በናይጄሪያ ከ50 በላይ ሕጻናት በታጣቂዎች መታገታቸው ተገለጸ

ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ ታትሟልከ 7 ሰአት በፊት የንባብ ጊዜ: 2 ደቂቃ በሰሜን ምሥራቅ ናይጄሪያ ከሦስት ትምህርት ቤቶች ከ50 በላይ ሕጻናት በታጣቂዎች መታገታቸው ተገለጸ። መምህራን እና ወላጆች ለቢቢሲ እንደገለጹት፤ አብዛኞቹ ታግተው የተወሰዱት ልጆች ዕድሜያቸው ከሁለት ዓመት እስከ አምስት ዓመት ነው። ሙሳ ቦንቶ በተባለው ግዛት ያለፈው አርብ ጥቃቱ ሲፈጸም በቦታው የነበሩ የዐይን እማኞች እንደተናገሩት፤ ታጣቂዎቹ […]

የእንግሊዝ ተዋጊ ጄቶች የኢራንን ድሮን ለማክሸፍ ሚሳዔል ሊገጠምላቸው ነው

ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ ታትሟልከ 8 ሰአት በፊት የንባብ ጊዜ: 2 ደቂቃ በመካከለኛው ምሥራቅ የተሰማሩ የእንግሊዝ ተዋጊ ጄቶች የኢራን ድሮኖችን ማምከን የሚችሉበት አዲስ ሚሳዔል ሊገጠምላቸው ነው። የሚገጠምላቸው ሚሳዔል በአነስተኛ ገንዘብ የኢራንን ድሮኖች ለማክሸፍ እንደሚውል ተገልጿል። የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር “ዒላማዎችን ለመምታት አሁን ጥቅም ላይ እየዋለ ካለው ሚሳዔል የሚረክስ ዘመናዊ መሣሪያ ነው” ሲል ገልጾታል። ይህ ፀረ […]

ትራምፕ ከቻይናው መሪ ጋር ከተገናኙ በኋላ ታይዋን ነጻነቷን እንዳታውጅ አስጠነቀቁ

ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ ታትሟል16 ግንቦት 2026 የንባብ ጊዜ: 3 ደቂቃ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ታይዋን ከቻይና የተነጠለች ነጻ አገር መሆኗን እንዳታውጅ አስጠነቀቁ። ትራምፕ አርብ ዕለት በቻይና ቤይጂንግ የሁለት ቀን ይፋዊ ጉብኝታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ለፎክስ ኒውስ በሰጡት ቃለ ምልልስ ወቅት “አንድ አካል ነፃ እንዲሆን አልፈልግም” ብለዋል። ቀደም ሲል የታይዋን ፕሬዝዳንት ላይ ቺንግ-ቴ፣ ታይዋን ራሷን […]

ቀጥታ,የኢራን እና አሜሪካን የሰላም ንግግር ለማስቀጠል የፓኪስታን ባለሥልጣን ቴህራን ገቡ

የፓኪስታን የአገር ውስጥ ሚኒስትር ሞህሲን ናቂቭ በኢራን እና አሜሪካ መካከል የተቋረጠውን የሰላም ንግግር ለማስቀጠል ቴህራን መግባታቸው ተገለጸ። የጉዞው ዓላማ “ንግግሮች እንዲካሄዱ ለማመቻች እና ቀጣናዊ ሰላም ለማስፈን” መሆኑ ተገልጿል። ጭምቅ ሃሳብ የቀጥታ ሽፋን

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አገራዊ ምክክር እየተደረገ ያለው የአገሪቱን መሪ የሥልጣን ዘመን “ለመገደብ” መሆኑን ተናገሩ

ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ ታትሟል15 ግንቦት 2026 የንባብ ጊዜ: 3 ደቂቃ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አገራዊ ምክክር እየተደረገ ያለው በአገሪቱ ሕገ መንግሥት ያለ ማብቂያ የተቀመጠውን የአገሪቱን መሪ የሥልጣን ዘመን “ለመገደብ” መሆኑን ተናገሩ። መንግሥት “ሥልጣኑ በሕግ ተገድቦ” ሕገ መንግሥት እንዲሻሻል እየጠየቀ ባለበት ሁኔታ በአገራዊ ምክክሩ “አንወያይም” ያሉ አካላትን ተችተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህንን የተናገሩት የአገራዊ […]

