ንብ ባንክ እንቅስቃሴዎች በመዳከማቸው ምክኛት የቦርድ አባላቱ እየተወዛገቡ ነው ።

December 3, 2023 – EthiopianReporter.com  በዳዊት ታዬ December 3, 2023 በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት የግል ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው ንብ ባንክ፣ አጋጥሞታል በተባለ የእንቅስቃሴ መዳከም ምክንያት፣ የባንኩ የቦርድ አባላት ውዝግብ ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጣልቃ በመግባት የባንኩን ባለአክሲዮኖች ለጠቅላላ ጉባዔ መጥራቱ ታወቀ። የባንኩ ውስጣዊ ችግርን መነሻ አድርጎ በባንኩ የቦርድ አመራሮች መካከል የተፈጠረ ውዝግብ፣ […]

በርካታ የኢዜማ አመራሮች መልቀቂያ ማስገባታቸው ተነገረ

ዜና በርካታ የኢዜማ አመራሮች መልቀቂያ ማስገባታቸው ተነገረ ዮናስ አማረ ቀን: December 3, 2023 የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ፓርቲ ሦስት አመራሮች ለፓርቲው የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸው ተነገረ፡፡ ፓርቲው ባለው ሁለት ዓይነት መዋቅር ማለትም በትይዩ ካቢኔና በሥራ አስፈጻሚ ውስጥ ሲሳተፉ የቆዩ የፓርቲው አመራሮች መልቀቂያውን ማስገባታቸው ታውቋል፡፡ መልቀቂያውን ካስገቡት መካከል ባንትይገኝ ታምራት (ዶ/ር) አንዱ ሲሆኑ፣ በድርጅቱ መሪ በብርሃኑ […]

ዩናይትድ ኪንግደም የሐማስ ታጋቾችን ለመፈለግ የቅኝት በረራዎችን ልታካሂድ ነው

ከ 7 ሰአት በፊት ዩናይትድ ኪንግደም የሐማስ ታጋቾች ያሉበትን ቦታ ለመፈለግ በመካከለኛው ምሥራቅ የቅኝት በረራዎች እንደምታካሂድ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። በረራዎቹ ታጋቾቹ የት እንዳሉ የሚጠቁሙ የደኅንነት መረጃዎችን ለመሰብሰብ ይረዳሉ ተብሏል። ሐማስ በእስራኤል ላይ የፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ አምስት የእንግሊዝ ዜጎች የጠፉ ሲሆን፣ የዩኬ መንግሥት ምን ያህሎቹ በሐማስ እገታ ሥር ሊሆኑ እንደሚችሉ አልገለጸም። ሚኒስቴሩ “ የዜጎቻችን ደኅንነት ከሁሉም […]

የአሜሪካ ኤምባሲ አዲስ አበባን ፊንፊኔ ሲል መጥራቱ ተቃውሞን አስነሳ

Saturday, 02 December 2023 19:36 Written by  መታሠቢያ ካሣዬ መቀመጫውን በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያደረገው በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ርዕሰ መዲናይቱን አዲስ አበባን ፊንፊኔ ሲል መጥራቱን ሃያሁለት  የሲቪክ ማህበራት ድርጅቶች ተቃወሙት። ማህበራቱ ተቃውሞአቸውን በመግለፅ ለአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ቢሊንከን ደብዳቤ ልከዋል።ኤምባሲው የሚሰጣቸውን የቪዛና ሌሎች አገልግሎቶችን አስመልክቶ ከትናት በስቲያ በማህራዊ ትስስር ገፁ […]

ፖሊስ በሞስኮ በሚገኙ የተመሳሳይ ጾታ የምሽት ክበቦች ላይ ዘመቻ አካሄደ

ከ 8 ሰአት በፊት በቅርቡ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እንቀስቃሴን ሕገወጥ በማለት የፈረጀችው ሩሲያ በሞስኮ በሚገኙ የተመሳሳይ ጾታ የምሽት ክበቦች (ክለቦች) ላይ ዘመቻ ማካሄዷ ተዘግቧል። ፖሊስ በርካታ የተመሳሳይ ጾታ ክለቦችን ጥሶ በመግባት የተወሰኑትን ታዳሚዎች አጠር ላለ ጊዜ በቁጥጥር ስር ማዋሉንም አስቶሮዥኖ ኖቮስቲ የተሰኘው የቴሌግራም ገጽ ዘግቧል። በተጨማሪም የአንዳንዶች ፖስፖርት ተወስዶ ፎቶ እንዲነሳ ተደርጓል ተብሏል። በክለቡ ተገኝቶ […]

