የጴጥሮሳውያን ኅብረት ጸሐፊ የሆኑት መምህር ተሾመ በየነ በጸጥታ አካላት ተወሰዱ !

May 23, 2023 – Konjit Sitotaw  የጴጥሮሳውያን ኅብረት ጸሐፊ የሆኑት መምህር ተሾመ በየነ በጸጥታ አካላት ተወሰዱ ! ++++ በቋሚ ሲኖዶስ መልካም ፈቃድ ጥር 24 ቀን 2015 ዓ.ም የተቋቋመውን ሀገር አቀፍ የቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ጉዳይ አስተባባሪ ዐቢይ ኮሚቴ በጸሐፊነት እንዲያገለግሉ ተመድበው የነበሩት መምህር ተሾመ በየነ በዛሬው ዕለት በጸጥታ አካላት ተወስደዋል። መምህር ተሾመ የጴጥሮሳውያን ኅብረት ጸሐፊ ሲሆኑ ኅብረቱን ወክለው […]

ኦሮሞ ኤጲስ ቆጶሳትን ምልመላና ምርጫ የሚያከናውን 7 ሊቃነ ጳጳሳት ያሉት አስመራጭ ኮሚቴ ተመርጧል

May 23, 2023 – Konjit Sitotaw  የዘጠኙ አዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ሥርዓተ ሢመት ሐምሌ 9/2015 እንደሚከናወን ተገለጸ የኤጲስ ቆጶሳቱን ምልመላና ምርጫ የሚያከናውን 7 ሊቃነ ጳጳሳት ያሉት አስመራጭ ኮሚቴ ተመርጧል በኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተመረጡ ዘጠኝ አዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ሥርዓተ ሢመት ሐምሌ 9/2015 እንደሚከናወን የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አስታወቀ። ምልዓተ ጉባኤው የአዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ምልመላና ምርጫ […]

የሀገር አቀፍ የቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ጉዳይ አስተባባሪ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ በእስር ላይ እንደሚገኙ ተረጋግጧል።

May 23, 2023 የሀገር አቀፍ የቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ጉዳይ አስተባባሪ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ በእስር ላይ እንደሚገኙ ተረጋግጧል። የነገረ መለኮት ምሩቃን ማኅበር ሰብሳቢና የሀገር አቀፍ የቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ጉዳይ አስተባባሪ ዐቢይ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ የሆኑት ቀሲስ አክሊሉ ዳምጠው ትናንት ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም በጸጥታ አካላት የተወሰዱ ሲሆን በአኹኑ ሰዓት ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን ውስጥ […]

የኑሮ ውድነቱ እየባሰ እንጂ እየቀነሰ አልሄደም

May 23, 2023 – Konjit Sitotaw  በኢትዮጵያ ከቀን ቀን እየተባባሰ የሄደው የኑሮ ውድነት የምግብ፣የፍጆታ፣የቁሳቁሶች፣የትራንስፖርትና የአገልግሎት ዋጋ ግሽበት አብዛኛውን ዜጋ አቅም አሳጥቷል።በተለይ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች የኑሮ ውድነትን መቋቋም የማይችሉበት ደረጃ ላይ ከደረሱ ሰንብቷል።  የቤት ኪራይ ዋጋ እና የተለያዩ አገልግሎቶች ክፍያ በየጊዜው መናር ኑሮን እጅግ አክብዶታል። መንግሥት  ለዓመታት የዘለቀውን የዋጋ ንረት ለማቃለል ይረዳሉ ያላቸውን የተለያዩ ዕርምጃዎችን መውሰዱን […]

ምዕራብ ጎጃም ለሁለት ተከፈለ

May 23, 2023 – Konjit Sitotaw ቀደም ሲል የምዕራብ ጎጃም ዞን በ14 የገጠር ወረዳዎችና በስምንት የከተማ አስተዳደሮች ተዋቅሮ ማዕከሉን ፍኖተ ሰላም አድርጎ ሲተዳደር ነበር። ሆኖም አንዳንድ ወረዳዎች ከማዕከሉ የራቁ በመሆናቸው አስተዳደራዊ ሥራዎችን ለማከናወን ነዋሪዎቹ ተቸግረው እንደቆዩና «ዞን ይከፈልልን» ጥያቄያቸውን በተደጋጋሚ ሲያቀርቡ እንደ ነበር ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። ሆኖም ከብዙ ጊዜ በኋላ ጥያቄው ቢመለስም ማዕከሉ ባሕር ዳር መሆኑ ተገቢ […]