እስራኤል በጋዛ የአየር ጥቃት የሐማስ አዛዥን እንደገደለች አስታወቀች

ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ ታትሟል16 ግንቦት 2026 የንባብ ጊዜ: 2 ደቂቃ እስራኤል በጋዛ በፈፀመችው የአየር ጥቃት የሐማስ አዛዥ ኢዝ አድ-ዲን አል-ሐዳድን እንደገደለች አስታወቀች። አዛዡ “የመስከረም 26ቱን ጥቃት ከአቀነባበሩት አንደኛው” መሆናቸው ተገልጿል። የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የመከላከያ ሚኒስትሩ እዝራኤል ካትዝ በጋራ ባወጡት መግለጫ ሐዳድ “በሺዎች ለሚቆጠሩ እስራኤላውያን እና ወታደሮች [የእስራኤል መከላከያ ኃይሎች] መገደል፣ […]

በዩክሬን የደራው የማህፀን ኪራይ ለእናቶች ምን ያህል ገንዘብ ያስገኛል?

ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ ታትሟልከ 9 ሰአት በፊት የንባብ ጊዜ: 6 ደቂቃ ካሪና የስድስት ወር ነፍሰጡር ናት። ነገር ግን በማህፀኗ ውስጥ ያለው ሕፃን የራሷ አይደለም። የ22 ዓመቷ ከምሥራቅ ዩክሬን የመጣችው ካሪና የማህፀን አከራይ እና (ሰሮጌት) ናት። ከቻይናዊያን ጥንዶች የእንቁላል እና የዘር ፍሬ የተፈጠረ ሽል ተሸክማለች። ካሪና ገና በ17 ዓመቷ ነበር በሩሲያ ወረራ የመጀመሪያ ምዕራፍ […]

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን የኒውክሌር ፕሮግራሟን ለ20 ዓመታት ብትገታ እንደሚቀበሉ ተናገሩ

ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ ታትሟል16 ግንቦት 2026 የንባብ ጊዜ: 2 ደቂቃ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቴህራን ለ20 ዓመታት የኒውክሌር መርሃ ግብሯን ብትገታ እንደሚቀበሉ ያሳወቁ ሲሆን፤ ይህም ከዚህ በፊት ሙሉ ለሙሉ ማቆም አለባት ከሚለው አቋማቸው ለውጥ ማድረጋቸውን አሳይቷል። ትራምፕ “እውነተኛ 20 ዓመት” መሆን አለበት ብለዋል። ቀደም ሲል ፕሬዝዳንቱ ኢራን መሣሪያ ማምረት በሚያስችላት ደረጃ ዩራኒየም ማበልፀጓን […]

ስዊትዘርላንድ በኦሽዊትዝ አይሁዶችን ሲያሰቃይ ስለ ነበረው ‘አስፈሪው ዶክተር’ ምስጢራዊ ሰነዶችን ይፋ ልታደርግ ነው

ዳታን በመቆጠብ ጽሑፍ ብቻ ለማንበብ ታትሟል16 ግንቦት 2026 የንባብ ጊዜ: 6 ደቂቃ የስዊስ የፌደራል ደህንነት አገልግሎት ለረዥም ጊዜ ተዘግቶ የቆየውን የናዚ ጦር ወንጀለኛው ጆሴፍ ሜንጌሌ ሰነዶች ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታወቀ። ሰነዶቹ ይፋ የሚደረጉት መቼ እንደሆነ ግን ከመግለጽ ተቆጥቧል። ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ ሜንጌሌ ወደ አውሮፓ የተሰደደ ሲሆን ምንም እንኳን ዓለም አቀፍ የእስር ትዕዛዝ ቢወጣበትም ስዊዘርላንድ […]