ኢላን መስክ የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ለሚያዘጋጀው ስብሰባ ባለመጋበዙ ቁጣውን ገለፀ

26 መስከረም 2024, 14:39 EAT የዓለማችን ቱጃሩ ሰው ኢላን መስክ የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት በሚያዘጋጀው የኢንቨስትመንት ስብሰባ ላይ ባለመጋበዙ ቁጣውን ገለፀ። ኢላን መስክ፤ ኢንተርናሽናል ኢንቨስትመንት ሰሚት ለተባለው ስብሰባ ያልተጋበዘው ባለፈው ወር በዩኬ በነበረው አመፅ ምክንያት ማኅበራዊ ሚድያ ላይ በለጠፋቸው መልዕክቶች ምክንያት መሆኑን ቢቢሲ ተገንዝቧል። “ማንም ሰው ወደዩኬ መሄድ የለበትም። ወሲባዊ ጥቃት ያደረሱ ሰዎችን እየለቀቁ፤ ማኅበራዊ ሚድያ […]

የሱዳን ጦር በዋና ከተማዋ ካርቱም በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ይዞታዎች ላይ ከፍተኛ ጥቃት ከፈተ

26 መስከረም 2024, 18:19 EAT የእርስ በርስ ጦርነት ላይ ባለችው ሱዳን ጠንካራ አቅም ካለው የፈጥኖ ደራሽ ላይል እየተዋጋ ያለው የሱዳን ጦር በዋና ከተማዋ ካርቱም በሚገኙ የተለያዩ ሥፍራዎች ላይ ጥቃት ከፈተ። የመንግሥት ኃይሎች ካርቱም እና በሰሜናዊው የከተማዋ ክፍል በምትገኘው ባሕሪ የሚገኙ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች (አርኤስኤፍ) ላይ ጥቃት የከፈቱት ሐሙስ ንጋት ነው። የመንግሥት ኃይል እና የአርኤስኤፍ ተዋጊዎች […]