውስጥ ሁለቱ በድጋሚ እንዲያገግሙ እንደሚደረግ ተገለጸ ሰላማዊት መንገሻ ቀን: April 28, 2024 የመጥፋት አደጋ ከተጋረጠባቸው ቋንቋዎች ውስጥ የብራይሌና ባጫ ቋንቋዎችን ለመታደግና መልሶ እንዲያገግሙ ለማስቻል እየተሠራ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የ2016 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዝያ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. […]
አፈር አልሚ ኬሚካዊ ውህዶችን ከመግዛት የሚታደገው የኢትዮጵያ ኖራና ጥቅማ ጥቅሞቹ በሽብሩ ተድላ (ፕሮፌሰር ኤምሪተሰ) እና በባለሟል አጥናፉ (ዶ/ር)
አስተያየት By አንባቢ April 28, 2024 መግቢያ በአገር ቤት ቋንቋ ሳይንሳዊ ጽሑፍ ማበርከት፣ የሳይንስ ዘዴዎችንና ሳይንሳዊ ዕውቀትን ለብዙ የማኅበረሰቡ አባላት ማድረስ ይቻላል፡፡ በተጨማሪ የማኅበረሰቡን ሳይንሳዊ አስተሳሰብን፣ ብሎም ምክንያታዊነትን ያዳብራል የሚል እምነት አለን፡፡ ዕውቀትን በአገር ቤት ቋንቋ መገብየት፣ ግንዛቤውን ቀለል ተደራሽነቱን ሰፋ ያደርገዋል፡፡ የዚህች ጽሑፍ ዋና ዓላማ ሳይንሳዊ አስተሳሰብን ማኸዘብ ብሎም ሳይንሳዊ ዕውቀትን በማኅበረሰቡ አባላት ውስጥ […]