ኢራናዊቷ የሰላም ኖቤል ተሸላሚ ተጨማሪ እስራት እንደተፈረደባት ጠበቃዋ ተናገሩ
ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ ከ 6 ሰአት በፊት የሰላም ኖቤል ሽልማት አሸናፊዋ ናርጌስ ሞሃመዲ በኢራን ፍርድ ቤት ተጨማሪ የሰባት ዓመት ከስድስት ወር እስራት እንደተፈረደባት ጠበቃዋ ተናገሩ። ሙስጣፋ ኒሊ እሁድ ዕለት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በለጠፉት መግለጫ ላይ የሰብአዊ መብት ተሟጋቿ “በመሰብሰብና በወንጀል ተግባር በመተባበር” ስድስት ዓመት፣ እንዲሁም “በፕሮፓጋንዳ እንቅስቃሴዎች” አንድ ዓመት ተኩል በሰሜን ምሥራቅ ማሽሃድ […]
የሩሲያ ከፍተኛ የጦር መኮንን ላይ ተኩስዋል የተባሉ ሦስት ተጠርጣሪዎች ተለዩ
ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ ከ 6 ሰአት በፊት የሩሲያ ከፍተኛ የጦር መኮንን የሆኑት ሌተናንት ጀነራል ቭላድሚር አሌክሲዬቭ ላይ ተኩሰዋል የተባሉ ሦስት ተጠርጣሪዎች መለየታቸውነ ተገለጸ። ጥቃቱን ፈጽሟል የተባለው ዩክሬን የተወለደው ሩሲያዊ ሉያምቦር ኮርባ ነው። የሩሲያ የመርማሪዎች ኮሚቴ እንዳለው ግለሰቡ ታኅሣሥ ላይ ሞስኮ የገባው ከዩክሬን የደኅንነት ተቋም “የሽብር ድርጊት እንዲፈጽም” ተልዕኮ ተሰጥቶት ነው። ዩክሬን በጥቃቱ እጇ […]
የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲን በድፍረት በመጋፈጡ ዋጋ እየከፈለ ያለው ቢልየነር
ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ 31 ታህሳስ 2025 ተሻሽሏል ከ 5 ሰአት በፊት በ2022 ክረምት ላይ ራፋኤል ዎንግ እና ፊጎ ቻን ሆንግ ኮንግ ወደሚገኝ እስር ቤት አቅንተው ከጂሚ ላይ ጋር ተገናኙ። ቢሊየነሩ ጂሚ ሊ ከሁለት ዓመት በላይ ታስሮ ፍርድ እየተጠባበቀ ነበር። የተከሰሰው ከብሔራዊ ደኅንነት ጋር በተያያዘ ነው። ከሳምንት በፊት ቢልየነሩ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብሏል። በአውሮፓውያኑ […]
ባለንበት ዘመን ወጣቶች ከአዛውንቶች በበለጠ በብቸኝነት የሚሰቃዩት ለምንድን ነው?
ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ ከ 6 ሰአት በፊት የ26 ዓመቱ አዳም ቤኬት በቀዝቃዛው የጥቅምት ወር አንድ ምሽት የሆነውን በሚገባ ያስታውሳል። ጊዜው በአውሮፓውያኑ 2021 ነው። ከአንድ ዓመት በፊት ወደ ብሪስቶል በሥራ ምክንያት ቢመጣም ጓደኛ ለማፍራት ግን ዳገት ሆኖበት ነበር። “ሁሌም ብቻዬን አይደለሁም. . . ግን ባዳነት ይሰማኝ ነበር” ሲል ያስታውሳል። የዚያን ዕለት ወደ ቤቱ እየሄደ […]
ቀጥታ,የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ እና የግብፁ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ በካይሮ
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ እና የግብፁ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ካይሮ ውስጥ ባደረጉት ውይይት ያላቸውን የደኅንነት ትብብር በማጠናከር ላይ መስማማታቸው ተዘገበ። ጭምቅ ሃሳብ የቀጥታ ሽፋን
“በይገባኛል ውዝግብ፣ በአስተዳደር ለውጦች እና በሰላም እጦት” እየተፈተኑ ያሉ የራያ አካባቢ ነዋሪዎች
ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ 7 የካቲት 2026 በትግራይ እና በአማራ ክልል የይገባኛል ጥያቄ ከሚነሳባቸው አካባቢዎች አንዱ የሆነው የራያ አካባቢ ነዋሪዎች በየጊዜው በሚለዋወጥ አስተዳደር እና በሚከሰት ግጭት ምክንያት ሰላማዊ እና የተረጋጋ ሕይወት ከራቃቸው ዓመታት ተቆጥረዋል። የሰሜኑን ደም አፋሳሽ ጦርነት ተከትሎ በአማራ ክልል ሥር የገባው አካባቢው ከዚያ በኋላ አንዴ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ሌላ ጊዜ በአማራ ክልል […]
“ሊቢያ ውስጥ በርካታ ስቃይ ባሳልፍም፤ በአይኤስ የተቀጠፉትን ወንድሞቼን በፍጹም አልረሳም” ዳንኤል አብርሃ
ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ 8 የካቲት 2026, 08:05 EAT ባለፈው ሳምንት “ሃያ ሦስት” የተሰኘ መጽሐፍ ተመርቆ ለንባብ በቅቷል። መጽሐፉ ከአዲስ አበባ ተነስቶ በሱዳን፣ በሊቢያ አድርጎ ወደ አውሮፓ የተሻገረ ወጣት የስቃይ እና የስኬት ታሪክ ነው። ይህ መጽሐፍ የ’አሉ፣ ተባለ’ ታሪክ አይደለም። እውነታውን ከፈረሱ አፍ የሚሰማበት መጽሐፍ ነው። ዳንኤል አብርሃ ታሪኩን ሲጽፈው ቢኒያም አቡራ ደግሞ የአርትዖት […]
ኤርትራ ሠራዊቷን በአስቸኳይ ከግዛቷ እንድታስወጣ እና ለድርድር ዝግጁ እንድትሆን ኢትዮጵያ ጠየቀች
ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ 8 የካቲት 2026, 15:34 EAT የኤርትራ ሠራዊት ተቆጣጣሯቸዋል ካላቸው የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛቶች እንዲወጣ እና ለድርድር ዝግጁ እንዲሆን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጠየቀ። ሚኒስቴሩ ቅዳሜ ጥር 30/2018 ዓ.ም. ለኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ ላይ ኤርትራ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ድንበር በመጣስ በሰሜን ምሥራቅ አቅጣጫ የሚገኙ አካባቢዎችን ተቆጣጥራ እንደምትገኝ ገልጿል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር […]
ሳዑዲ አረቢያ ለሃብታም የውጭ አገር ዜጎች የአልኮል መጠጥ እገዳን አነሳች
ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ 8 የካቲት 2026, 11:53 EAT ሳዑዲ አረቢያ ከ73 ዓመታት እገዳ በኋላ በአገሪቷ የሚኖሩ ቱጃር የውጭ አገር ዜጎች የአልኮል መጠጥ እንዲገዙ መፍቀድ ጀመረች። ይህም ትልቅ እርምጃ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን አስተያየት ሰጪዎች አገሪቷ አሁን ላይ ያላላችውን ሕግ ወደ ጎብኝዎች ታሰፋዋለች ብለው እንደሚጠብቁ የቢቢሲው ሰሚር ሃሽሚ ከሪያድ ዘግቧል። ዲፕሎማሲያዊ መቀመጫ የሆነችው ሪያድ ለአስርተ […]
ትራምፕ በኢራን የንግድ አጋሮች ላይ ታሪፍ መጣል የሚያስችላቸውን ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ፈረሙ
ከኢራን ጋር የንግድ ግንኙነት ባለቸው አገራት ላይ ታሪፍ መጣል የሚያስችላቸውን ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ የፈረሙት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ አገራቱ ከቴህራን ጋር መገበያየት የሚቀጥሉ ከሆነ ቀረጡን ሊጥሉ እንደሚችሉ ተናገሩ። ኦማን ውስጥ እየተካሄደ ባለው ንግግር ኢራን “ስምምነት ላይ ካልደረሰች ውጤቱ በጣም ከባድ ይሆናል” ሲሉም አስጠንቅቀዋል። ጭምቅ ሃሳብ የቀጥታ ሽፋን