በኮሌራ መስፋፋት የተቆጡ የደቡብ አፍሪካዋ ከተማ ነዋሪዎች ከንቲባቸውን አሳደዱ

May 23, 2023 – BBC Amharic  ከ 4 ሰአት በፊት በኮሌራ መስፋፋት እጅግ የተቆጡ ደቡብ አፍሪካውያን ሰኞ ዕለት ከንቲባቸውን መንገድ ለመንገድ ሲያሳድዷቸው ታይተዋል። ነዋሪዎቹ፤ ከንቲባው ንፁህ ውሃ ማቅረብ ተስኗቸዋል ሲል ወቀሳቸውን ያሰማሉ። ከደቡብ አፍሪካ ግዛቶች በርካታ ሕዝብ ይኖርባታል በምትባለው ጋውቴንግ በኮሌራ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 15 ደርሷል። የሺዋኔ ከተማ ከንቲባ ሲሊዬርስ ብሪንክ ከብሔራዊው መንግሥት ከሚመጡ ባለሥልጣናት ጋር ለመምከር […]

ህወሓትን በድጋሚ ለማስመዝገብ ማመልከቻ እንደማይገባ የፓርቲው ሊቀመንበር አስታወቁ

May 23, 2023 – VOA Amharic  ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ(ህ.ወ.ሓ.ት) ሊቀ መንበር ዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል፣ የድጋሚ ምዝገባ ለማድረግ፣ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማመልከቻ እንደማያስገባ አስታወቁ። “50 ዕድሜ ያለውን ሰው እንደ ዐዲስ አኹን ጀምር እንደማለት ነው” ያሉት ሊቀመንበሩ “ረዥም ዕድሜ ያለው ፓርቲ በሌላ መንገድ ራሱ ካልፈረሰ ይቀጥላል” ብለዋል።ፓርቲያቸውም ኾነ ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሰጠውን የህጋዊነት […]

በትግራይ ያለው ሰብአዊ ቀውስ እጅግ አሠቃቂ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ

May 23, 2023 – VOA Amharic  የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት፣ በትግራይ ክልል ያለው ሰብአዊ ቀውስ፣ እጅግ አሠቃቂ ደረጃ ላይ በመድረሱ፣ የሚመለከታቸውን አካላት ትኩረት እንደሚሻ አስታወቀ፡፡ ምክር ቤቱ በአወጣው መግለጫ፣ የአሜሪካ የዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ/USAID/ እና የዓለም ምግብ ፕሮግራም/WFP/ ለትግራይ ክልል ሲያቀርቡት የነበረውን ሰብአዊ ርዳታ በማቋረጣቸው፣ ተረጅዎች ጭንቀት ውስጥ መግባታቸውን ገልጿል፡፡ በትግራይ ያለው ሰብአዊ ቀውስ እጅግ […]

ከሱዳን በቀን እስከ 800 ፍልሰተኞች በመተማ በኩል ይገባሉ

May 23, 2023  የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች፣ ካለፈው ወር ሚያዝያ ሰባት ቀን ጀምሮ፣ በካርቱም እና በሌሎች አካባቢዎች በሚያካሒዱት ግጭት ምክንያት፣ 25ነጥብ7 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች፣ አስቸኳይ ሰብአዊ ርዳታ ፈላጊዎች ኾነዋል። ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት(IOM)፣ ረቡዕ ዕለት ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው፣ በመላው ሱዳን ቢያንስ 843ሺሕ130 ሰዎች ሲፈናቀሉ፣ ወደ 259ሺሕ የሚደርሱ ሰዎች ደግሞ ወደ ጎረቤት […]

በጋዜጠኛና የታሪክ ምሁሩ አቶ ታዲዎስ ታንቱ የክስ ሂደት ላይ ሲካሄድ የነበረው ምስክር የመስማት ሂደት ተቋረጠ

May 23, 2023  በጋዜጠኛና የታሪክ ምሁሩ አቶ ታዲዎስ ታንቱ የክስ ሂደት ላይ ሲካሄድ የነበረው ምስክር የመስማት ሂደት ተቋረጠ! ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ጀነራል አበባው ታደሰ ፍርድ ቤት አንቀርብሞ ብለዋል በዛሬው ችሎት አቃቤ ህግ “የሰነድ ማስረጃዎች ከቀረበው ክስ ጋር ግንኙነት የላቸውም እንዲሁም እንዲመሰክሩ የተጠሩት ምስክሮች ተከላከሉ ከተባሉበት አግባብ አንፃር ትክክለኛና ቀጥተኛ የሆኑ ስላልሆኑ ሊሰሙ አይገባም” ሲል በፅሁፍ […]