አሜሪካ በተቃዋሚዎች ላይ የሳይበር ጥቃት በፈጸሙ ቻይናውያን ጠላፊዎች ላይ ክስ መሰረተች

ከ 2 ሰአት በፊት የአሜሪካ አቃቤ ሕጎች በአገሪቱ የሚገኙ የቻይና መንግሥት ተቃዋሚዎችን መረጃ በመመንተፍ ለቤጂንግ መንግሥት በመሸጥ የተጠረጠሩ 12 ቻይናውያን ላይ ክስ መሰረቱ። የአሜሪካ ፍትህ ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያመለክተው፤ “በመንግሥት የተደገፈው” የሳይበር ጥቃት የአሜሪካ መንግሥት ተቋማት ላይም ያነጣጠረ ነበር። የአሜሪካ የሃይማኖት ተቋማት እና በሆንግ ኮንግ የሚገኝ አንድ ጋዜጣም የጥቃቶቹ ሰለባዎች መሆናቸውን የሚኒስቴሩ መግለጫ አስረድቷል። ቻይና ይህንን […]