በአማራ ክልል የተጣለው የኢንተርኔት እገዳ እንዲነሳ ጥሪ ቀረበ

December 3, 2023 – Addis Admas  – ከ150 አገራት የተውጣጡ 300 የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እገዳው እንዲነሳ ጠይቀዋል  – የእገዳ ተግባሩ ከሌሎች የአፍሪካ አገራት በኢትዮጵያ የከፋ ነው ተብሏል                     በአማራ ክልል የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ በመንግስት የተወሰደውን የኢንተርኔት እገዳ እርምጃ በመቃወም መንግስት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እገዳውን እንዲያነሳና መደበኛ የኢንተርኔት አግልግሎት መስጠቱን… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ […]

ጦርነቱ ከጀመረ ወዲህ እስራኤል ከባድ የአየር ጥቃት መፈፀሟን ነዋሪዎች ተናገሩ

ከ 8 ሰአት በፊት እስራኤል በደቡባዊ ጋዛ በምትገኘው ኻን ዩኒስ ከተማ ከባድ የአየር ድብደባ ፈፀመች። የከተማዋ ነዋሪዎች ድብደባው ጦርነቱ ከጀመረ ወዲህ የከፋው ነው ብለዋል። በከተማዋ ምሥራቃዊ አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎችም አካባቢውን ለቀው ወደ ደቡባዊ ክፍል እንዲሄዱ በእስራኤል ጦር ተነግሯቸዋል። እስራኤል የሰሜን ጋዛ ተፈናቃዮችን ባስጠለለችው በዚች ከተማ የተወሰኑ የሐማስ መሪዎች እንዳሉ ታምናለች። በሐማስ የሚተዳደርው የጋዛ ጤና ሚኒስቴር […]

ኢትዮጵያ በከፋ ችግርና የደህንነት ስጋት ውስጥ ትገኛለች ተባለ

December 3, 2023 – Addis Admas    የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላም ፍላጎት የለውም ተብሏል የአሜሪካ ህግ አውጭ ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ መክሯል     የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልክዕክተኛ ማይክ ሐመር                                   የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጪ ጉዳይ ኮሚቴ የአፍሪካ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ሲመክር ውሏል፡፡ ምክር ቤቱ በቀጥታ በሚተላለፈው … … ሙሉውን ለማየት ወይም […]

በፓሪስ በደረሰ የስለት እና የመዶሻ ጥቃት የሰው ሕይወት አለፈ

ከ 9 ሰአት በፊት በማዕከላዊ ፓሪስ ላይ በደረሰ የስለት እና የመዶሻ ጥቃት አንድ ሰው ሲገደል ሁለት ሰዎች ቆሰሉ። ጥቃቱ የተፈጸመው ቅዳሜ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ በታሪካዊው ኤይፍል ታወር አካባቢ በምትገኘው ኩዋይ ደ ግሬኔሌ ሰፈር ነው። የፈረንሳይ ዜግነት ያለው የ26 ዓመቱ ጥቃት አድራሽ በቁጥጥር ስር ውሎ የጸረ ሽብርተኝነት አቃብያነ ሕግ ምርመራ ከፍተውበታል። በጥቃቱ የተገደለው ግለሰብ ጀርመናዊ […]

“በውሻ መነከስ፣ ድብደባ እና ምግብ መከልከል” የፍልስጤማውያን መከራ በእስራኤል እስር ቤቶች

3 ታህሳስ 2023, 08:19 EAT የጋዛ የተኩስ አቁም ፋታ ለማድረግ በተደረሰው ስምምነት ከእስራኤል እስር ቤቶች የተፈቱ ፍልስጤማውያን ስቃይ እና ግፎች እንደደረሰባቸው ተናገሩ። በእስራኤል እስር ቤቶች ውስጥ ውሻ ይለቀቅባቸው፣ ድብደባ ይፈጸምባቸው እንዲሁም ምግብ ይከለከሉ እንደነበር ለቢቢሲ ገልጸዋል። የእስር ቤት ጠባቂዎቹ ልብሳቸውን እና ብርድ ልብሳቸውን በመግፈፍ የሚመገቡትነ ምግብም መሬት ላይ ይደፉባቸው ነበር ብለዋል። በቅርቡ ከተለቀቁ ፍልስጤማውያን መካከል […]